Get Mystery Box with random crypto!

'የጥርስ ሳሙናን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣልና አልጠቀምም!' ይህ የበርካታ ታካሚዎች ፍላጎ | ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

"የጥርስ ሳሙናን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣልና አልጠቀምም!"

ይህ የበርካታ ታካሚዎች ፍላጎት ሲሆን ዳሩ ግን ቀድሞ የነበረንን ጠረን ስለሚያጠፋ እንጂ ለአዲስ መጥፎ የአፍ ጠረን አይዳርገንም።

ብዙን ጊዜ የአፋችንን ንፅህና ከመጠበቅ በምንሰንፍበት ጊዜ ልማም እና ሻሃላ(Plaque & calculus) የመከማቸት ዕድልን ስለሚያሰፋ ይህ ክምችት ድድ እና የመንጋጋ አጥንትን ከመብላት እና የድድ እና የመንጋጋ አጥንት ኢንፌክሽን ከማምጣትም ባለፈ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ይዳርጋል።

በተለምዶ ሽቶ ስንጠቀም ከሰዓታት በኋላ ለሽቶው ጠረን አፍንጫችን ለማዳ ይሆንና ልዩነቱ ብዙም አይታወቀንም ለሌላ ሰው ግን የሽቶው መዓዛ እንደ አዲስ የሚሸት ሲሆን መጥፎ የአፍ ጠረንም እንደዛው የአፍ ንፅህናችን ሳንጠብቅ ስንቀር አፍንጫችን ይለምደውና መጥፎ የአፍ ጠረን ያለንም አይመስለንም።

ነገር ግን የጥርስ ሳሙና ከይዘቶቹ መካከል ጥሩ መዓዛ ሰጪ ይዘት(Flavoring Agent) አንዱ ሲሆን ጥርሳችንን በምንቦርሽበት ወቅት አፋችን ጥሩ ጠረን ይኖረውና ለቀናት በጥርስ ሳሙና መቦረሽ ስናቋርጥ እንደ አዲስ ለሚመጣው መጥፎ የአፍ ጠረን አፍንጫችን መልመድ ስለሚጀምር ጠረኑ የመጣው ባለመቦረሻችን ሳይሆን በጥርስ ሳሙናው ይመስለናል እንጂ የጥርስ ሳሙና መጥፎ የአፍ ጠረን ያጥፋ እንጂ አያባብስም።

በመጨረሻም የአፋችንን ንፅህና የጥርስ ሳሙናና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ተጠቅመን ጠዋት ከቁርስ በኋላ እና ማታ ከመኝታ በፊት መቦረሽ ይመከራል።

ታሞ ከማማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነውና ነገሩ በየ ስድስት ወሩ ማለትም በዓመት ሁለት ጊዜ በሐኪም መታየት ይመከራል።

ቸር ያሰማን

በዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ: Dental Surgeon