Get Mystery Box with random crypto!

' ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች ' - ዶ/ር ሁሴን | ሰበር ዜና

" ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች " - ዶ/ር ሁሴን አደም

የህወሓት ኃይሎች በአፋር ያሎ በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል።

ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸውም ውስጥ ወደ ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል መጥተው ህክምና የተከታተሉ እንዳሉ የሆስፒታሉ ስራ አኪያጅ ዶ/ር ሁሴን አደም ተናግረዋል።

ዶ/ር ሁሴን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፥ " ጦርነቱ እንደገና ተነስቶ ዜጎች እኛ ጋር አብሶ ከረጅም ርቀት በሚተኮስ ትልቅ መሳሪያ የተጎዱ ቁስለኞች መጥተዋል፤ አብዛኞቹ ቁስለኞችን ስናያቸው ሲቪሊያን (ሰላማዊ ዜጎች) ናቸው እኛ ጋር የመጡት ለጊዜው እየተደረገ ያለው እዛው አቅራቢያ ህክምና ሚያስፈልጋቸው ዜጎች ህክምና እያገኙ ነው ፤ ከዛ የባሰ ከነሱ በላይ የሆነው ወደኛ ሆስፒታል እየላኩ ይገኛሉ። ጉዳታቸው ከሰው ሰው ይለያያል እዚህ ለመድረስ እድለኛ የሆኑት ህክምና እያገኙ ነው ለጊዜው እዚህ ከመጡ በኃላ ህይወት ያለፈ አልነበረም እስካሁን ድረስ፤ መጥፎውን አላህ ይያዝልን " ብለዋል።

እስካሁን 13 የሚደርሱ በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ወደሆስፒታሉ እንደገቡ ጠቁመዋል።

ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ ተገልጿል።

ዶ/ር ሁሴን አደም፤ "አንድ እናት አለች 2 ህፃናት ልጆቿ የሞቱባት ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ትልቅ መሳሪያ ቤት ውስጥ ባሉበት ሰዓት ተመተው 2 ህፃኖቿን እዛው ነው ያጣችው እሷ ግን እኛ ጋር መጥታለች የህክምና አገልግሎት እያገኘች ትገኛለች " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

Via tikvahethiopia

@BreakingNewsEthiopiaa