Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_haileleul_mekonnen — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_haileleul_mekonnen — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የሰርጥ አድራሻ: @dr_haileleul_mekonnen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.35K
የሰርጥ መግለጫ

📞 0974013612 በመደወል አስፈላጊዉን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ።
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን ተጭናችሁ 👉
@drhaileleulmd
ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-10-31 07:48:17
የማር ጥቅሞች

1. ንጹህ ማር በቫይታሚን እና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ሲሆን እነዚህ ቫይታሚኖች እና ንጥረ ነገሮችም ሰውነታችንን ከባክቴሪያዎች ይከላከላሉ፡፡

• ማር የሰውነታችንን የበሽታ መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡
• ጉንፋን ሲይዘን እና የሚያስለን ከሆነ አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር በትኩስ ውሃ ውስጥ መበጨመር አንዲሁም የተወሰነ ሎሚ እና ቀረፋ በማድረግ መጠቀም ይቻላል፡፡

2. ማርን በትኩስ ውሀ ውስጥ ከሎሚ ጋር በመጨመር ጠዋት ምግብ ከመውሰዳችን በፊት ከወሰድን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ቆሻሻን እና ቅባትን ያስወግዳል፤ የሰውነት ክብደትንም እንድንቀንስ ይረዳል፡፡

3. ማርን ከቀረፋ ጋር በመደባለቅ የምንወስድ ከሆነ የሰውነታችንን የኮሌስትሮል መጠን በ10 በመቶ መቀነስ እንችላለን

• አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ ጋር በትኩስ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡

4. በሀይል ሰጪነቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ማር ከቡና ባልተናነሰ ሰውነታችን ያነቃቃል፡፡

5. ማር ለቆዳችን ልስላሴ እና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

• በተጎዳው ቆዳ ላይ በመቀባት አንድ ሌሊት ማሳደር እና ጠዋት ጠዋት በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡ ይህንን በተደጋጋሚ የምናደርግ ከሆነ ለስላሳ እና ንጹህ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

6. የምግብ አለመፈጨትን ይቀንሳል ፡፡

አንድ ወይም ሁለት የሾርባ ማንኪያ ማር ከበድ ያሉ ምግቦችን ከመመገባችን በፊት ብንወስድ አሊያም ምግብ ተመግበን የመክበድ ስሜት ከተሰማን በኋላ መውሰድ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡

እባክዎ ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይሰጥልኝ!

የዶክተርን ትክክለኛ የዩትዩብ ገፅ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።



1.4K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 11:25:19
የጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች

• ከጥጋብ በላይ አለመመገብ

• ምግብን በዝግታ መመገብ

• ቅባታማ ምግቦችን ማስወገድ

• ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ

• ሲጋራ ያለማጤስ

• ቡና፤አልኮል እና የለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር

• የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

• አዕምሮዎን ዘና በማድረግ ጭንቀትን ማስወገድ

ጤና ይስጥልኝ

የዶክተርን ትክክለኛ የዩትዩብ ገፅ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።



1.8K viewsedited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 08:27:48
የድካም ስሜት የሚሰማዎ ለምን እንደሆነ ያውቀሉ?

• አካል ብቃት እንቅስቃሴ አያደርጉም

• በቂ ውሃን አይጠጡም

• አይረን የሚባል ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች አያዘወትሩም

• ቁርስዎን አይመገቡም

• ለጤና ተስማሚ ከሆኑ ምግቦች ይልቅ ጣፋጭ እና ቅባታማ ምግቦችን ይመገባሉ

• የሥራ ቦታዎ የተዘበራረቀ እና ያልተስተካከለ ከሆነ

• በሥራ ምክንያት ሰለሚያመሹ በቂ እንቅልፍ አለማግኝትዎ ፡፡

እባክዎ ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይሰጥልኝ!

የዶክተርን ትክክለኛ የዩትዩብ ገፅ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

https://youtube.com/c/HaileleulMekonnen
2.2K viewsedited  05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 09:44:55
ቀረፋን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

1. በአንቲ ኦክሲደንት የበለፀገ ነው

ቀረፋ በውስጡ ያዘው አንቲ ኦክሲደንት መጠን ቶሎ የማርጀትን ሁኔታ አንደሚያዘገይ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

2. ለልብን ጤናማነት

ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ቀረፋ ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሆኑታዎችን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮሌስትሮል መጠን እንዳይጨምርም የመከላከል አቅም አለው፡፡

3. ስኳር ሕመም

ቀረፋ የስኳር ሕመምን የመከላከል አቅም ስለአለው በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

4. ካንሰርን ይከላከላል

አንቲ ኦክሲደንትን በውስጡ ያዘው ቀረፋ ለካንሰር ተጋላጭነታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡

5. ኢንፌክሽንን ይከላከላል

የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም የነበረ እንዲሆን ይረዳናል፡፡

6. ለጥርስ ጤናማነት እና ጥሩ የአፍ ጠረን

መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖረን እና በአፍ ውስጥ የሚገኙ ሕመሞችን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚናን ይጫወታል፡፡

እባክዎ ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይሰጥልኝ!

የዶክተርን ትክክለኛ የዩትዩብ ገፅ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

https://youtube.com/c/HaileleulMekonnen
2.4K viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 17:05:04
የኩከምበር የጤና ጥቅሞችን ያውቃሉ?

1. የመገጣጠሚያ ህመም ስሜትን ያስታግሳል

2. የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል

3. ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

4. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያግዛል

5. የእራስምታት ህመምን ይከላከላል

6. ካንሰርን የመዋጋት አቅም አለው

7. ለፀጉሮ ወዝን ይሰጣል

8. ለደም ግፊትና ለስኳር ህመምተኞች ጠቃሚ ነው።

ጤና ይስጥልኝ

የዶክተርን ትክክለኛ የዩትዩብ ገፅ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

https://youtube.com/c/HaileleulMekonnen
2.6K views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:08:43
ለአንጎል ጎጂ የሆኑ ልማዶች/ Brain Damaging Habits

1. ቁርስ አለመመገብ

ቁርስ የማይመገቡ ከሆነ በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለአንጎል የሚደርሰውን የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።

2. በህመም ወቅት በቂ እረፍት አለማድረግ

ሰውነታችን በህመም ሲጠቃ በቂ እረፍት ማድረግ እና ከህመሙ ማገገም በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዳይኖር ይረዳል።

3. ሲጋራ ማጤስ

ሲጋራ ማጤስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የልብ ህመም፣ የሳምባ ካንሰር እና ስትሮክን ከማስከተል ባለፈ በአንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

4. ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች ማዘውተር ለአንጎል ጉዳት መንስኤ ናቸው።

5. የአየር ብክለት

አንጎል ከየትኛውም የሰውነት ክፍሎቻችን በበለጠ ኦክስጂን ያስፈልገዋል። የምንተነፍሰው አየር የተበከለ ከሆነና ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ ጉዳት ያስከትላል።

6. የእንቅልፍ እጦት

እንቅልፍ አንጎልን እረፍት እንዲያገኝ የምናደርግበት ሂደት ስለሆነ በቂ እንቅልፍ አለመውሰድ ለጉዳት ይዳርጋል።
ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡

7. የአልኮል መጠጥ ማብዛት

በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስ በቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

8. የምግብ አይነቶችን መምረጥ

ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ለአንጎል ጤናማነት ወሳኝ ነው።

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ

ጤና ይስጥልኝ

በቪድዮ የተደገፉ መረጃዎችን ለማየት ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ ።

https://youtube.com/c/HaileleulMekonnen
2.9K viewsedited  04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 14:07:18
ሪህ/ Gout Arthritis

የሪህ ሕመም የሚከሰተዉ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል የሚገኘው ፕሮቲንን በዉስጣቸዉ ከያዙ ምግቦች ነው፡፡ የሪህ ችግር አንድ ጊዜ ከጀመረ በኋላ የመከላከያ ዕርምጃዎችን ካልወሰድን የመመላለስ ባህርይም አለዉ፡፡

የአጥንት መገጣጠሚያዎች በተለይም በእግራችን የአውራ ጣት፣ በቁርጭምጭሚት፣በጉልበት፣በእጃችን የክንድ እና የእጅ መገጣጠሚያዎች ላይ ተከማችቶ ይገኛል፡፡

የሪህ ህመም ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታዎች

• ዉስጣዊ የሆኑ ህመሞች
• አልኮል መጠጦችን ማዘዉተር
• ፕሮቲን የበዛባቸው የምግብ ዓይነቶችን መመገብ (ስጋ፣ሽሮ የመሳሰሉት)
• የሰዉነት ቁስለት
• ድካም
• ጭንቀት
• በሃኪም የታዘዘን የሪህ መድኃኒት ማቆም ናቸዉ፡፡

የሪህ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸዉ፡፡

• ከአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆኑ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚኖር ኃይለኛ የሕመም ስሜት፡፡
• የመገጣጠሚዎች ማበጥ፣ መቅላት እና የሙቀት መጠን መጨመር
• ትኩሳት መኖር
• ብርድ ብርድ ማለት ናቸዉ

ሪህ ተደጋግሞ እንዳይመጣ ምን ማድረግ ይገባል

• ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች በተለይም ቀይ የበሬ ሥጋ፣አሳ፣እንቁላል፣የመሳሰሉት ምግቦች መቀነስ ወይንም ለጊዜው ማስወገድ፣
• ውሃ በብዛት መውሰድ፣
• የአልኮል መጠጦችን አለመጠጣት፣
ከላይ የተጠቀሱት የሕመም ስሜቶች ሲሰማዎትም ሐኪምዎን ማማከር የኖርቦታል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

በቪድዮ የተደገፉ መረጃዎችን ለማየት ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ ።

https://youtube.com/c/HaileleulMekonnen
3.1K viewsedited  11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 21:56:09 በግል ለማግኘት ወይም ቀርባችሁ ህክምና ማድረግ የምትፈልጉ፣ በዚህ አድራሻ ቀጠሮ ማስያዝ ትችላላችሁ።



@DrHaileleulMD

0974013612
1.4K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 16:44:07
የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ

1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣

የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ

• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል

• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት

ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

2. በቂ እረፍት ማድረግ

መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ

ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ

በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል

እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ

መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ

ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ

ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ

(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።

ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ

ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ

የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ

ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ

ራስዎን ዘና ያድርጉ
1.9K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 10:27:06
1.5K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ