Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @breakingnewsethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.92K
የሰርጥ መግለጫ

Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources.
Facebook page link https://m.facebook.com/BreakingNewsEthiopia/?ref=bookmarks

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-27 20:13:48
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ !!

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።

የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።

አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፤

ነሃሴ 21 ቀን 2014 ዓም አዲስ አበባ

@BreakingNewsEthiopiaa
1.7K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:11:07 አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ የሚደረጉ በረራዎችን አገደች

የበረራ እገዳው ለአንድ ወር ገደማ ይቆያል ተብሏል
አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ የሚደረጉ በረራዎችን ላይ እገዳ መጣሏ ተሰምቷል።

ከዚህ በፊት በንግድ አሁን ደግሞ በታይዋን ጉዳይ መካረር ውስጥ የገቡት አሜሪካ እና ቻይና ሌላ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።
ቻይና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብሯን አቋረጠች

ቻይና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተወሰኑ የአሜሪካ አየር መንገዶች ላይ የጉዞ እገዳዎች አስተላልፋ ነበር። አሜሪካም ለዚህ እገዳ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች ሲሆን 26 በረራዎች ከቻይና ወደ አሜሪካ እንዳይደረጉ እገዳ ጥላለች።
እገዳ ከተጣለባቸው አየር መንገዶች መካከልም ሺያሜን፣ ኤየር ቻይና፣ ሳውዘርን ቻይና እና ቻይና ኢስተርን ዋነኞቹ ናቸው ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

እንደ አሜሪካ ትራንስፖርት ዲፓርትመንት መግለጫ ከሆነ በቻይን ላይ የተጣለው የበረራ እገዳ ከፈረንጆቹ መስከረም አምስት እስከ 28 ባሉት 23 ቀናት ነው።
ሰባቱ በረራዎች ከቻይና ወደ ኒዮርክ፣ 19ኙ በረራዎች ደግሞ ወደ ሎስ አንጀለስ ሊደረጉ ታስበው እንደነበርም ተጠቅሷል።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@BreakingNewsEthiopiaa
2.0K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:27:03 #Repost

የጠላቻ ወሬ ሰሞኑን እየተንሰራፋ ነው

ብዙ የጥላቻ ወሬ እየተስተራፋ ሰሞኑን ይገኛል ለጥቅማቸው ህዝብ ከህዝብ  እያጣሉ የሚገኙ ሰዎች አሁንም በተለይ በ Facebook ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ።

ከዚህ እንጠንቀቅ ማንን ገለን ከማን ጋር ልንሮር ነው ?
ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ነን ጠላት አንድነታችንን በታትኖ ለማጥቃት ቀን ከለሊት እየሰራ ይገኛል።

እኛ ታዲያ ምን ማረግ አለብን?

ይህን የጠላት ወሬ ሳንሰማ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳቸ ሳንደናገጥ ሳንረበሽ እውነታውን ማጣራት ለሌሎች ማሰማት ይገባናል።

በቻልነው ነገር ሁሉ ስለሀገራችን እውነታ መስበክ
አንድነታችንን ማሳየት አለብን።

በአሁን ሰአት በተለይ በ  Facebook ግጭቶች እንዲነሱ የሚያረጉ ንግግሮች መልዕክቶች ስናይ Report ማድረግ እና Share Like አለማድረግ።

በዘር እና በሀይማኖት ማንም አይከፋፍለንም

#አንድነን
#ለተቸገሩት_እንድረስ

አምላክችን ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይጠብቅልን
2.0K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:08:28
የሲዳማ ክልል የዞን አደረጃጀት ፀደቀ።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የዞን አስተዳደር እና አደረጃጀትን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ተቀብሎ ክልሉ በ4 ዞኖች እና በ1 ከተማ አስተዳደር እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል።

የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ነው።

የዞኖቹ ስያሜዎች ሰሜን ሲዳማ ዞን፣ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን፣ ደቡብ ሲዳማ ዞን እና ምስራቅ ሲዳማ ዞን በሚል እንደሚጠራ ተገልጿል።

@BreakingNewsEthiopiaa
1.9K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:42:02
ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ!

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ነሐሤ 21/2014 በተለያዮ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያሰመረቀ ሲሆን በዕለቱም ሲጠበቅ በነበረው ፕሮግራም ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ  እና  ለአትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት አበርክቷል::

ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር እየኖሩ ያሉ አርአያ ሰብ በመሆናቸው እንዲሁም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በስፖርቱ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት በመሆን እና ለህብረተሰብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት እየተጋች ያለች ተምሳሌት በመሆኗ ነው ብሏል ዮኒቨርሲቲው::

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ ሶስተኛ ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ እንዲሁም በማሪታይም ሙያ ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው በዛሬው ዕለት ያስመረቀው።

[Reporter]
@BreakingNewsEthiopiaa
1.9K views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 01:42:47 " ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች " - ዶ/ር ሁሴን አደም

የህወሓት ኃይሎች በአፋር ያሎ በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል።

ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸውም ውስጥ ወደ ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል መጥተው ህክምና የተከታተሉ እንዳሉ የሆስፒታሉ ስራ አኪያጅ ዶ/ር ሁሴን አደም ተናግረዋል።

ዶ/ር ሁሴን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፥ " ጦርነቱ እንደገና ተነስቶ ዜጎች እኛ ጋር አብሶ ከረጅም ርቀት በሚተኮስ ትልቅ መሳሪያ የተጎዱ ቁስለኞች መጥተዋል፤ አብዛኞቹ ቁስለኞችን ስናያቸው ሲቪሊያን (ሰላማዊ ዜጎች) ናቸው እኛ ጋር የመጡት ለጊዜው እየተደረገ ያለው እዛው አቅራቢያ ህክምና ሚያስፈልጋቸው ዜጎች ህክምና እያገኙ ነው ፤ ከዛ የባሰ ከነሱ በላይ የሆነው ወደኛ ሆስፒታል እየላኩ ይገኛሉ። ጉዳታቸው ከሰው ሰው ይለያያል እዚህ ለመድረስ እድለኛ የሆኑት ህክምና እያገኙ ነው ለጊዜው እዚህ ከመጡ በኃላ ህይወት ያለፈ አልነበረም እስካሁን ድረስ፤ መጥፎውን አላህ ይያዝልን " ብለዋል።

እስካሁን 13 የሚደርሱ በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ወደሆስፒታሉ እንደገቡ ጠቁመዋል።

ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ ተገልጿል።

ዶ/ር ሁሴን አደም፤ "አንድ እናት አለች 2 ህፃናት ልጆቿ የሞቱባት ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ትልቅ መሳሪያ ቤት ውስጥ ባሉበት ሰዓት ተመተው 2 ህፃኖቿን እዛው ነው ያጣችው እሷ ግን እኛ ጋር መጥታለች የህክምና አገልግሎት እያገኘች ትገኛለች " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

Via tikvahethiopia

@BreakingNewsEthiopiaa
2.2K viewsedited  22:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:48:27
" አሁንም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላም በጋራ ሊቆም ይገባል " - ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎችና አዴ ስንቄዎች በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የጋራ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮችና ሃይማኖቶች መገኛ መሆኗን የገለጹት የሃይማኖት መሪዎቹና አባ ገዳዎቹ ሁሉም ኢትዩጵያዊ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለአገር አንድነትና ሰላም በአንድነት እንዲቆም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

አባ ገዳዎቹ ችግሮች ሁሉ በሰላምና በስምምነት መፈታት እንደሚገባው ገልፀዋል።

አገራችን ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ያደረገችውና እያደረገች ያለችው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው አሁንም ችግሮች ሁሉ በሰላምና በሰላም ብቻ መፍትሔ እንዲያገኙ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ መቀጠሏ ተገቢ ነው ብለዋል።

ይህ የሰላም ጥረት ፍሬ ያፈራ ዘንድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚደረገውን የሰላም ጥረት በአንድነት በመቆም ዘርና ሃይማኖት ሳይለዩ ሊደግፉት ይገባል ብለዋል።

የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበኩላቸው ፤ " ባለፉት 5 ወራት መንግስት ለሰላም ያደረገው ጥረት ፍሬ አፍርቶ ለማየት በእጅጉ በጉጉት እየጠበቅን ባለንበት ጊዜ ሰላምን የሚያደፈርሱ  ተግባራት መታየታቸው አሳዝኖናል " ብለዋል።

አሁንም ችግሮች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላም በጋራ መቆም ይኖርበታል ብለዋል።

(ተጨማሪ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@BreakingNewsEthiopiaa
2.1K views20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:46:55
ሚሼል ባሽሌት ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት በሰጡት መግለጫ በሰሜን #ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ ​​እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

" ሲቪሎች በቂ ጉዳት ደርሶባቸዋል " ያሉት ባሽሌት አሁን ዳግም ግጭት መቀስቀሱ አስፈላጊ የሆነ ድጋፍ የሚሹ የሰላማዊ ዜጎችን ስቃይ የሚያባብስ ብቻ ነው ብለዋል።

ባሽሌት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) አሁን ያለውን ሁኔታ ለማርገብ እንዲሰሩና ግጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ተማፅነዋል።

@BreakingNewsEthiopiaa
2.2K views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:14:12
ተርኪዬ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ማርች 24 /2022 በፌዴራል መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ከታወጀ በኃላ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶችን በሀዘን እና ስጋት ውስጥ ሆና እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልፃለች።

ሁሉም ወገኖች ግጭት በዘላቂነት እንዲቆም ለማድረግ እና በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ወደ ንግግር እንዲመለሱ ጋብዛለች።

ለዚህ አላማ ደግሞ ሁሉንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጣለች።

ተርኪዬ በኢትዮጵያ ሰላምን እና መረጋጋትን ለማስፈን ባሚደረገውን ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፃለች።

በሌላ በኩል ፤ ዩናይትድ ኪንግደም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶች እንደሚያሳስባት ገልፃለች።

ይህ ሁኔታ ቀድሞም አስከፊ የነበረውን የሰብዓዊ ሁኔታ ይበልጥ ያባብሰዋል ብላለች።

ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ግጭት እንዲያቆሙና የፖለቲካ መፍትሄ እንዲመጣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ አሳስባለች።

@BreakingNewsEthiopiaa
2.9K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:01:06
" አሁኑኑ የተሰረቀውን ነዳጅ መልሱ " - WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ድርጅታሸድ ለእርዳታ ሥራው የሚያውለውን 570,000 ሊትር ነዳጅ " የትግራይ ባለሥልጣናት ሰርቀዋል " ብለዋል።

" ምግብ ለማድረስ ነዳጅ ከሌለን በሚሊዮኖች ይራባሉ " ያሉት ቢዝሊ ድርጊቱን " የሚያስቆጣ እና አሳፋሪ " ብለውታል።

አሁኑን የተሰረቀው ነዳጅ እንዲመለስ ጠይቀዋል።

@BreakingNewsEthiopiaa
3.0K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ