Get Mystery Box with random crypto!

ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ! ባሕርዳር ዩኒ | ሰበር ዜና

ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ!

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ነሐሤ 21/2014 በተለያዮ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያሰመረቀ ሲሆን በዕለቱም ሲጠበቅ በነበረው ፕሮግራም ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ  እና  ለአትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት አበርክቷል::

ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር እየኖሩ ያሉ አርአያ ሰብ በመሆናቸው እንዲሁም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በስፖርቱ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት በመሆን እና ለህብረተሰብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት እየተጋች ያለች ተምሳሌት በመሆኗ ነው ብሏል ዮኒቨርሲቲው::

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ ሶስተኛ ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ እንዲሁም በማሪታይም ሙያ ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው በዛሬው ዕለት ያስመረቀው።

[Reporter]
@BreakingNewsEthiopiaa