Get Mystery Box with random crypto!

እረ ልጄን አምጡልኝ! * ጉድ ሆንኩ #Ethiopia | ይህቺ የ2 ዓመት ጨቅላ ህፃን ሶልያና | ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

እረ ልጄን አምጡልኝ!

* ጉድ ሆንኩ

#Ethiopia | ይህቺ የ2 ዓመት ጨቅላ ህፃን ሶልያና ዳንኤል ትባላለች።

የወንድማችን #Daniel Mulu ልጅ ናት።

ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አካባቢ ቤዛዊት በቀለ የተባለችዉ ሞግዚቷ ይዛት ተሰዉራለች:: ሞግዚቷ ከተቀጠረች 20 ቀናት ሆኗታል።

ወላጆች ለሥራ ሲወጡ ልጃቸው፣ ሞግዚቷና አያቷ በቤት ውስጥ ነበሩ።

እናትና አባት እያለቀሱ ጭንቅ ላይ ናቸው!

ንፋስ ስልክ ወረዳ 9 ፖሊስ መምሪያ - መጥፋቷን አመልክተናል።

በትራንስፖርትም ሆነ በመንገድ ላይ አጠራጣሪ ነገር ከተመለከታችሁ ደውሉልን።

+251-951-090999 - ዳንኤል
+251-947-365252 - የውብዳር

ወይንም

በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ አሳውቁልን።

"ለልጄ ፀልዩልኝ " - እናት የውብዳር

"እረ ልጄን አምጡልኝ!" - አባት ዳንኤል

እግዚአብሔር ይስጥልን!