Get Mystery Box with random crypto!

AMHARA INFORMER

የቴሌግራም ቻናል አርማ aiinfor — AMHARA INFORMER A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aiinfor — AMHARA INFORMER
የሰርጥ አድራሻ: @aiinfor
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.62K
የሰርጥ መግለጫ

#NewsInfo

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 21:14:09 ➔በሌሎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች
▬ኦነግ ወደ አገር ቤት የገባ ቀን 400 ጋሞዎች፣ ጉራጌዎችና አማራዎች ተጨፈጨፉ።
▬በ2013 ዓ.ም በኦነግ የተከበቡ ንጹሐን የመታደግ ዓላማ አንግበው በፖሊስ መኪና ሲጓዙ የነበሩ 20 የፌደራል ፖሊስ አባላት በቦንብ ጋይተው መንገድ ላይ ቀሩ፡፡
▬በ2013 ዓ.ም ኮንሶ ወረዳን የወረረው የኦነግ ታጣቂ “ሥማችሁ ከአማራ ጋር ይመሳሰላል››በሚል ምክንያት ከ66 በላይ የአማሮ ተወላጆችን ጨፈጨፈ፡፡

ማሳሰቢያ ፡-
▬▬▬▬
ይህ የዘር ፍጅት መረጃ በመንግሥታዊ መዋቅር ታግዘው በድብቅ ከተፈጸሙ እልፍ አእላፍ ጭፍጨፋዎች መሀከል ሾልከው የወጡትንና በኔ ማስታወሻ ላይ የተመዘገቡትን ያካተተ እንጂ በብልጽግና ዘመን የተፈጸመውን ድምጽ የለሽ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሊገልጽ የሚችል አይደለም፡፡


አሳዬ ደርቤ
1.6K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:14:08 ዘር ፍጅት የታወጀባቸው አማራዎች የጭፍጨፋ ዶሴ ሲገለጥ
(አማራ የሆንክ ሁሉ ይሄንን ማንበብ ግዴታህ ነው)
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬▬
➔ጃዋር መሐመድ ተከብቤያለሁ ያለ ቀን 86 አማራዎች ተገደሉ፡፡

➔አርቲስት ሐጫሉ የተገደለ ቀን 350 አማራዎች ተጨፈጨፉ፡፡

➔በቤኒሻንጉል ክልል በመተከል ዞን በ2013 ዓ.ም ብቻ በኦነግና በጉምዝ ታጣቂዎች 2,980 አማራዎች ሲገደሉ 411 ዜጎችን አካል ጉዳተኛ ሆኑ፡፡ 408 ሕጻናትም ወላጅ አልባ ለመሆን ሲገደዱ፣ 216,980 ዜጎች ደግሞ ተፈናቀሉ፡፡

➔በ2012 ዓም ወደ ደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ያመሩ 17 ሴት ተማሪዎች ወደ ትውልድ ቀያቸው በመመለስ ላይ ሳሉ ተሰወሩ፡፡

➔በወርሐ ጥቅምት መጀመሪያ 2013 ዓ.ም መከላከያ ሠራዊቱ እንዲወጣ በተደረገ ቅጽበት ለስብሰባ የተጠሩ ከ287 በላይ የጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አማራዎች አንድ እንኳን ለመሀላ ሳይተርፍ ሁሉም ተጨፈጨፉ፡፡ የክልሉ መንግሥትም የተወሰነውን አስከሬን ማንነት ቀይሮ ኦሮሞዎች ቢያደርጋቸውም ጭፍጨፋውን ግን መካድ አልተቻለውም፡፡

➔ሚያዚያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ያለማንም ከልካይ ወደ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ያመራው የኦነግ ታጣቂ አጣዬን አውድሞ ከ265 በላይ አማራዎችን ገደለ፡፡

➔በወርሐ ሕዳር 2013 ዓ.ም ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 7 ሹፌሮች “አሊ ዶሮ” ላይ በኦነግ ታግተው ተገደሉ፡፡ ተሸከርካሪዎቻቸውም ተቃጠሉ፡፡

➔ከሕዳር 20-21 2013 ዓ.ም፡- በምስራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ አርቁምቢ መንደር በምሽት ቃጠሎ መነሳቱን የሚገልጽ እሪታ ሰምተው እሳቱን ለማጥፋት ከወጡ አማራዎች መሃከል 38 ንጹሐን ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ፡፡

➔ሕዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም በዚሁ ዞን እና ወረዳ ውስጥ በሪሶ ቀበሌ ከ27 በላይ አማራዎች ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ደብዛቸው ጠፋ፡፡

➔ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2013 ዓ.ም፡- በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ 15 አማራዎች ሲገደሉ፣ ከአንድ ሺህ በላይ ደግሞ ተፈናቀሉ፡፡ በቀጣዩ ወር ታሕሳስ 1 ቀን 2013 ዓም በዚሁ ዞን ውስጥ በጊዳ አያና ወረዳ ድሬ ጎዳ ቀበሌ ከ20 በላይ አማራዎች የሞት ፍርድ ሲፈረድባቸው ከ40 በላይ ንጹሐን ደግሞ ታፍነው ተወሰዱ፡፡

➔ታሕሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም፡- በሆሮ ጉድሩ ዞን አባይ ጮመን ወረዳ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካን የሸንኮራ እርሻ በእሳት ያጋየው የኦነግ ታጣቂ በአካባቢው ያገኛቸውን የአማራ ተወላጅ የሆኑ 7 አዛውንቶችን በጥይት ደብድቦ ገደለ፡፡ ታሕሳስ 7 ቀን ደግሞ በሆሮ ጉድሩ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ በከካ በሚባል አካባቢ የአቶ ባይሌና የአቶ እንደሻው ስድስት ቤተሰቦች በጅምላ ሲያልቁ ሌሎች አማራዎችም ተጎዱ፡፡

➔ከየካቲት 27-28/ 2013 ዓ.ም፡- በሆሮ ጉድሩ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ ደቢስ ቀበሌ ሕጻናትን ሳይቀር በቀጠፈ ጭፍጨፋ ከ50 በላይ አማራዎች ተገደሉ፡፡ ይሄውም መረጃ በቁጥር ብቻ ሳይሆን በሥም ዝርዝር ጭምር ተደግፎ ሶሻል ሚዲያ ላይ የወጣ ቢሆንም በመንግሥት በኩል ግን የተባለ ነገር አልነበረም፡፡

➔በወርሐ መጋቢት 2013 ዓ.ም፡- የኒጀርና የማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በመውጣታቸው የተነሳ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጠሪያ ማለፏን የሰሙ ኢትዮጵያውያን በደስታ ሲንሳፈፉ፣ በዚያው ምሽት የኦነግ ታጣቂ በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ሰዴቃ እና ሎንቺሳ ቀበሌዎች ውስጥ በሰነዘረው ጥቃት ከ170 በላይ አማራዎች ተጨፈጨፉ፡፡ የኦሮሚያና የአማራ ክልል መንግሥታትም የኀዘን መግለጫ አስተላለፉ፡፡

➔ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም፡- በኦነግ ሸኔ ጥቃት ከ350 በላይ አማራዎች መገደላቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ቢገለጽም ኢሰመኮ ባቀረበው ሪፖርት ግን ከ150 በላይ ንጹሐን መገደላቸውን አረጋግጦ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የዜጎችን ሕይወት እንዲጠብቁ አሳሰበ፡፡ ይሄውም ሪፖርት ከኢሰመኮ የፌስቡክ ገጽ ላይ ይገኛል፡፡

➔ነሃሴ 9/2013 ዓ.ም፡- በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 24 አማራዎች ሲገደሉ 10 አማራዎች ደግሞ ታግተው መወሰዳቸው የወረዳው አስተዳደሪ በሆኑት በአቶ ቡላ ደመረ አማካኝነት ተገለጸ፡፡

➔በሌላ መልኩ ደግሞ አሸባሪው ትሕነግ ተመትቶ ከተባረረ በኋላ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታ መንፈስ ሲሞላ ኦነግ ሸኔ ግን በወለጋና በሸዋ የአማራ ንጹሐንን ነፍስ ሲበላ ነበር፡፡ በወቅቱም የሚከተሉት የጥቃት ሪፖርቶች ኢሰመጎ ገጽ ላይ ወጥተው ነበር፡፡

➔መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ጅባት ወረዳ፣ ዳርጌ ቀበሌ በስድስት መንደሮች በርካታ ቤቶችና ክምሮች ተቃጥለው በሺህዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸውን… በ23/4/2014 ዓ.ም በሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርቲ ወረዳ ለገበያ የወጡ ሰባት አማራዎች ተገድለው አስከሬናቸው ተሰጥቶ መዋሉን…. በ11/4/2014 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ መንቃት ቀበሌ ሌሊት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 10 አማራዎች ተገድለው በማግሥቱ በአምቦ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መቀበራቸውን…..ታሕሳስ 14/2014 ዓ.ም ደራ ከተማ እና አካባቢው ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አማራዎች ሲገደሉ በከተማው የሚገኙ የአማራ ባለሃብቶች ደግሞ ሲዘረፉ ማደራቸውን….. ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ በእርሻ ማሳቸው ላይ በነበሩ ገበሬዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የስድስት ቤተሰብ አባላት የሆኑ 14 አማራዎች መገደላቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች በኢሰመጎ የቴሌግራም ገጽ ላይ ይፋ ሆነው ነበር፡፡

➔በመጋቢት ወር 2014 ዓም አባይ በረሐ ድረስ የመጣው የኦነግ ታጣቂ አራት ሹፌሮችን ገደለ፡፡ በዚያም ዘመቻው ጎሃ ጽዮን ድረስ ዘልቆ በመግባት ከ20 በላይ አማራዎችን ጨፍጭፎና በርካታ ንብረት ዘርፎ ተሰወረ፡፡

➔በወርሐ ጥር መጨረሻ 2014 ዓ.ም አሸባሪው ኦነግ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳማ ወረዳ 168 አማራዎችን ጨፈጨፈ፡፡ ከእነዚህም አማራዎች አስከሬን መሃከል የ87 ንጹሐን አስከሬን ባንድ ቦታ ተከምሮ መገኘቱ በመንግሥት ሚዲያዎች ሳይቀር ተላለፈ፡፡ ፊደል የቆጠሩት የአማራ ልጆችም በሁለት ቀናት ውስጥ በተጨፈጨፈው ወገናቸው ፈንታ በሁለት እግሩ የቆመ የአገው ፈረስና የአንዲት ቆንጆ ልጅ ፎቶ ይዘው “አይገርምም ወይ” ሲባባሉ ነበር፡፡

➔በእለተ ስቅለት 2013 ዓ.ም በአንድ በአውቶብስ ወደ ጎጃም በማምራት ላይ የነበሩ ከ30 በላይ አማራዎች መንገድ ላይ ታግተው ተረሸኑ፡፡

➔ታሕሣስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም (የገና እለት) ደግሞ በሆሮጉድሩ ዞን የኦነግ ታጣቂ በከፈተው ጥቃት አጎቴን ጨምሮ 26 አማራዎች ባንድ ጎጆ ውስጥ ከተዘጋባቸው በኋላ በእሳት ተቃጥለው አለቁ፡፡

➔ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ባንክ ሥራ በጀመረበት እለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በብልጽግና ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራሮች ድጋፍ ከ1500 አማራዎች በኦነግ ታጣቂዎች ተጨፈጨፉ፡፡

➔ከሁለት ቀን በፊት ደግሞ በቄለም ወለጋ ሃዋ ገላን ወረዳ ለበተፈጸመ የጅምላ ፍጅት በ8 ሰዓታት ውስጥ ከ350 በላይ አማራዎች ተጨፈጨፉ፡፡
1.4K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 14:08:38 #አስቸኳይ #share

#Gojjam
አዴት ላይ በየ100 ሜትሩ ርቀት አድማ በታኝ ተበትኖል ስናፐር ተጠምዶ ይገኛል።

በአካባቢው ያላችሁ ፋኖዎች ጥንቃቄ አድርጉ።
2.1K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 16:24:47 ሰበር ዜና!

እነ አርበኛ ዘመነ ካሴን አገኛለሁ በሚል እየተንቀሳቀሰ የከረመው መንግስታዊ አፋኝ ቡድን ከመሸንቲ ከተማ ወጣ ብሎ ወደ አጫድር ገጠር አካባቢ በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

እነ አርበኛ ዘመነ ካሴን አገኛለሁ በሚል እየተንቀሳቀሰ የከረመው መንግስታዊ አፋኝ ቡድን ከመሸንቲ ከተማ ወጣ ብሎ ወደ አጫድር ገጠር አካባቢ በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው ሲሉ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች ሰኔ 19/2014 በየአብያተ ክርስቲያናቱ እየዞሩ ሲያስፈራሩ እንደነበር አውስተዋል።

መሸንቲ ከተማ እንደወጣን መጠበቂያው አካባቢ ወደ አጫደር ገጠሩ አካባቢ ያቀናው እነ አብይ አህመድ ለአፈና የላኩት የመከላከያ ሰራዊት አርበኛ ዘመነ ካሴን አገኛለሁ በሚል ነው በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ያለው ሲሉም አክለዋል።

የአካባቢው የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በንፁሀን ዜጎች እና በሰው እና በእንስሳት እንዲሁም በቤት ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው፤ የጉዳቱን መጠን ምን ያህል እንደሆነ ግን ገና አላወቅነውም ብለዋል።
2.2K views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 19:08:09 ሊታወቅ የሚገባው መረጃ ከጋዜጠኛ ገነት አስማማው!

"የሰው ዘር የተባለ ሁሉ ይህንን ይስማልን"

"የቀበሌው አስተዳዳሪ እኮ ከላይ በተላለፈልኝ ትዕዛዝ ጭፍጨፋውን አስፈጽሜያለሁ አለ ወላሂ" - የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ

የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ እና የቀበሌዋ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ ኪዳኔ ወርዋ በሃገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በአራተኛ ቀናቸው ዛሬ በቶሌ ቀበሌ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ እውነታውን በህዝብ ፊት ተናዘዋል

የቀበሌዋ አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ ኑዛዜያቸውን ሲናገሩ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ በስልክ ደውለው ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም አሉኝ፡፡

ሰራዊታችን( ኦነግ ሸኔን) ቅዳሜ የሚያካሂደው ኦፕሬሽን አለ ብለው አስፈላጊውን ትብብር እንዳደርግ ነግረውኛል ብሏል አቶ ንጋቱ፡፡

አቶ ንጋቱ እንደሚሉት አቶ ባጫ እና የጸጥታ ሃይሉ ሃላፊ፤ ሰራዊቱ ቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ማታ እንደሚገባ፤እኔ፤አቶ ኪዳነ መርዋ እና ሳጂን አሰፋ የፖሊስ አባላቱን እና የሚሊሻ አባላቱን ከቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ዕለት እንድናስወጣቸው አዘዙን ብሏል፡፡

ሰራዊቱ ወደ ቶሌ ቀበሌ ሲገባም ሰንጋ እንዲታረድለትም ታዘናል የሚሉት አቶ ንጋቱ የተባልነውን አድርገናል ብለዋል፡፡

የጸጥታ ሃይሉን ጨምሮ የቶሌ ቀበሌ ዋና ዋና አመራሮች ሃሙስ ዕለት ቀበሌዋን ለቀው እንዳደሩ የተናገሩት አቶ ንጋቱ ከቀበሌዋ በቅርብ ርቀት ሂደው ማደራቸውን ገልጠዋል፡፡

ሰራዊቱ ሃሙስ ማታ ከገባ በኋላ በቀበሌዋ የተጣለለትን ሰንጋ እየተመገበ ሲጨፍር እንዳደረ ተናግረዋል፡፡

አርብ ዕለት ቀበሌዋ ምንም አይነት የመንግስት መዋቅር ቀበሌ ሆነች የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ቀኑን ሙሉ የቶሌ ቀበሌ ሰፊ በመሆኑ እኛም ራሳችንን ቀይረን ከቀበሌው አንድም ሰው እንዳይወጣ ከሰራዊቱ ጋር ከበባ አደረግን ይላሉ፡፡

የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና ሰላም እና ጸጥታ ሃላፊው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይከታተሉ ነበር የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ዕለት ደውለውልኝ ቅዳሜ ከጠዋቱ ሁለት ጭፍጨፋው እንደሚጀመር እና ስምንት ሰአት ውስጥ እንደሚያልቅ ትዕዛዝ አስተላልፈውልኛል ብለዋል፡፡

የወረዳ አመራሮቹ ሲደውሉልኝ ሌሎች አመራሮችም ከጎኔ ነበሩ እንደ እኔ ራሳቸውን ቀይረው ከሰራዊቱ ጋር ተሰልፈዋል ብለዋል፡፡

አቶ ባጫ ቅዳሜ ተዋት ሁለት ሰአት ይጀመራል ባሉት መሰረት ጭፍጨፋውን እና ዝርፊያውን ጀመርን እስከ ስምንት ሰአትም ቆየን ብለዋል አቶ ንጋቱ

ጥቂት አማራዎች አልሞት ባይ ተጋዳይነታቸውን ሲያደርጉ የሰራዊታችን አባላት ሲመቱ ከወረዳ አምቡላንስ ተልኮልን፤የሰራዊታችንን ቁስለኞች ወደ ጊምቢ ሆስፒታል ስታመላልስ ዋለች አምቢላንስ ነበረች ያሉት አቶ ንጋቱ ኡመታ ከቀኑ ስምንት ሰአት ሲሆን በቃችሁ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ጊምቢ እየመጣ ነው የሚል ትዕዛዝ ተላልፎልን ተመልሰን ከሰራዊታችን ጋር ወደ ጫካ ሄድን፤ከዚያም እኔ እና ባልደረቦቸ መሳሪያችንን እና ልብሳችንን ቀይረን ወደ ቶሌ ቀበሌ ሰላማዊ መስለን መጣን ሲሉ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝብ በተሰበሰበበት ተናዘዋል፡፡

የቶሌ ቀበሌ የሚሊሻ ጽ/ቡት ሃላፊ አቶ ኪዳነ መርዋም በተመሳሳይ የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ የሰጡትን መረጃ ተናግረዋል፡፡

ከጭፍጨፋው የተረፉት የአማራ ተወላጆች ይህንን ከሰሙ በኋላ በከፍተኛ ዋይታ እና ጩሀት ውስጥ እንደነበሩ የአካባቢው የአይን እማኝ ነግሮኛል
አሁን ላይ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በአካባቢው መኖሩን የገለጡት ነዋሪው ገዳዮቹን መከላከያ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት እየተቃወሙ ነው ብለዋል፡፡

‘’ጨፍጫፊዎች ሲያዙ ፤ ልዩ ሃይሎቹ ያለቅሳሉ ይቆረቁራሉ የሚያዝኑት ለእነሱ ነው ለእኛ አይደለም ‘’ ሲሉ ገልጸውታል

መከላከያው ከልዩ ሃይሉም ጋር ተፋጧል የሚሉት የአይን እማኙ ጫካ የገባውም ሁነ ያልገባው አንድ ናቸው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

ከጭፍጨፋ የተረፈው ሜዳ ላይ ነው ያለው፤የሚልሰው የሚቀምሰው የለም የሚሉት ነዋሪው ለመሳፈሪያ ገንዘብ ያለው አማራ በመኪና እንኳን ተሳፍሮ እንዳይሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ሹፌሮቹ ሁሉ አኩርፈዋል አድመውብናል ብለዋል።

ከቶሌ ቀበሌ ሸሽተው በአጎራባች ግንቢ አቅራቢያ የተፈናቀሉ 3ሺ የሚደርሱ አማራዎች በለቻቸው ብር እንኳን ገዝተው እንዳይመገቡ ብራቸውን ከፍለው እንኳን የሚሸጥላቸው ነጋዴ አላገኙም ስቃይ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

አማራ እዚህ መኖር የለበትም መልሰን ስንመጣ እንዳናገኛችሁ ተብለናል የሚሉት የአካባቢው ነዋሪ፣ የተረፍነውን አዲስ አበባ ድረስ እንኳን የሚወስደን እና እሩሃችንን የሚታደገን ወገን ይድረስልን፤ ድምጻችንን አሰሙልን ሲሉ ተማጽነዋል።

ዛሬም ድረስ አስከሬን እየተቀበረ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪው፤ እኔ ራሴ እንኳን የ20 ቀን ህጻናትን ጨምሮ 19 ህጻናት ከተቃጠሉበት እና ታርደው ከተጣሉበት፤በጥይት ተመተው ከወደቁበት አንስቸ 20 ህጻናትን ጉድጓድ ቆፍሬ አንድ ላይ ቀብሬያለሁ ብለዋል፡፡ በቶሌ ጉትን ቀበሌ ብቻ ከአስር ሺ የማያንስ ጠቅላላ ብሬል እና መትረየስ የታጠቀ ሰራዊት ነው የጨፈጨፈን ብለዋል ነዋሪው።

ሼር ይደረግ፣ ብዙዎች ጋ ይድረስ!
3.6K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 21:38:27 #አዲስ_አበባ

የኦሮሞው ሰልቃጭ ብልፅግና ሸኔ ለእርድ እያመቻቸህ መሆኑን አውቀህ ተዘጋጅ!

ዛሬ ከወደ አዳነች አቤቤ ቢሮ እየተሰማ ያለው ነገር ከባድ ነው።በከተማው ውስጥ የአማራ ተወላጅ የሆነ ፖሊስ፣ፌደራል፣እና ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛም ይሁን ባለሀብት መሳሪያ ያለው እንዲያወርድ ፣በፖሊስ እና በፌደራል መዋቅር ስር ያሉ የአማራ ተወላጆች ደሞ መሳሪያ እንዳይሰጣቸው ትዛዝ ተሰቷል።

ይሄ ማለት ደሞ በከተማው ያለው የኦነግ አባላት አማራው ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መታቀዱን ያመለክታል።
3.7K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 22:23:50
ሀዋሳ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በዩኒቨርስቲ ተማሪነትና ለአንድ ሴሚስተር በኮሌጅ መምህርነት ቆይቸባታለሁ!
እናም እነዚያን ቅንና የዋህ ሲዳማዎችን አውቃቸዋለሁ!

ዛሬ ሚዲያቻችን ኦነግ እየተደመሰሰ ነው እያሉ እየዘገቡ ባለበት ቀን የሲዳማዎች ቀየና ህይወት በኦነግ እየወደመ እንደሆነ በሰማሁ ጊዜ ልቤ ተነካ!

ሄኖክ
4.4K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 22:38:55
#በየትኛው አለም የዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ህዳጣን (አናሳ ቁጥር ያለው ማህበረሰብ በንዑሳን የበላይነት ሊመራ አይችልም።የለምም።

ስለዚህም አዴፓም ሆነ ስልጣን ላይ ያለው የኢሀዲግ መንግስት በህውኃት አማራን የጣሰን ህግ ሲሰራ ዝም ብለን የምናልፍበት ግዜ አብቅቷል።

ለ20% ነዋሪ ዞን ይሰጣል፣ 100% አመራሮች ከወለጋ ይመጡለታል፣ ለ20% ነዋሪ የስራ ቋንቋ የፈለገዉ ይሆንለታል። በየትኛውም ህግ majority rules እና minority right ህግን የጣሰ ያለ አግባብ የተሰራው የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እንደገና ህዝባዊ ምርጫ ተደርጎ መፍረስ አለበት።

አማራ በርሥቱ እንደ መጤ የሚቆጠርበት ዘመን ያበቃ ዘንድ ነው ትግላችን ።

መረጃው:- በ1994 የተደረገው CSA የህዝብና ቤት ቆጠራ የጥናት ውጤት ነው።
3.1K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 18:15:08
2.1K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 18:15:03 የአዲስ አበባ ጉዳይ እና የእስክንድር ተቀባይነት ማጣት
……………………………………………………………………..
የአዲስ አበባ ጉዳይ የእስክንድር ብቻ መስሎ ታይቷል፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ብሔርተኞች ደግሞ እስክንድርን የአማራ ብሔርተኛ ነው የሚሉት፡፡ ስለዚህ የአዲስ አበባን ጉዳይ የአማራ ጉዳይ አድርገው ነው የሚያዩት፡፡
የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ብሔርተኞች ይህን ሲሉ፤ ሌላው ተከትሎ ‹‹እስክንድር አበደ፣ ጨለለ፣ ነቀለ…›› እያለ ያሾፋል፡፡ በእርግጥ የእስክንድር አካሄድም በፖለቲካ ባህላችን መንገድ አይደለም፡፡ ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው፡፡ በስልት መሄድ አይችልበትም፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን የእስክንድር ጥያቄ የአንድ ወገን ጥያቄ አልነበረም፡፡ ዛሬ የሚያሾፍበት ቢበዛም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የሚመሰገንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ምነው ያኔ ሀሳቡን ደግፈን አብረነው በቆምን ነበር የሚባልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው!
የአዲስ አበባ ጉዳይ ለኦሮሞ ፖለቲከኞች የልዩ ጥቅም ጉዳይ አይደለም፡፡ በልዩ ጥቅሙ ጉዳይ ስንደነቅ አሁን ግን ጥያቄው ከዚያ አልፏል፡፡ አሁን ‹‹የኦሮሞ ልዩ ጥቅም ይከበር›› ማለት ከኦሮሞ ጋር ያጣላል፡፡ ጉዳዩ የባለቤትነት ጥያቄ ነው፡፡ የባለቤትነት ጥያቄ ማለት አዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ ናት ማለት ነው፡፡
ይሄ ማለት አዲስ አበባ ልክ እንደ ጅማ፣ አምቦ፣ ነቀምት.. ናት ማለት ነው፡፡ በእነዚህ ከተሞች ማንም አያዝዝም፡፡ የእነዚህ ከተሞች እንቅስቃሴ የሚወሰነው በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ነው፡፡ የሥራ ቋንቋቸውም የክልሉ የሥራ ቋንቋ ኦሮምኛ ነው፡፡ በእነዚህ ከተሞች የሌላ ብሔር ተወላጅ መኖር ይችላል፤ የሚተዳደረው ግን በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ሕግና ደንብ ነው፡፡
‹‹አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት፤ ግን ሌሎች ብሔሮችም መኖር ይችላሉ›› እየተባለ ያለው ለዚህ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ የምትኖረው ልክ ጅማ፣ አምቦ፣ ነቀምት እንደሚኖረው ሌላ ብሔር ነው፡፡ ዛሬ ላይ ሆነህ ስታስበው ‹‹ይሄማ እንዴት ሊሆን ይችላል!›› ያስብልህ ይሆናል፤ ግን በዚህ አካሄድ ሩቅ በማይባሉ ዓመታት ውስጥ ይሆናል፡፡
‹‹አዲስ አበባ የኦሮሚያ ሆና፤ ልክ በኦሮሚያ ከተሞች እንደሚኖረው ሌላው ብሔር ብንኖር ምን ችግር አለው?›› ይባል ይሆናል፡፡ ምንም ችግር አልነበረውም! ችግሩ የሚመጣው ይህ ሕግ ጸድቆ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ነው፡፡ ለዛሬው ለPolitical Correctness ምንም አይባልም፤ ‹‹ውጣልኝ›› ማለት የሚመጣው በሕግ ደረጃ ጸድቆ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ነው፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ከሆነች ዛሬ ከወለጋ ውጣ እንደሚባለው ሁሉ ከአዲስ አበባም ውጣ ትባላለህ፡፡
የኦሮሞ ብሔርተኞች ‹‹አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት›› ሲሉ የአማራ ብሔርተኛ የተባሉት ግን ‹‹አዲስ አበባ የአማራ ናት›› አላሉም፡፡ እስክንድር እብድ ቢሆን ኖሮ ‹‹አዲስ አበባ የአማራ ናት›› ነበር የሚል፡፡
እብድ አካሄድ ማለት አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ማለት ነው፡፡ እንዲያውም ለዚህ ተመጣጣኝ አዲስ አበባ የአማራ ናት የሚል ሌላ አካሄድ ያስፈልጋል፡፡ አዲስ አበባ የሸዋ ነገሥታት መሬት ናት፡፡ አዲስ አበባን የመሰረቷት አጼ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ናቸው፡፡ ከዚያ በፊትም የሸዋ ነገሥታት መሬት ነው፡፡ ስለዚህ የመሬ፣ የመንዝ፣ የአንኮበር ገበሬ እየመጣ መስፈር አለበት፡፡ እንዲህ እንዲህ አይነት አካሄዶች ያስፈልጉ ነበር፡፡ ችግሩ ግን አሁን አዲስ አበባ የአንድ ብሔር አይደለችም፡፡ የአገር ዋና ከተማ ስለሆነ ሑሉም ብሔር ነው የሚኖርባት፤ ስለዚህ የአንድ ብሔር ባለቤትነት ሊኖራት አይገባም፡፡
ይህን ሀሳብ የሚያራምደውን እስክንድርን ‹‹እብድ›› እያለው ያለው ግን ሁሉም ነው፡፡ ለማን እየታገለ እየመሰላቸው እንደሆነ አላውቅም!
እስክንድርን እብድ ያስመሰሉትን ነገሮች እናንሳና ውጤታቸው ምን እንደሆነ እንታዘብ፡-
1. የመስቀል አደባባይ ጉዳይ
እስክንድር የመስቀል አደባባይን ግንባታ ሲቃወም ‹‹እብድ›› ያላለው አልነበረም፡፡ እንዴት ግንባታን፣ ልማትን፣ ብልጽግናን ይቃወማል? አምሮና ተውቦ የመስቀል በዓል ቢከበርበት ምን ችግር አለው? የሚሉ የዋሃን ነበሩ፡፡ የእስክንድር ጥያቄ ሀሳብ የነበረው ደግሞ፤ መንግሥት ካስገነባና ካስዋበ በኋላ በሕዝብ ገንዘብ የተሰራ ስለሆነ ከዚህ በኋላ የኦርቶዶክስ አይሆንም ይላል ነው፡፡ እነሆ በዚህ ዓመት እንዳየነው ገና ከወዲሁ የባለቤትነቱ ጉዳይ ሲያወዛግብ ቆይቷል፡፡ የብልጽግና ደጋፊዎችም እንደ ምክንያት ሲያቀርቡት የነበረው ‹‹በሕዝብ ገንዘብ የተገነባን ቦታ እንዴት ለአንድ ሃይማኖት ይሰጣል?›› የሚል ነበር፡፡
የዚህ አካሄድ መጨረሻ የሚሆነው መጀመሪያ መስቀል አደባባይን ከኦርቶዶክስ ባለቤትነት ማላቀቅ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በማስፈቀድ ለአንድ ወይም ሁለት ዓመት ያህል የመስቀል በዓል ይከበርበታል፤ ከዚያ በኋላ የመስቀል በዓል እንዳይከበርበት መከልከል ይቻላል፤ ቤተ ክርስቲያኗም ህጋዊ መከራከሪያ እንድታጣ ይደረጋል፡፡
2. የዓድዋ አደባባይ
የዓድዋ አደባባይ ግንባታ ሲጀመር የእስክንድር ተቃውሞ የነበረው፤ ምኒልክ አደባበይ የሚለውን ታሪክ ለመቀየር ነው የሚል ነበር፡፡ እነሆ ገና ግንባታው እንኳን ሳይጠናቀቅ የእስክንድር ሥጋት ልክ መሆኑን አረጋገጥን፡፡ በዚህ ዓመት የተከበረው የዓድዋ በዓል ምኒልክ አደባባይ ሳይሆን ዓድዋ ድልድይ እንድሆን ተደረገ፡፡ በወቅቱ ለተፈጠረው ውዝግብ ከንቲባዋ የሰጡት አስታራቂ ሀሳብ፤ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ዓድዋ አደባባይ ስለሚጠናቀቅ እዚያ ይከበራል የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ምኒልክ አደባባይ አይኖርም ማለት ነው፡፡
ታዲያ የእስክንድር ሥጋት ምኑ ነበር ስህተት? ምኒልክ አደባባይ ባይባል ምን ችግር አለው? የምኒልክ ሀውልት ቢፈርስ ምን ችግር አለው? ከሆነ በዚህ መስማማት ነው!
እነርሱ ምኒልክ አደባባይ የሚለውን ስም ለመለወጥ ይህን ያህል ርቀት ሲሄዱ፤ የምኒልክ አደባባይ አይለወጥ ማለት ምኑ ነው እብደት?
በአዲስ አበባ ውስጥ በብዙ ትምህርት ቤቶች በር ላይ የኦሮምኛ ማስታወቂያ ነው የሚለጠፍ፡፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አርማ ለጊዜው በአማርኛና በኦሮምኛ ነው፡፡ ከጊዜ በኋላ ደግሞ አማርኛው ይቀር ይሆናል፡፡ አዲስ አበባ የሁሉም ናት ከተባለ ሕግ ሳይቀየር ኦሮምኛ ብቻ የአዲስ አበባ ቋንቋ መሆን ቀጣይ ወዴት እንደሚወስደን አመላካች ነው፡፡
ባለፈው ብልጽግና ከነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ከነዋሪዎች የተሰማው ቅሬታ፤ በየመገልገያ ቦታዎች በኦሮምኛ ካልሆነ አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም የሚል ነው፡፡ በቅርቡ ኢንጂነር ጌታሁን ሔራሞ ያጋሩን ገጠመኝም የዚሁ አካል ነው፡፡ አንድ የፌዴራል ተቋም ሄደው ጥበቃው በኦሮምኛ ካልሆነ አላስተናግዳቸው ብሎ ሌሎች ሰዎች መጥተው ነው ያግባቧቸው፤ ጥበቃው አማርኛ ይችል ነበር፡፡
በአጠቃላይ እየሆኑ ያሉ ነገሮች ቀጣይ ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ናቸው፡፡ ስለዚህ የእስክንድር ጉዳይ የአንድ ግለሰብ ስሜት ሳይሆን የሁሉንም ችግር ይዞ የተነሳ ነው፡፡ ዛሬ ብትስቅበትም ነገ ችግሩ ሲያደባይህ ታመሰግነዋለህ! የኦሮሞ ብሔርተኞች የሚስቁበት እኮ ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን አስልተው ነው!

ዋለልኝ
2.1K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ