2022-11-09 09:47:30
ሰዎች ራሳቸውን ለምን ያጠፋሉ?
አንዳንድ ግለሰቦች ራስን ማጥፋት የሰይጣን ግፊት ፣የሞራል ግድፈት እና ጥጋብ ይመስላቸዋል::
ነገር ግን ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው ከከሸፈባቸው ሰዎች መካከል ለድርጊታቸው እንደዋና ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የጀርባ ታሪካቸው ሲጠና የአዕምሮ ህመም እንደነበረባቸው ጥናቶች ያሳያሉ::
ራሳቸውን ለማጥፋት ተጋላጭ የሆኑ እነማን ናቸው?
ራሳቸውን ለማጥፋት ከሚሞክሩ ግለሰቦች መካከል 95% የሚሆኑት ቢያንስ አንድ የአዕምሮ ህመም ሊኖርባቸው ይችላል::ከዚህ ዉስጥም 80% የሚሆነው ድብርት በሽታ(Major Depressive Disorder)ይሸፍናል::
-ጭንቀት
-ቋሚ የሆነ አካላዊ ህመም(የስኳር፣ የነርቭ ፣ የካንሰር ህመም )
-ብቻቸውን የሚኖሩ ፣ከሌሎች ሰዎች ድጋፍ የማያገኙ ፣ያላገቡ
-ከቤተሰብ አባል ዉስጥ ከዚህ በፊት ራሱን ያጠፋ ሰው ካለ
-ከዚ በፊት ራስን ለማጥፋት ሙከራ ያደረገ
-መጥፎ የህይወት ጠባሳ ያሳለፈ ( መደፈር ፣ጉልበት ብዝበዛ)
-እስረኞች
ራሱን ለማጥፋት ያሰበ ሰው እንዴት ልናውቅ እንችላለን?
እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት ነገሮች ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ሊጠቀማቸው የሚችሉት ነገሮች ስለሚሆን ቤተሰብ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል:-
-ከፍተኛ የሆነ ተስፋ የመቁረት ስሜት እንዳላቸው አዘውትረው መናገር ፤
-ህይወት አሰልቺ እና አድካሚ እንደሆነች መናገር ፤
-ለቤተሰብ ሸክም እንደሆኑ መሰማት፤
-ወደአልጋ ሲሄዱ ምነው ተኝቼ በቀረሁ ማለት፣
-ምነው ፈጣሪ ህይወቴን በወሰዳት የሚል ቃል መናገር፣
እንዴት መከላከል ይቻላል?
አንድ ሰው ራሱን ለማጥፋት ከሞከረ ወይንም ከላይ የተገለፁትን ሁኔታዎች ካሳየ የስነልቦና ባለሙያ ጋር በመውሰድ የድርጊቱን መንስኤ ምን እንደሆነ ምርመራ ቢደረግለት መልካም ነዉ።
1.9K views06:47