Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @breakingnewsethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.92K
የሰርጥ መግለጫ

Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources.
Facebook page link https://m.facebook.com/BreakingNewsEthiopia/?ref=bookmarks

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-01 12:27:44
“መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በአሸባሪው ሕወሓት ላይ የትኛውንም እርምጃ ይወስዳል”
አቶ ደመቀ መኮንን

@BreakingNewsEthiopiaa
2.0K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:42:45
አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሰጡ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች፣ ሚሲዮንና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ማብራሪያ ሰጡ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን አሸባሪው ህወሓት እያደረገ ያለውን ትንኮሳና መንግስት እየወሰደ ያለውን የሰላም ጥረት አብራርተዋል።

መንግስት ጦርነቱን በሰላም ለመፍታት ሲዘጋጅ አሸባሪው ህወሓት ግን ለሌላ ዙር ጦርነት ታዳጊዎችን መልምሎ በማሰልጠን ለጦርነት ሲዘጋጅ ነበር ብለዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ያስቀመጠውን የሰላም አማራጭ ወደጎን በመተው ነሐሴ 18 ሦስተኛ ዙር ጦርነት መጀመሩን ገልጸዋል።

Via FBC

@BreakingNewsEthiopiaa
2.2K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:16:48 አንድ ከሆን በአንድ ከቆምን ማንም አያሸንፈንም ወገን ለሀገራችን አሁን ነው መቆም ያለብን።

በቻልነው ሁሉ ከኢትዮጵያ እናታችን ጎን ልንሆን ይገባል


ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

ፈጣሪ ሐገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን
2.6K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:23:06
ሰበር ዜና

https://www.facebook.com/1853049384808818/posts/pfbid0rezD2GiwdvyrR5R3iuao9fzMGVyedhCGH1Rzi6Q6WA73cxAYfvWDDyFD1E9RtKRgl/

@BreakingNewsEthiopiaa
2.6K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:12:20 ሰበር ዜና pinned « የሰበር ዜና መልዕክት ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሚሳዝነው አሸባሪው ሕውሓት ምንም የማያውቁ ህፃናትና አዛውቶችን ጦር መሳሪያ አስታትቆ ህይወታቸውን መገበሩ ነው። አሁንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መንግስት ያቀረበለትን የሰላም ጥሪ አሻፈረኝ አልቀበልም ያለውን እና ወደ ጦርነት የገባውን ይህን አሸባሪ እየደመሰሰው ይገኛል።፣ በተያያዘ ሕውሓት ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን እየነዛ…»
15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:07:21
የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች፣ መረጃዎችና አሉባልታ አትደናገሩ ብሏል።

ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል።

ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር ግን በዚህም መሃል ሰርገው ሊገቡ የሚችሉ የጥፋት ኃይሎች ካሉ በመከታተል ለሚመለከተው የጸጥታ ኃይል መጠቆም እንደሚገባ አስተዳደሩ ገልጿል።

የባንክና መሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍት ሆነው እየተሰጡ መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት የተሰጠ ሲሆን አገልግሎት በሚያቋርጡና ዋጋ አላግባብ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

በከተማው የታወጀውን አሰገዳጅ ህግ ሁሉም ሊያከብረው የሚገባ ሲሆን ጥሰት የሚታይ ከሆነ አስተዳደሩ ትእግስት እንደማያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ አጥብቆ አስጠንቅቋል።

በሌላ በኩል ፤ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በየመዝናኛ ቤቶችና ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታዎች ላይ አሉባልታ ወሬ በማናፈስ ህብረተሰቡ እንዳይረጋጋ በማድረግ ኗሪው በፍርሃት ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንዳሉ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ይህንን በማወቅ በአሉባልታ ሳይደናገር የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

የከተማው ጸጥታ ማዋቅር የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑንም የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

ወልድያን በተመለከተም ዛሬም #ሰላማዊ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎች ከአሉባልታ በመራቅ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።

@BreakingNewsEthiopiaa
2.6K viewsedited  15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:30:08 የሰበር ዜና መልዕክት

ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

የሚሳዝነው አሸባሪው ሕውሓት ምንም የማያውቁ ህፃናትና አዛውቶችን ጦር መሳሪያ አስታትቆ ህይወታቸውን መገበሩ ነው።

አሁንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መንግስት ያቀረበለትን የሰላም ጥሪ አሻፈረኝ አልቀበልም ያለውን እና ወደ ጦርነት የገባውን ይህን አሸባሪ እየደመሰሰው ይገኛል።፣

በተያያዘ ሕውሓት ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን እየነዛ ህዝቡ እንዲሸበር እያደረገ ስለሚገኝ ጥንቃቄ እናድርግ እንዚህን ከእውነት የራቁ መልዕክቶች Like,share ከማድረግ እንቆጠብ።

ወገን ከሀገራችን ጎን መቆም አለብን

ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን


ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

@BreakingNewsEthiopiaa
2.7K viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:31:45
ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

@BreakingNewsEthiopiaa
1.3K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:24:48 ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ የክልሉን ሕዝብ በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር ተጠቃሚ የሚሆንበትን ወሳኝ ተግባራት አከናውኗል።ይህን ሁኔታ የተረዳው አሸባሪው የሕወሐት ቡድን  የአማራ ሕዝብና መንግሥት የራሱን የመልማት ዐቅም ተጠቅሞ የራሱን ዕድገት የሚያረጋግጥበትን ዕድል ለማጨናገፍ ከመነሻው ዓላማ ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል።

በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመላ ኢትዮጵያ በሚገኘው የአማራ ሕዝብን  ላይ የተጠኑ፤ ተከታታይነት ያላቸው፣ አሰቃቂ ዘር ተኮር ጥቃቶችን፤ ግድያዎችን፤ ዝርፊያና መፈናቀል እንዲደርስበት በማድረግ አማራን ማኅበራዊ ዕረፍት የመንሣት ስልትን ሲከተል ከርሟል፡፡

በዚህ የጥፋትና የእልቂት ድርጊቶቹ ያልተገታው ሽብርተኛው የሕወሐት ቡድን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ክህደት ፈጽሟል።በዚህም  በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ወታደራዊ ጥቃት  አድርሷል።ከዚህም አልፎ  በመልከአ ምድራዊ አቀማመጡም ሆነ በባህላዊና ሃይማኖታዊ መስተጋብሮች የሺ ዓመታት የአብሮነት ታሪክ ባለው የአማራ ክልል ሕዝብ ላይ ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳቶችን አድርሷል።ከ288 ቢልዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መሠረተ ልማቶችና ተቋማትንም አውድሟል፡፡

የክልሉ መንግሥት በአማራ ሕዝብ ላይ የህልውና አደጋ ጋርጠውበት የነበሩትን  እነዚህን ሁሉ ግፎች ለመከላከል ጥረት ከማድረግ በዘለለ ወደለየለት መጠፋፋት እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የተፈጠሩት ግጭቶች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን አማራጮች በማስቀደም ከሁሉም በፊት፤ከምንም በላይ ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ ሽብርተኛው የሕወሐት ቡድን ለሰላም የተከፈተውን በር የጥፋት መናፍስቶቹ ማሹለኪያ በማድረግ በሚፈጽማቸው የጦርነት ትንኮሳዎችና ወረራዎች ስላለፈው የጋራ ታሪካችን እና ስለ መጪው  አንድነት፤ዕድገትና ተስፋችን ስንል ቅድሚያ የሰጠነውን የሰላም ዕድል በተደጋጋሚ አምክኗል፡፡

ዛሬም ቢሆን ለትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የክልላችን አካባቢዎች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ በመፈጸም ከወራት በፊት በክልላችን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ሁለንተናዊ ጥቃት ለመድገም እየተክለፈለፈ ይገኛል፡፡ይህ ጦር ናፋቂ የሽብር ቡድን በንጹሐን ዜጎች፤ በሃይማኖታዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ላይ የፈጸማቸው ጥቃቶች የቡድኑን እውነተኛ ማንነት አጋልጠውታል።በመሆኑ መላው ሰላም ፈላጊ የሰው ዘር እና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሽብር ቡድኑን ሊያወግዝ እና  ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂነት ሊያደርጉት ይገባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሁሉንም ዓይነት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ የሰነቀው ልባዊ መሻት ጽኑ ነው። ነገር ግን በአሸባሪው የሕወሐት ቡድን እምቢተኝነት ምክንያት የሰላም አማራጮች የተዘጉ በመሆናቸው  የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት የማስጠበቅ መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል። 

ስለዚህም  በአሸባሪው የሕወሐት ቡድን የተቃጣበትን ወረራ ለመቀልበስ የሚያስችል አስፈላጊና ተመጣጣኝ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም መላው የአማራ ሕዝብ የክልሉ መንግሥት የሚያቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲጠብቅና ተገቢውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርግ  የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከወዲሁ ያሳስባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ነሐሴ- 21/2014ዓ/ም
ባሕር ዳር

@BreakingNewsEthiopiaa
1.4K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:22:11
#Video

ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

ከ FBC የተወሰደ

@BreakingNewsEthiopiaa
1.7K viewsedited  17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ