Get Mystery Box with random crypto!

ለጤና ባለሙያዉ እንድረስለት ከታች የምትመለከቱት ወንድማችን ተሾመ አበራ ይባላል። ተወልዶ ያ | ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

ለጤና ባለሙያዉ እንድረስለት

ከታች የምትመለከቱት ወንድማችን ተሾመ አበራ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በደምቢ ዶሎ ከተማ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን  እዛው በማጠናቀቅ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመሄድ በህብረተሰብ ጤና ት/ት ክፍል በጥሩ ዉጤት ተመርቆ ህብረተሰቡን እያገለገለ ለተወሰነ ጊዜ ቢቆይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት እንደቀድሞዉ መስራት አልቻለም።

በአካባቢው ባለ ሆስፒታል ቢታከምም ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እና ወደ አማኑኤል ሆስታፒል ሪፈር ቢፃፍለትም ወላጅ እናቱ ብቻቸውን በመሆናቸው እሱን ለማሳከም ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል ።

አቅማችንሁ በፈቀደ መጠን በእናቱ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት እጃችሁን እንድትዘረጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።

# 1000527420265(CBE-አያሉ)

ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ::

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ