Get Mystery Box with random crypto!

ESAT International

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomereja1 — ESAT International E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomereja1 — ESAT International
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomereja1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 154
የሰርጥ መግለጫ

የ Telegram ቻናላችንን Join አድርጉ🤏🤏👏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ኢትዮ አሜሪካ ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ
የ YOUTUBE ቻናላችንን SUBSCRIBE 🤏🤏👏 ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/ethiomereja1

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2021-02-13 20:12:58
በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊየን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ተያዘ!

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊየን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ ተይዟል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል።

@ethiomereja1 ሼር
79 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:58 መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማሩን ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ከሰተ ለገሰ፣ የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመሩት ከሚጠበቁት 13ሺህ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹን በመቀበል ላይ መሆኑንና የቀሩትንም እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች ኅብረት አቀባበል እየተደረገላቸው ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንሥቶ ትምህርታቸውን መከታተል መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች፣ መኝታ ቤቶች፣ ምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ አዳራሾችን የኮሮና ወረረሽኝን ለመከላከል ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቀድመው መሰናዳታቸውን ዶ/ር ከሰተ አስረድተዋል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩት እነዚህ ተማሪዎቹ የተቋሙን ሕግ እና ሥርዓት አክብረው ትምህርታቸውን መከታታል እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

ትምህርታቸው መከታተል ከጀመሩት መካከል ከደቡብ ክልል የመጣው የአዲሀቂ ካምፓሰ የሶሾሎጂ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ቸርነት ሺፈራው ትምህርት በመጀመሩ መደሰቱን ገልጾ፣ በንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት በኩል ግን እጥረት ስላለ እንዲስተካከል አስተያየቱን ሰጥቷል።

የእኛ ተማሪዎች ሕልም በሰላም እና ፍቅር ትምህርታችንን መከታተል እና ተመርቀን ራሳችንና ሀገራችን መጥቀም ነው ያለው ደግሞ የሁለተኛ ዓመት ሶሾሎጂ ተማሪ እንድሪስ አብዱ ነው።

ከኦሮሚያ ክልል የመጣው ተማሪ ጫላ ሳፋይ በበኩሉ ዩኒቨርሲቲው ለመማር ማስተማር የሚያስችል የግቢው መሠረተ ልማት ማሟላቱን ገልጿል።

በምግብ ሰዓት ግን በወረፋ ብዛት ምክንያት ለብዙ ሰዓታት እየጠበቅን መሆኑን ታውቆ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

@ethiomereja1 ሼር
77 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:57
በ24 ሰዓት ውስጥ አራት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያንን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋን በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ቀጥረው በማግኘት "2 ሚሊዮን ትክክለኛ የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ይዘህ ከመጣህ በ24 ሰዓት ውስጥ በሁለት እጥፍ በማተም በአጠቃላይ አራት ሚሊዮን ዶላር ስለሚሆን 40 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ ላንተ ቀሪውን 60 በመቶ ገንዘብ ደግሞ ለራሳችን እንወስዳለን" ብለው እንዲስማማ በማግባባት የማታለል ወንጀል ሲፈጽሙ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ካሜሮናውያኑ ኢትዮጵያዊውን ግለሰብ ያባዛነው የአሜሪካው ዶላር ናሙና ነው በማለት ትክክለኛውን ኖት አንድ መቶ ዶላር በመሥጠት ወደ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሄዶ ወደ ኢትዮጵያ ብር እንዲቀይረው በማደረግ ጭምር የሚያባዙት የገንዘብ ኖት ትክክለኛና ህጋዊ ተቀባይነት ያለው እንደሆነ በማስመስል ግለሰቡን ለማጭበርበር እንደቻሉ ከተገኘው ማስረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ጉዳዩን አስመልከቶ መረጃ የደረሳቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትም ሁለቱ ካሜሮናውያንና በውጭ አገር ሆኖ ስምሪት የሚሰጣቸውን ግለሰብ ጨምሮ የሚያደረጉትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በጥብቅ ሚስጥር በመከታተል ሃሰተኛ ገንዘብ ለማተም የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ መሣሪያዎች፣ የአሜሪካን ዶላር፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ገንዘብ፣ ድርሃምና የኬንያ ሽልንግ ትክክለኛ ገንዘቦችን ጨምሮ ሰነዶችና ፓስፖርቶች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርገዋል።

@ethiomereja1 ሼር
60 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:57
54 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:57
ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

ሀሰተኛ የኢትዮጵያን የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ ከነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች መካከል ዮሴፍ ተከስተብርሃን እና ተክለብርሃን ገ/መስቀል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታቋል፡፡

ግለሰቦቹ በቡድን በመደራጀት ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን አትመው ሲያሰራጩ መቆየታቸውን የጠቆመው ፖሊስ ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በተደረገባቸው ጥብቅ ክትትልና ድንገተኛ ፍተሻ 40 ሺህ ሃሰተኛ ባለ አንድ መቶ ብር የገንዘብ ኖቶች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር ያልዋለውና የቡድኑ አባል የሆነው ሶስተኛው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ እንደነበረው በፖሊስ ምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ግለሰቡ ለጊዜው ቢሰወርም በደህንነትና በጸጥታ አካላት ክትትል ስር መሆኑን ከፖሊስ ኮሚሽኑየተገኘው አመልክቷል፡፡

@ethiomereja1 ሼር
54 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:57 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ ማከናወን የተራዘመባቸው ክልሎችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ለ6ተኛው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸመ እንደሆነ ይታወቃል።

ቦርዱ በማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ (1) እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 37 ንዑስ አንቀጽ (7) እና አንቀፅ 163 ንዑስ አንቀፅ (2) ላይ በተሰጠው ሥልጣን ባወጣው የዕጩዎች ምዝገባ መመሪያ መሠረት፤ የዕጩዎችን ምዝገባ ለማከናወን የሚያስችሉትን ከክልል መስተዳድሮች እና ከከተማ መስተዳድሮች የሚጠበቁ የትብብር ግዴታዎችን ለሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ገልፆ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደነበር ይታወቃል።

በዚህም መሰረት የክልሎች ዝግጁነት ምን እንደሚመስል ሰኞ የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በመግለጫውም
• አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር
• ጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና
• ሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊ የሆኑትን ለምርጫ ክልል እና ለዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሊያገለግሉ የሚችሉ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዳስታወቁ በመግለጽ፤ በጊዜ ሠሌዳው በተቀመጠው ቀን መሠረት ከየካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩ ምዝገባ የሚከናወነው ከላይ በተጠቀሱት ክልልሎች በሚገኙ የምርጫ ክልል ቢሮዎች መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በቀሪዎቹ ክልሎች የክልል መስተዳድሮቹ ደግሞ አስፈላጊውን ትብብር ሲያደርጉ ምዝገባው የሚጀመርበትን ቀን ቦርዱ የሚያሳውቅ ገልፆ ነበር።

መሆኑን በዚሁ መሠረት እጩ ምዝገባ በማይጀመርባቸው ቀሪ ክልሎቹ የሚካሄዱት የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት እንደሚከተለው ይሆናል፤
• አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት እና
• ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከየካቲት 05 እስከ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ለዕጩዎች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች የሚጓጓዙበትና የዕጩዎች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ሥልጠና የሚሰጥበት ጊዜ ሲሆን፤ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ደግሞ የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ እንዲሆን ቦርዱ ወስኗል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

@ethiomereja1 ሼር
52 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:56
#NewsAlert

በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል ውስጥ 'የከፋ' የአመራር ችግር የታየባቸው አመራሮች ከኃላፊነት ሲነሱ የከፋ አመራር የለባቸውም የተባሉት ደግሞ ሽግሽግ አደረጉ !

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ፥ በቅርቡ የተካሄደውን የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ተከትሎ ህብረ-ብሔራዊነትን በጠበቀ መልኩ አዲስ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ መደረጉን አሳወቀ።

በህዝብ በማስተቸት የከፋ ችግር የታባታቸውን አመራሮች በማንሳት በአዲስ እንዲተኩ በማድረግና የከፋ ችግር የሌለባቸውን ደግሞ በማሸጋሸግ የመተከል ዞንና ወረዳዎች መዋቅር መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ብሏል።

የመተከል ዞን መምሪያ መዋቅር መልሶ ለማደራጀት በተወሰደ እርምጃ የትምህርት መምሪያ ፣ የከተማ ልማት እና የንግድ መምሪያ፣ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ፣ ፍትህ መምሪያ እንዲሁም የውሃ እና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ቦታ ላይ የአመራር አዲስ ምደባና ሽግሽግ ስራ ተሰርቷል ተብሏል።

- የወምበራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

- የቡለን ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

- የድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።

- የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።

- የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

በተመሳሳይ የካቢኔ እና የጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች ላይ የአመራር አዲስ ምደባ እና የማሸጋሸግ ስራ በመስራት መልሶ የማዋቀር ስራ መስራቱ ተገልጿል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@ethiomereja1 ሼር
50 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:55
46 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:55
45 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:12:55
45 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ