Get Mystery Box with random crypto!

' አሁንም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለ | ሰበር ዜና

" አሁንም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላም በጋራ ሊቆም ይገባል " - ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎችና አዴ ስንቄዎች በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የጋራ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮችና ሃይማኖቶች መገኛ መሆኗን የገለጹት የሃይማኖት መሪዎቹና አባ ገዳዎቹ ሁሉም ኢትዩጵያዊ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለአገር አንድነትና ሰላም በአንድነት እንዲቆም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

አባ ገዳዎቹ ችግሮች ሁሉ በሰላምና በስምምነት መፈታት እንደሚገባው ገልፀዋል።

አገራችን ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ያደረገችውና እያደረገች ያለችው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው አሁንም ችግሮች ሁሉ በሰላምና በሰላም ብቻ መፍትሔ እንዲያገኙ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ መቀጠሏ ተገቢ ነው ብለዋል።

ይህ የሰላም ጥረት ፍሬ ያፈራ ዘንድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚደረገውን የሰላም ጥረት በአንድነት በመቆም ዘርና ሃይማኖት ሳይለዩ ሊደግፉት ይገባል ብለዋል።

የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበኩላቸው ፤ " ባለፉት 5 ወራት መንግስት ለሰላም ያደረገው ጥረት ፍሬ አፍርቶ ለማየት በእጅጉ በጉጉት እየጠበቅን ባለንበት ጊዜ ሰላምን የሚያደፈርሱ  ተግባራት መታየታቸው አሳዝኖናል " ብለዋል።

አሁንም ችግሮች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱና በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላም በጋራ መቆም ይኖርበታል ብለዋል።

(ተጨማሪ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@BreakingNewsEthiopiaa