Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_haileleul_mekonnen — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_haileleul_mekonnen — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የሰርጥ አድራሻ: @dr_haileleul_mekonnen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.35K
የሰርጥ መግለጫ

📞 0974013612 በመደወል አስፈላጊዉን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ።
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን ተጭናችሁ 👉
@drhaileleulmd
ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-01 20:20:47
ንዴት የሚያስከትለውን የጤና ችግር ያውቃሉ?

ለድንገተኛ የልብ ሕመም ያጋልጣል

በቶሎ የሚበሳጩ እና የሚናደዱ ከሆነ ራስዎን ለድንገተኛ የልብ ሕመም እያጋለጡ እንደሆነ ሊያውቁ ይገባል፡፡

አሉታዊ ስሜታዊነት ሰውነትዎን ለሕመም ያጋልጣሉ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከ85% በላይ የሚሆኑ የበሽታ ዓይነቶች ከሚኖረን ስሜት ጋር ተያያዥነት አላቸው፡፡

ንዴት በውስጥዎ ማመቅ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ተጋላጭነትዎን በ3 ዕጥፍ ይጨምራል

በሚናደዱ ጊዜ ንዴትዎን ለማብረድና መፍትሔ ለመፈለግ ራስዎን የሚዝናና እና ንዴትዎን ሊቀንስ ሰለሚችል ነገርን ያድርጉ፡፡ ይህን የማያደርጉ ከሆነ እራስዎን ለልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣሉ፡፡

የሰውነትዎን በሽታ የመከላከል አቅም ይቀንሳል

ንዴት በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኙ በሽታ ተከላካይ የሆኑ ሴሎች እንዲዳከሙ እና በቀላሉ በበሽታ እንዲጠቁ መንገድ ይክፍታል፡፡

ንዴት ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እና ሌሎችንም ስለሚያስከትል ቢቻል ባይናደዱ አልያም በዕለት ተዕለት የኑሮ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ እክሎችን በተረጋጋ መንፈስና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱና ጤንነትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ስል አመክራለሁ፡፡

ጤና ይስጥልኝ
725 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 10:25:06
"የጥርስ ሳሙናን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣልና አልጠቀምም!"

ይህ የበርካታ ታካሚዎች ፍላጎት ሲሆን ዳሩ ግን ቀድሞ የነበረንን ጠረን ስለሚያጠፋ እንጂ ለአዲስ መጥፎ የአፍ ጠረን አይዳርገንም።

ብዙን ጊዜ የአፋችንን ንፅህና ከመጠበቅ በምንሰንፍበት ጊዜ ልማም እና ሻሃላ(Plaque & calculus) የመከማቸት ዕድልን ስለሚያሰፋ ይህ ክምችት ድድ እና የመንጋጋ አጥንትን ከመብላት  እና የድድ እና የመንጋጋ አጥንት ኢንፌክሽን ከማምጣትም ባለፈ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ይዳርጋል።

በተለምዶ ሽቶ ስንጠቀም ከሰዓታት በኋላ ለሽቶው ጠረን አፍንጫችን ለማዳ ይሆንና ልዩነቱ ብዙም አይታወቀንም ለሌላ ሰው ግን የሽቶው መዓዛ እንደ አዲስ የሚሸት ሲሆን መጥፎ የአፍ ጠረንም እንደዛው የአፍ ንፅህናችን ሳንጠብቅ ስንቀር አፍንጫችን ይለምደውና መጥፎ የአፍ ጠረን ያለንም አይመስለንም።

ነገር ግን የጥርስ ሳሙና ከይዘቶቹ መካከል ጥሩ መዓዛ ሰጪ ይዘት(Flavoring Agent) አንዱ ሲሆን ጥርሳችንን በምንቦርሽበት ወቅት አፋችን ጥሩ ጠረን ይኖረውና ለቀናት በጥርስ ሳሙና መቦረሽ ስናቋርጥ እንደ አዲስ ለሚመጣው መጥፎ የአፍ ጠረን አፍንጫችን መልመድ ስለሚጀምር ጠረኑ የመጣው ባለመቦረሻችን ሳይሆን በጥርስ ሳሙናው ይመስለናል እንጂ የጥርስ ሳሙና መጥፎ የአፍ ጠረን ያጥፋ እንጂ አያባብስም።

በመጨረሻም የአፋችንን ንፅህና የጥርስ ሳሙናና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ተጠቅመን ጠዋት ከቁርስ በኋላ እና ማታ ከመኝታ በፊት መቦረሽ ይመከራል።

ታሞ ከማማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነውና ነገሩ በየ ስድስት ወሩ ማለትም በዓመት ሁለት ጊዜ በሐኪም መታየት ይመከራል።
853 viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 11:50:35 በግል ለማግኘት ወይም ቀርባችሁ ህክምና ማድረግ የምትፈልጉ፣ በዚህ አድራሻ ቀጠሮ ማስያዝ ትችላላችሁ።




@DrHaileleulMD

0974013612
656 views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 18:04:55
ቲማቲምን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

• ቲማቲምን መመገብ ለቆዳ ጥራት ጠቃሚ ነው፡፡
ቲማቲም በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር ለቆዳ ተስማሚ የሆነ ሲሆን ቲማቲምን ልጦ የልጣጩን ውስጠኛ ክፍል በፊትዎ ላይ በመለጠፍ ለ10 ደቂቃ በማቆየት መታጠብ ንፁህና የሚያበራ ፊት እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡

• ቲማቲም የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ሊኮፒን የተባለ ንጥረ ነገር በፕሮስቴት ካንሰር፣የጨጓራ እና የአንጀት ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው፡፡

• ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል
ቲማቲም በውስጡ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬን የያዘ ሲሆን ሁለቱም ንጥረ ነገሮች አጥንትአጥንት እንዲጠነክር ያደርጋሉ።

• ቲማቲም ለልባችን ጠቀሜታም አለው
ቲማቲም በቫይታሚን ቢ እና በፖታሺየም የበለፀገ ሲሆን ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን የመቀነስ አቅምም አለው፡፡ ቲማቲምን በዕለት ተዕለት የምግብ ስርአትዎ ውስጥ ማስገባት ከድንገተኛ የልብ ሕመም እና ኮሌስትሮል እራስዎን ይከላከላሉ፡፡

• ለፀጉርዎ ጠቀሜታ አለው
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ፀጉርዎን ጠንካራና ያማረ እንዲሆን ያደርጋል።

• ቲማቲም ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይቀንሳል

• ለዓይንዎ ጥራት
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ለዓይንዎ ጥራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ
830 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 21:39:50
ህክምና እና ጤና ሳይንስ መማር ለምትፈልጉ
239 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 08:17:23
የአለርጂ ሳይነስ ህመምን ለማስታገስ የሚረዱ ስድስት ነጥቦች

1. በቂ እረፍት ማድረግ፡
እረፍት መውሰድ ሰውነቶ ህመም የመከላከል አቅሙን እንዲጨምርና በፍጥነት እንድናገግም ይረዳል።

2. ፈሳሽ በብዛት መውሰድ፡
ፈሳሽ በብዛት በምንወስድ ጊዜ በሰውነታችን የሚመነጩ እና ሣይነሶቻችንን የሚደፍኑ ወፍራም ፈሳሾች እንዲቀጥኑ ያደርጋል። አልኮልና ካፊን የበዛባቸው መጠጦች ማስወገድ ይኖርብናል። አልኮል መጠጣት በሳይነሶቻችን አካባቢ እብጠት እንዲኖር በማድረግ ህመሙን ያባብሳል።

3. የሞቀ ውሀ ውስጥ የተነከረ ፎጣ በአፍንጫዎ አካባቢ እና በላይኛው ጉንጮቾ ላይ በማድረግ በፊቶ አካባቢ የሚሰማዎትን ህመም ያስታግሱ።

4. አፍንጫዎን በሚገባ ያፅዱ፡
አፍንጫዎን በንፁህ እና ሞቆ በቀዘቀዘ ውሀ በድንብ አድርገው ያፅዱ።

5. በሞቀ ውሃ ይታጠኑ፡
በፎጣ ተሸፍነው የሞቀን ውሃ መታጠን ህመሞን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

6. ከጭንቅላትዎ ቀና ብለው ይተኙ፡
ይህም በሳይነሶቻችን ውስጥ የሚገኙ ፈሳሾች በቀላሉ እንዲወገዱ እና መታፈን እንዳይኖር ያደርጋል።

ጤና ይስጥልኝ
1.2K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 16:44:28
የ12ኛ ክፍል ዉጤት ላልመጣላችሁ!!

ሼር በማድረግ መልዕክቱ እንዲደርሳቸዉ አድርጉ
1.7K viewsedited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 10:37:52
ድብርት ህመም ሀጥያት ወይስ በሽታ?
2.4K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 10:34:08
ረጅምና ጤናማ እድሜ ለመኖር የሚጠቅሙ የምግብ አይነቶች በጥቂቱ:

*አትክልትና ፍራፍሬዎች

በውስጣቸው የሚይዙት የካሎሪ መጠን አነስተኛ ስለሆነና በፋይበርና የተለያዩ ንጥረነገሮች የተሞሉ ስለሆኑ ለጤና ተመራጭ ናቸው።

*ጨው በአነስተኛ መጠን መመገብ

የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አነስተኛ የጨው መጠንን መመገብ ለደም ግፊት ያለንን ተጋላጨነት ይቀንሳል። ይህም በተዘዋዋሪ የአንጎል ሴሎች እንዳይጎዱ በማድረግ ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ ያግዛል።

*በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦች

የአጥንት መሳሳት ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ቢሆንም በተቻለ መጠን ጉዳቱን ለመከላከል በከልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ጠቀሜታ አለው።

*ቡና

በአብዛኛው የተደረጉ ጥናቶች ስንመለከት ቡና ያልተጠበቁ የጤና ጥቅሞች አሉት። ለስኳር ህመም ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ቡናን ሳይበዛ መጠጣት ከእድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ ያደርጋል።

*ቲማቲም

ቲማቲም በፋይበር እና በቫይታሚኖች የበለፀጉ ስለሆነ እና ካንሰርን የመከላከል አቅም ስላለው ለጤናማ እና ረጅም እድሜ ተመራጭ ያደርገዋል።

*ሶያ

ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምንጭ የሆነው ሶያ ስጋን እና ሌሎች የፕሮቲን ምንጮችን የሚተካ በተፈጥሮ አትክልት የሆነ ምግብም ነው።

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ
2.2K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 08:37:36
የቆዳ ጤንነት

1. የፊት ቆዳችንን ጤና ለመጠበቅ አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ቆዳችንን ከሃይለኛ ጸሀይ መከላከል ነው፡፡
በብዘት ለጸሀይ የተጋለጠ ቆዳ የመሸብሸብ እና ለሌሎች የቆዳ ችግሮች የተጋለጠ ይሆናል ፤ ስለዚህም ከጸሃይ የመከላከያ ቅባቶችን ፣ ዣንጥላ እና ለጸሃይ የማያጋልጡ አይነት አለባበሶችን በመልበስ መከላከል ይቻላል፡፡

2. በምግባችን ውስጥ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ለቆዳ ጤንነት ወሳኝ ነው፡፡

3. ቆዳችን እንክብካቤ ይፈልጋል
የምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ፣ ቅባቶች እና የጺም መላጫ ቁሳቁሶችን ለቆዳችን ተስማሚ መሆናቸውን በሚገባ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

4. ሲጋራ ማጤስ እንደሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ሁሉ ቆዳችንንም ይጎዳል፡፡ ሲጋራ ማጤስ ቆዳን እንዲሸበሸብ በማድረግ ያለ እድሚችን ያረጀ ገጽታን ሊያላብሰን ስለሚችል ማስወገድ ይኖርብናል፡፡

5. ከልክ ያለፈ ጭንቀት እና ውጥረት በቆዳችን ላይ ለሚወጡ እንደ ብጉር ላሉ እና ለሌሎች የቆዳ በሽታዎች ስለሚያጋልጡን አእምሯችንን ዘና ማድረግ አለብን፡፡

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ
2.7K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ