Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_haileleul_mekonnen — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_haileleul_mekonnen — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የሰርጥ አድራሻ: @dr_haileleul_mekonnen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.35K
የሰርጥ መግለጫ

📞 0974013612 በመደወል አስፈላጊዉን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ።
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን ተጭናችሁ 👉
@drhaileleulmd
ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-17 06:39:46
Morning Motivation|ምክረ_ማለዳ

ብዙ ጊዜ ህይወትህን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ ጥረት አድርገህ ይሆናል።ትንሽ ቆይተህ ደግሞ ወደ ቀድሞዉ እና ወደ ማትፈልገዉ ህይወት ውስጥ ገብተን ትገኛለህ።

ታድያ ራስን ፈፅሞ ለመለወጥ  መፍትሄው ምን ይሆን ?

ራስን ማወቅ ትልቅ ማንነትን የመገንባት እና ራስን ማብቂያ መንገድ ነው።

ሁሌም ራስን ለማበልፀጊያ ጊዜ ስጥ፤ራስህን እንደ መፅሐፍ በጥልቀት አንብብ ፣ገምግም፣መርምር፣ የውስጥህን ፍላጎት አድምጠዉ ፣ ሰዎችን ለመምሰል ሳይሆን የራስህን መንገድ እያየህ ተጓዝ፤ ያንጊዜ የምትፈልገዉን ማንነት ወደመሆን ትመጣለህ።

     ጁመዓ ሙባረክ


በዶክተር ኃይለልዑል የሚቀርቡ የጤና መረጃዎችን ለመከታተል ድረ ገፃችንን ይጎብኙ

www.doctorhaileleul.com
445 views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 18:29:35
እረ ልጄን አምጡልኝ!

* ጉድ ሆንኩ

#Ethiopia | ይህቺ የ2 ዓመት ጨቅላ ህፃን ሶልያና ዳንኤል ትባላለች።

የወንድማችን #Daniel Mulu ልጅ ናት።

ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አካባቢ ቤዛዊት በቀለ የተባለችዉ ሞግዚቷ ይዛት ተሰዉራለች:: ሞግዚቷ ከተቀጠረች 20 ቀናት ሆኗታል።

ወላጆች ለሥራ ሲወጡ ልጃቸው፣ ሞግዚቷና አያቷ በቤት ውስጥ ነበሩ።

እናትና አባት እያለቀሱ ጭንቅ ላይ ናቸው!

ንፋስ ስልክ ወረዳ 9 ፖሊስ መምሪያ - መጥፋቷን አመልክተናል።

በትራንስፖርትም ሆነ በመንገድ ላይ አጠራጣሪ ነገር ከተመለከታችሁ ደውሉልን።

+251-951-090999 - ዳንኤል
+251-947-365252 - የውብዳር

ወይንም

በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ አሳውቁልን።

"ለልጄ ፀልዩልኝ " - እናት የውብዳር

"እረ ልጄን አምጡልኝ!" - አባት ዳንኤል

እግዚአብሔር ይስጥልን!
998 viewsedited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 18:01:10
#ምግብ ያለመብላት በሽታ

(በ ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

#አኖሬክዚያ_ነርቮሳ (Anorexia Nervosa)

ይህ በሽታ ከአዕምሮ በሽታዎች አንዱ ሲሆን ፤ የዚህ በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ስለሚበሉት እና ስለ መወፈር አብዝቶ የሚያሳስባቸው ሲሆን መወፈርን እጅግ አብዝተው የሚጠሉ ናቸው::

ይህ በሽታ በሴቶች ላይ ጎልቶ የሚስተዋል ሲሆን በአብዛኛው እድሜያቸው ከ 20 ዓመት በታሽ የሆኑትን ያጠቃል::

የዚህ በሽታ መለያው ምንድነው?

እራስን ለረሃብ ማጋለጥ

መወፈርን አጥብቆ መፍራት እና መጨነቅ

ውፍረትን ለመቀነስ በማሰብ ትንሽ መብላት

የበሉትን ምግብ ማስመለስ

የምግብ ሰዓትን ማሳለፍ

ከመጠን በላይ ከስተው እያሉ የራሳቸውን ሰውነት እጅግ በጣም እንደወፈረ ማሰብ

በበሽታው ምክንያት በሰውነት ላይ የሚታዩ ምልክቶች አሉ?

ለልብ በሽታ መጋለጥ
ሰውነት መድከም እና ሁሌም ብርድ ብርድ ማለት

በሴቶች የወር አበባ መዛባት እንዲሁም ለተከታታይ ጊዜያት የወር አበባ አለማየት
የሆድ ድርቀት
የእንቅልፍ ችግር
የማሰብ እና የማስታወስ ችሎታ መቀነስ
ለድብርት በሽታ መጋለጥ

ለዚህ በሽታ መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

የአመጋገብ ስርዓትን ለመቀየር ከሃኪም ጋር መማክር

የስነልቦና ህክምና

ሌሎች የጤና መረጃዎችን ለማግኘት ድረ ገፃችንን ይጎብኙ


www.doctorhaileleul.com
1.0K viewsedited  15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 16:22:13
በጠዋት ዉሃ የመጠጣት ልምድ አላችሁ ?

ሼር ያድርጉ

በጠዋት ከእንቅልፍ እንደተነሱ በባዶ ሆድ ውሃ የመጠጣት 8 ጥቅሞች :-

አንጀትን ያጸዳል፣ ንጥረ ምግቦችን በቀላሉ ለመምጠጥ ያስችላል።

የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ይረዳል እንዲሁም አንጀትዎን እና ፊኛዎን ከተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ ይረዳል።

የእርስዎን የንቃተ ህሊና፣ የማስታወስ እና የአዕምሮ ብቃትን ይጨምራል።

የአዲስ የጡንቻ ሴሎችን እና የደም ሴሎችን መመረት ይጨምራል፣

ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።

የሚያበራ ቆዳ፤ ውሃ ከደም ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማጽዳት ይረዳል፣ ይህም ቆዳዎ ብሩህ እና ንጹህ እንዲሆን ይረዳል።

ጤናማ አንፀባራቂ ፀጉር እንዲያድግ ያበረታታል ።

የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያጠናክራል እና የሊምፍዎን(lymph) ሚዛን ያስተካክላል፣ እነዚህ እጢዎች የእለት ተእለት ተግባራትን እንዲያከናውኑ፣የሰውነትዎን ፈሳሽ ማመጣጠን እና ኢንፌክሽንን ለመከላከል እና ለመዋጋት ይረዳሉ።

በዩትዩብ የጤና መረጃ ለማግኘት



484 views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 20:31:45
ኩላሊት መድከሙን የሚያሳዪ ምልክቶች በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን አጠር ያለ ገለፃ ተዘጋጅቷል ሙሉዉን ለማየት ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ ።




611 viewsedited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 08:27:11 በግል ለማግኘት ወይም ቀርባችሁ ህክምና ማድረግ የምትፈልጉ፣ በዚህ አድራሻ ቀጠሮ ማስያዝ ትችላላችሁ።




@DrHaileleulMD

ቀጠሮ የሚያዝበት ሰዓት ከ ቀኑ 10:00 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ብቻ ነዉ ።
615 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 15:44:09
ወቅቱ የፆም ወር እንደመሆኑ ቴምር ከወትሮው በተለየ መልኩ በገበያ ላይ እናገኛለን።

ታድያ በዚህ ወቅት ቴምርን አዘውትሮ መመገብ በርካታ የጤና በረከቶች እናገኛለን።

የቴምር የጤና በረከቶች

በሰዉነትታችን የሚገኘውን የስብ ክምችት(cholesterol )ይቀንሳል

የሆድ ድርቀትን ይከላከላል/ይፈውሳል፤

ክብደትን ለመጨመር ይረዳል።

የልብ ጤንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል

ቴምር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ እንደመሆኑ ጉልበት/ኃይል ይሰጠናል ።

ጤናማ የሆነ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ያደርጋል።

ጥርሳችን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል

የአጥንት ጥንካሬን ይጨምራል
397 views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 17:31:00
የመስማት ችግር እንዳይገጥምዎ ማድረግ የሌለብዎ ነገሮች
1.በእንጨት ወይም ሹል ነገር በጆሮዎ ውስጥ መክተት አይገባም
2. የመዳመጫ ቁሳቁሶቹን አይዋዋሱ
3. ለከፍተኛ ድምጽ አይጋለጡ
4. በቆሻሻ ውሃ ውስጥ አይዋኙ ወይም አይታጠቡ
#WorldHearingDay2023 #HearingCare #safelistening
678 views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:51:41
ለጤና ባለሙያዉ እንድረስለት

ከታች የምትመለከቱት ወንድማችን ተሾመ አበራ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በደምቢ ዶሎ ከተማ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን  እዛው በማጠናቀቅ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመሄድ በህብረተሰብ ጤና ት/ት ክፍል በጥሩ ዉጤት ተመርቆ ህብረተሰቡን እያገለገለ ለተወሰነ ጊዜ ቢቆይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት እንደቀድሞዉ መስራት አልቻለም።

በአካባቢው ባለ ሆስፒታል ቢታከምም ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እና ወደ አማኑኤል ሆስታፒል ሪፈር ቢፃፍለትም ወላጅ እናቱ ብቻቸውን በመሆናቸው እሱን ለማሳከም ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል ።

አቅማችንሁ በፈቀደ መጠን በእናቱ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት እጃችሁን እንድትዘረጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።

# 1000527420265(CBE-አያሉ)

ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ::

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
4.3K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 20:27:04
"የጥርስ ሳሙናን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣልና አልጠቀምም!"

ይህ የበርካታ ታካሚዎች ፍላጎት ሲሆን ዳሩ ግን ቀድሞ የነበረንን ጠረን ስለሚያጠፋ እንጂ ለአዲስ መጥፎ የአፍ ጠረን አይዳርገንም።

ብዙን ጊዜ የአፋችንን ንፅህና ከመጠበቅ በምንሰንፍበት ጊዜ ልማም እና ሻሃላ(Plaque & calculus) የመከማቸት ዕድልን ስለሚያሰፋ ይህ ክምችት ድድ እና የመንጋጋ አጥንትን ከመብላት እና የድድ እና የመንጋጋ አጥንት ኢንፌክሽን ከማምጣትም ባለፈ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ይዳርጋል።

በተለምዶ ሽቶ ስንጠቀም ከሰዓታት በኋላ ለሽቶው ጠረን አፍንጫችን ለማዳ ይሆንና ልዩነቱ ብዙም አይታወቀንም ለሌላ ሰው ግን የሽቶው መዓዛ እንደ አዲስ የሚሸት ሲሆን መጥፎ የአፍ ጠረንም እንደዛው የአፍ ንፅህናችን ሳንጠብቅ ስንቀር አፍንጫችን ይለምደውና መጥፎ የአፍ ጠረን ያለንም አይመስለንም።

ነገር ግን የጥርስ ሳሙና ከይዘቶቹ መካከል ጥሩ መዓዛ ሰጪ ይዘት(Flavoring Agent) አንዱ ሲሆን ጥርሳችንን በምንቦርሽበት ወቅት አፋችን ጥሩ ጠረን ይኖረውና ለቀናት በጥርስ ሳሙና መቦረሽ ስናቋርጥ እንደ አዲስ ለሚመጣው መጥፎ የአፍ ጠረን አፍንጫችን መልመድ ስለሚጀምር ጠረኑ የመጣው ባለመቦረሻችን ሳይሆን በጥርስ ሳሙናው ይመስለናል እንጂ የጥርስ ሳሙና መጥፎ የአፍ ጠረን ያጥፋ እንጂ አያባብስም።

በመጨረሻም የአፋችንን ንፅህና የጥርስ ሳሙናና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ተጠቅመን ጠዋት ከቁርስ በኋላ እና ማታ ከመኝታ በፊት መቦረሽ ይመከራል።

ታሞ ከማማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነውና ነገሩ በየ ስድስት ወሩ ማለትም በዓመት ሁለት ጊዜ በሐኪም መታየት ይመከራል።

ቸር ያሰማን

በዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ: Dental Surgeon
684 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ