Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @breakingnewsethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.92K
የሰርጥ መግለጫ

Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources.
Facebook page link https://m.facebook.com/BreakingNewsEthiopia/?ref=bookmarks

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 09:52:59
በደባርቅ ከተማ 16 ሰርጎ ገቦች ተያዙ

የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በምሽት የኬላ ጥበቃ 16 የአሸባሪው የህወሓት ቡድን አባላት የሆኑ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።**

የአሸባሪው ህወሓት ቡድን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማቀበል ሥራ የሚሠሩ 16 ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦች እና ሶስት ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ ብርሃን ፀጋየ ገልፀዋል።

የአሸባሪው ቡድን ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ የመጀመሪያው ተግባር የከተማችን ከሰርጎ ገብ መጠበቅ እና የደጀንነት ሚና መወጣት ዋነኛ እና ቁልፍ ተግባር መሆኑ ታውቆ በአደረጃጀት ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

Via:- EBC
@BreakingNewsEthiopiaa
489 views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:42:05 የሰበር ዜና መልዕክት

ውጊያው ከአሸባሪው ከሕውሓት ብቻ ሳይሆን የውጪ ሀይላት ጋርም በመሆኑ ወገኔ ንቃ።


ይህ ውጊያ ከውስጥም ከውጪ ሀይላት ጋር መሆኑን ተገንዝበን በአንድነት  በዘር በሀይማኖት ሳንከፋፈል ሰው ስለሆንን ብቻ ፤ ኢትዮጵያውያን ስለሆንን ብቻ የጠላትን ወሬ ሳንሰማ አንድ በመሆን ለሀገራችን ኢትዮጵያ በሕብረት እንቁም።


ፈጣሪ ሐገራችንን ሰላም ያድርግልን

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

#አንድነን

#Share

@BreakingNewsEthiopiaa
1.9K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:42:19
የኢትዮጵያን ትንሣኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ምድራዊ ኃይል አይኖርም - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኢትዮጵያን ትንሣኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ምድራዊ ኃይል አይኖርም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የሻዴይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓልን ልጃገረዶች፥ ወጣቶችና ሴቶች ባከበሩበት ወቅት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመውን ወረራ የሚያወግዝና ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ንቅናቄ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የከተማዋ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በንቅናቄው ላይ ታድመዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ "የዛሬውን የሻደይ፣አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ማክበራችን ዋናው ዓላማ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ክብር ለመስጠት፣ለንፁሃን ወገኖቻችን ድምፅ ልናሰማ እና የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለማውገዝ ነው"ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ሀገርን በማስቀደም፣ በሁሉም ግንባሮች በንቃት፣ በትጋትና በአንድነት መሰለፍ ግድ ይለናልም ነው ያሉት ከንቲባዋ።

ኢትዮጵያ ለሰላም የዘረጋችው እጅ ሳይታጠፍ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ያበረውን ወራሪ ኃይል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲፈጥርበትም መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ እና ለጀግባው ሠራዊቱ ያልተቆጠበ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@BreakingNewsEthiopiaa
2.0K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:41:13
ዳያስፖራው ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚያደርግባቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ይፋ ሆኑ

የገንዘብ ሚኒስቴር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሠራዊትን ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥሮችን ይፋ አደረገ፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ የኢትዮጵያ ጠላቶች በሀገራችን  እና በሰላም ወዳዱ ወገናችን ላይ ዳግም ጥቃት በማወጅ የተጠናወታቸውን ኢትዮጵያን የማዋረድ እኩይ ተግባር እንደገና መጀመራቸውን አንስቷል፡፡

ይህንን የተቃጣብንን የተቀናጀ  ጥፋትም ጀግኖቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎች ከሰላም ወዳዱ ደጀን ህዝባችን ጋር በመሆን በጽናት እና በጀግንነት እየመከቱ ይገኛሉ ነው ያለው ።

ይህ ተጋድሎ የሚደረገውም  ለሀገራችን የሚሰነብት፣ የሚከርም፣ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ ሊኖር የሚችል ዘላቂ ሰላም ለማስገኘት  ነው ሲልም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

በውጭ የሚትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም እንደተለመደው ለዚህ ትግል እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥሮችም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

ለዩሮ - 1000439142832 ፣ ለዶላር - 1000439142786   እና ለፓውንድ - 1000443606304   የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥሮች የተዘጋጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@BreakingNewsEthiopiaa
1.8K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:55:19
“ የሰላም በር ሁሌም ክፍት መሆን ይኖርበታል” - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

@BreakingNewsEthiopiaa
1.9K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:42:38
#ሰቆጣ

መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

Via tikvahethiopia

@BreakingNewsEthiopiaa
2.0K views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:19:02
የሰላም ጥሪን ሁሉም እንዲቀበል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ

የኢትዮጵያ እናቶች እና ሰላም ወዳድ ዜጎች እያቀረቡት ያለውን የሰላም ጥሪ ሁሉም እንዲቀበልና ተግባራዊ ምላሽ እንዲሰጥ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ፕሬዚዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍቅርና ሰላም የሰፈነባት እንዲሁም ለዜጎች የምትመች ሀገር እንድትሆን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ የዳያስፖራ ማህበረሰብን ጨምሮ ኢትዮጵያውን እናቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ተወካዮች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ ግለሰቦች እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

እስካሁን ለተደረገው ጥረት አመስግነው÷ ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

@BreakingNewsEthiopiaa
1.9K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:53:56 ጥያቄ ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ
@BreakingNewsEthiopiaa_bot ያነጋግሩን
1.9K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:19:47
የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠየቁ!

የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል የጀመሩትን ውጊያ አቁመው ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጠየቁ። ሚኒስትሯ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ኃይሎች ክልሉን ለቀቅው መውጣት አለባቸው ብለዋል።

ቪኪ ፎርድ ይህን ያሉት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች ዳግም ወደ ግጭት መመለሳቸውን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 26፤ 2014 ባወጡት መግለጫ ነው። ሁለቱ ኃይሎች እንደገና ወደ ግጭት መግባታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ “መከራ የሚያመጣ” ነው ያሉት የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር፤ በክስተቱ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን የማጣት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ገልጸዋል።

በሁለቱ ኃይሎች ውጊያ ምክንያት በቀጥታ ከሚደርሰው የሰዎች ሞት ባሻገር፤ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኘው ሰብዓዊ ሁኔታ በግጭቱ ምክንያት ይበልጥ ስለሚባባስ የሰዎችን ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ፎርድ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር የሚገኙ 13 ሚሊዮን ሰዎችን የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ እንዳደረጋቸው ያስታወሱት ሚኒስትሯ፤ የአሁኑ ውጊያ እና በህወሓት የተያዘው የዓለም የምግብ ድርጅት ነዳጅ፤ የሰብዓዊ ድርጅቶችን ስራ “ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል” ብለዋል።

የብሪታንያ መንግስት፤ ህወሓት የያዘውን ነዳጅ ለእርዳታ ማከፋፈል እና ለሌሎች አንገብጋቢ አገልግሎቶች እንዲውል እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል ሲሉም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትሯ አክለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7931/

@BreakingNewsEthiopiaa
2.0K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:34:42
"ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል" - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም:-

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው እርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት እርዳታው ለተረጂው ሕዝብ እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት አቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።

ይሁንና በሕወሓት የሽብር ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ  አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሓት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

በመሆኑም ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

@BreakingNewsEthiopiaa
2.0K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ