ረጅምና ጤናማ እድሜ ለመኖር የሚጠቅሙ የምግብ አይነቶች በጥቂቱ:
*አትክልትና ፍራፍሬዎች
በውስጣቸው የሚይዙት የካሎሪ መጠን አነስተኛ ስለሆነና በፋይበርና የተለያዩ ንጥረነገሮች የተሞሉ ስለሆኑ ለጤና ተመራጭ ናቸው።
*ጨው በአነስተኛ መጠን መመገብ
የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አነስተኛ የጨው መጠንን መመገብ ለደም ግፊት ያለንን ተጋላጨነት ይቀንሳል። ይህም በተዘዋዋሪ የአንጎል ሴሎች እንዳይጎዱ በማድረግ ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ ያግዛል።
*በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦች
የአጥንት መሳሳት ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ቢሆንም በተቻለ መጠን ጉዳቱን ለመከላከል በከልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ጠቀሜታ አለው።
*ቡና
በአብዛኛው የተደረጉ ጥናቶች ስንመለከት ቡና ያልተጠበቁ የጤና ጥቅሞች አሉት። ለስኳር ህመም ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ቡናን ሳይበዛ መጠጣት ከእድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ ያደርጋል።
*ቲማቲም
ቲማቲም በፋይበር እና በቫይታሚኖች የበለፀጉ ስለሆነ እና ካንሰርን የመከላከል አቅም ስላለው ለጤናማ እና ረጅም እድሜ ተመራጭ ያደርገዋል።
*ሶያ
ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምንጭ የሆነው ሶያ ስጋን እና ሌሎች የፕሮቲን ምንጮችን የሚተካ በተፈጥሮ አትክልት የሆነ ምግብም ነው።
እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!
ጤና ይስጥልኝ