Get Mystery Box with random crypto!

የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ | ሰበር ዜና

የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች፣ መረጃዎችና አሉባልታ አትደናገሩ ብሏል።

ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል።

ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር ግን በዚህም መሃል ሰርገው ሊገቡ የሚችሉ የጥፋት ኃይሎች ካሉ በመከታተል ለሚመለከተው የጸጥታ ኃይል መጠቆም እንደሚገባ አስተዳደሩ ገልጿል።

የባንክና መሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍት ሆነው እየተሰጡ መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት የተሰጠ ሲሆን አገልግሎት በሚያቋርጡና ዋጋ አላግባብ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

በከተማው የታወጀውን አሰገዳጅ ህግ ሁሉም ሊያከብረው የሚገባ ሲሆን ጥሰት የሚታይ ከሆነ አስተዳደሩ ትእግስት እንደማያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ አጥብቆ አስጠንቅቋል።

በሌላ በኩል ፤ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በየመዝናኛ ቤቶችና ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታዎች ላይ አሉባልታ ወሬ በማናፈስ ህብረተሰቡ እንዳይረጋጋ በማድረግ ኗሪው በፍርሃት ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንዳሉ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ይህንን በማወቅ በአሉባልታ ሳይደናገር የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

የከተማው ጸጥታ ማዋቅር የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑንም የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

ወልድያን በተመለከተም ዛሬም #ሰላማዊ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎች ከአሉባልታ በመራቅ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።

@BreakingNewsEthiopiaa