Get Mystery Box with random crypto!

#ምግብ ያለመብላት በሽታ (በ ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን) #አኖሬክዚያ_ነርቮሳ (Anorexi | ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

#ምግብ ያለመብላት በሽታ

(በ ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

#አኖሬክዚያ_ነርቮሳ (Anorexia Nervosa)

ይህ በሽታ ከአዕምሮ በሽታዎች አንዱ ሲሆን ፤ የዚህ በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ስለሚበሉት እና ስለ መወፈር አብዝቶ የሚያሳስባቸው ሲሆን መወፈርን እጅግ አብዝተው የሚጠሉ ናቸው::

ይህ በሽታ በሴቶች ላይ ጎልቶ የሚስተዋል ሲሆን በአብዛኛው እድሜያቸው ከ 20 ዓመት በታሽ የሆኑትን ያጠቃል::

የዚህ በሽታ መለያው ምንድነው?

እራስን ለረሃብ ማጋለጥ

መወፈርን አጥብቆ መፍራት እና መጨነቅ

ውፍረትን ለመቀነስ በማሰብ ትንሽ መብላት

የበሉትን ምግብ ማስመለስ

የምግብ ሰዓትን ማሳለፍ

ከመጠን በላይ ከስተው እያሉ የራሳቸውን ሰውነት እጅግ በጣም እንደወፈረ ማሰብ

በበሽታው ምክንያት በሰውነት ላይ የሚታዩ ምልክቶች አሉ?

ለልብ በሽታ መጋለጥ
ሰውነት መድከም እና ሁሌም ብርድ ብርድ ማለት

በሴቶች የወር አበባ መዛባት እንዲሁም ለተከታታይ ጊዜያት የወር አበባ አለማየት
የሆድ ድርቀት
የእንቅልፍ ችግር
የማሰብ እና የማስታወስ ችሎታ መቀነስ
ለድብርት በሽታ መጋለጥ

ለዚህ በሽታ መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

የአመጋገብ ስርዓትን ለመቀየር ከሃኪም ጋር መማክር

የስነልቦና ህክምና

ሌሎች የጤና መረጃዎችን ለማግኘት ድረ ገፃችንን ይጎብኙ


www.doctorhaileleul.com