2022-06-01 17:57:18
ብጉር ከመክሰሙ በፊት የቆዳ ቁጣ የሚያስከትል ከሆነ፣ ጠባሳ እና ጥቋቁር ነጠብጣብ የመፍጠር እድል አለው።
ብጉር ጠባሳ እንዳይፈጥር የሚደረጉ ጥንቃቄዎች።
ብጉርን አለመነካካት፣
አለማፈንዳት እና፣
የህክምና ክትትል በማረግ የሚሰጡ መዳኒቶችን በሀኪም ትእዛዝ ብቻ መጠቀም ያስፈልጋል።
በተደጋጋሚ የሚወጣ ብጉር፣ ተደጋጋሚ ክትትል ያስፈልገዋል።
የብጉር ጠባሳ የሚያብጥ ወይም ደሞ የሚሰረጉድ ሊሆን ይችላል።
ባጠቃላይ 4 አይነት የብጉር ጠባሳዎች አሉ።
3 የሚሰረጉድ እና
1 የሚያብጥ
የብጉር ጠባሳ አይነት የሚወሰነው፣ በቆዳ ተፈጥሮ እንዲሁም በወጣው የብጉር አይነት እና ደረጃ ስለሆነ፣ አንድ ሰው ሁሉንም አይነት የብጉር ጠባሳዎች ሊይዝ ይችላል።
የብጉር ጠባሳው ደረጃ አነስተኛ ከሆነ ማለትም ወደውስጥ ያልገባ ከሆነ እንዲሁም ከ 50 cm የአይን እይታ እና በታች ብቻ መለየት የሚቻል ከሆነ፣ በሚቀቡ የቆዳ መገሽለጫዎች የመጥፋት እድል አለው።
ለብጉር ጠባሳ የሚሰጡ የህክምና አይነቶች።
በ ኬሚካል እና በመሳሪያ ቆዳን መገሽለጥ
(Chemical peel and Microdermabresion)
የጨረር ህክምና (laser therapy)
ስብ ህዋስ የመውጋት ህክምና (Fat transplant)
የራስን ደም አጥልሎ የመውጋት ህክምና (PRP)
በቀጫጭን መርፌ የመብጣት ህክምና (Needling)
ጠባሳውን ቆርጦ ማውጣት (Punch technique)
እንዲሁም ለሚያብጥ ጠባሳ ደሞ
በቅዝቃዜ የማድረቅ ህክምና (Cryotherapy)
ጠባሳ ላይ በሚወጋ (IST)
ቆዳ ላይ በሚደረግ ቀዶህክምና አማራጮች አሉት።(Dr Seife Worku)
9.7K views14:57