2023-01-24 13:35:10
ጥቅል ጎመንን የመመገብ የጤና ጥቅሞች
1, ካንሰርን ይከላከላል
ጥቅል ጎመን በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች ሉፔኣኦል፣ ሲንግሪን እና ሰልፎራፌን የካንሰርን እድገት መከላከል አቅም እንዲኖረው እንዳደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።
2, የሰውነት መቆጣት እንዳይኖር ይከላከላል
ይህም አለርጂ፣ የመገጣጠሚያ ህመም፣ትኩሳት እና ሌሎች የቆዳ ችግሮች እንዳይከሰቱ ይረዳል።
3, እይታን ያሻሽላል
ጥቅል ጎመን ቤታ ካሮቲንን በውስጡ ስለያዘ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣን በጥራት የማየት ችግር በተወሰነ መልኩ ይከላከላል።
4, ክብደትን ለመቀነስ
ጥቅል ጎመን በአብዛኛው ክብደት ለመቀነስ የሚሞክሩ ሰዎች እንዲመገቡት ይመከራል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በውስጡ የያዛችው ቫይታሚኖችና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የጥጋብ ስሜት እንዲሰማን ቢያደርጉም የካሎሪ መጠኑ እጅግ ያነሰ በመሆኑ ክብደት መጨመርን ይከላከላል።
5, የአንጎልን ጤና ያዳብራል
ጥቅል ጎመን በውስጡ ቫይታሚን ኬ እና አንቶኪዎኒንን ስለሚይዝ የአንጎል ስራን ማፋጠንና ትኩረት መጨመር እንዲኖር ያደርጋል።
6, ለአጥንት ጤና ጠቃሚ ነው
ጥቅል ጎመን ካልሲየም፣ ማግኒዚየምና ፖታሲየምን ስለሚይዝ ለአጥንት ጥንካሬና ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች የመከላከል ከፍተኛ ጠቃሚነት አለው።
7, ለደም ግፊት መጨመር
በውስጡ የሚጘኘው ፖታሲየም ከደም ግፊት መጨመር በመከላከል ተያያዥ ድንገተኛ የልብ ህመም እና ስትሮክ እንዳይከሰት ይከላከላል።
8, ለቆዳ ጤናማነት
ጥቅል ጎመን ለቆዳ ጠቃሚነት እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ። ቆዳችን በቶሎ እንዳያረጅ እና ጥርት ያለ ሆኖ እንዲቆይ ይረዳናል።
9, የጡንቻ ህመምን ይቀንሳል
በጥቂቱም ቢሆን የጡንቻ ህመምና መሸምቀቅ እንዲቀንስ ያደርጋል።
ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያካፍሉ።
ጤና ይስጥልኝ!
2.7K views10:35