Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና 🇪🇹🌟

የቴሌግራም ቻናል አርማ seberr_zena — ሰበር ዜና 🇪🇹🌟
የቴሌግራም ቻናል አርማ seberr_zena — ሰበር ዜና 🇪🇹🌟
የሰርጥ አድራሻ: @seberr_zena
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.59K
የሰርጥ መግለጫ

ነፃነት ለህዝባችን 〰 ብልፅግና ለሀገራችን

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-17 07:26:09
የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ጆ ባይደን ወሰኑ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት ዶናልድ ትራምፕ የተወሰነዉን ውሳኔ በመቀልበስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቅደዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ሊመለሱ ይችላሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በአልሸባብ የታጣቂ ቡድን መሪዎች ላይ ዒላማ ለማድረግ ከፔንታጎን የቀረበላቸዉን ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸዉን በፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆነችዉ አድሪያን ዋትሰን እንደተናገሩት "እንደገና ለማስጀመር የወሰነው የኃይላችንን ደህንነት እና ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ብሎም ለአጋሮቻችን ቀልጣፋ ድጋፍ ለመስጠት ነው" ብለዋል።

አክለዉም "በአልሸባብ ላይ የበለጠ ውጤታማ ትግል" ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት እሁድ እለት አዲሱን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን መምረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

#share
4.1K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 07:21:18
የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ

ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል።

የቢሮው ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው ትሕነግ የጥፋት መንገድ ተጋሪዎች የአማራን ሕዝብ አንድነት ለመሸርሸር በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን የተለያዩ አጀንዳዎችን እየዘረጉ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው የሽብር ቡድኑ አሁንም ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው ብለዋል።

የጥፋት ኃይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

#share
3.1K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 21:14:47
#ሰበር_ዜና

ግድባችን ኃይል ማመንጨት ጀመረ።
ብርሃን፣ ጉልበት፣ ሐብት መሆን ጀመረ

አንኳን ደስ አለን !
እንኳን ደስ አላችሁ !
የሚጠበቀው ቀን ዛሬ እውን ሆነ!!!

#GERD #Ethiopia #Africa
6.5K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 12:04:19
በሻሸመኔ በህገወጥ መንገድ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረተ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ድርጅት ታሸገ!

በቀን 27/01/2014 በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት መሥራቱን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።

በዚህም ቅኝት ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፣ የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት እንዲሁም ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጠ የተገኘ አንድ ድርጅት ላይ ምርት የማምረት ሥራዉን እንዲያቆሙና ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት ምርትና ለዘይት ምርት የሚገለገሉበት የቅባት እህል (ጎመንዘር) ጋር እንዲታሸጉ መደረጉ ተገልጿል።

በገበያ ቅኝቱ ወቅት ባጠቃላይ በግምት 150 ኩንታል በላይ የጎመንዘር እህል እና በዛገ በርሜል የተከማቸ 80 በርሜል ህገወጥ ዘይት አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋው 2 ሚሊየን 244 ሺህ ብር የሚያወጣ ህገወጥ የዘይት ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው መደረጉንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

[Addis Maleda]
12.8K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 12:25:46
#ጥንቃቄ

የእብድ ውሻ በሽታ በመቅደላ ተቀሰቀሰ ፦

• 2 ሰዎች ሞተዋል።
• ከሟቾች ጋር ንክኪ ያላቸው 9 ግለሰቦች ወደከፍተኛ ህክምና እንዲሄዱ ጥረት እየተደረገ ነው።

በመቅደላ ወረዳ የእብድ ውሻ በሽታ ተቀስቅሶ የሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አሳወቀ።

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የእብድ ውሻ በሽታ መከሰቱ ተገልጿል።

በመቅደላ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጤና ኦፊሰር የሆኑት አቶ ዋሱ ሞላ እንደገለፁት በወረዳው 08 ቀበሌ ባዙራ በሽታው ተከስቶ የ2 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከሟቾች ጋር ንክኪ ያላቸው 9 ግለሰቦች ወደ ከፍተኛ ህክምና እንዲሄዱ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በቀበሌው እስካሁን 52 ውሻዎች መገደላቸውን ገልፀው ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት በማድረግ የቀሩ ውሻዎችን ለመግደል የጉድጓድ ቁፋሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ አቶ ዋሱ ገልፀዋል፡፡

ማህበረሰቡ ውሻዎችን በማስከተብ እንዲሁም በመግደል ራሱን ከበሽታው እንዲከላከልና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
9.7K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-06 09:44:27
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዋናው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ማካሄድ ጀምሯል።
7.4K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 10:11:00
ትናንት በደረሰ የመኪና አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 15 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደረሰ!

መነሻዉን አርባ ምንጭ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3 03348 የሆነ ቅጥቅጥ FSR 45 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ትላንት ከጠዋቱ 2:30 አካባቢ ከአርባ ምንጭ መናኸሪያ ተነስቶ ወደ ጅንካ ሲጓዝ ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰው ከባድ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የተከሰተው በአሌ ልዩ ወረዳ ቀርቀርቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ላገኖ በሚባል አካባቢ ሲሆን፤ መኪናው ባጋጠመዉ የፍሬን ችግር ምክንያት መኪናው ሊገለበጥ መቻሉም ተገልጿል።

በአደጋው ምክንያት 8 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ በ6 ሰዎች ላይ ከባድ እንድሁም በ9 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአሌ ልዩ ወረዳ ፖሊስ አሳውቋል።

Via Addis Maleda
6.9K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-04 15:56:23
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ይፋዊ ፌስቡክ ገፅ #ሀክ መደረጉ ተገልጿል።
6.2K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-04 15:55:19 በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚወጡት መልዕክቶች ?

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኩል የወጡት ፅሁፎች ከፍተኛ መነጋገሪያ እየሆኑ ነው።

ከፅሁፎቹ መካከል አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ ተብሎ የወጣው ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ምንም እንኳን ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግግር ያላደረጉ ቢሆንም ኢብኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ንግግር ብሎ ከላይ የተያያዘውን ፅሁፍ አሰራጭቷል።

በተጨማሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በዝግ መምከሩን የሚገልፅ ሌላ ፅሁፍም አውጥቷል።

ድርጅቱ እስካሁን ስለተፈጠረው ጉዳይ በግልፅ ማብራሪያ አልሰጠም።
5.8K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-04 15:55:13
5.5K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ