Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ breakingnewsethiopiaa — ሰበር ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @breakingnewsethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.92K
የሰርጥ መግለጫ

Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources.
Facebook page link https://m.facebook.com/BreakingNewsEthiopia/?ref=bookmarks

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-24 19:14:43
በቅርቡ ስልጣን የያዙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ሽምቅ ተዋጊውን ቡድን አሸባብን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ ጦርነት ለመክፈት ቃል ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጡት መግለጫ የሶማሊያ ህዝብ የሰላም ጠላት በሆኑት ጨካኞች ላይ ለሚካሄድ አጠቃላይ ጦርነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።የሶማሌ ህዝብ ማብቂያ በሌለው የሀዘን መግለጫና ሀዘን መሰላቸቱን አውቃለሁ ያሉት ፕሬዝዳንቱ አሸባሪው ቡድን በሚፈጽመው በእያንዳንዱ ግድያ እጅግ የተከበሩ ሰዎች እንደሚሞቱም አስታውሰዋል። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያው የተባለው የአሸባብ ከባድ ጥቃት ባለፈው አርብ በዋና ከተማይቱ መቅዲሾ በሚገኘው በሃያት ሆቴል ውስጥ ደርሷል።

በዚሁ የጠመንጃና የቦምብ ጥቃትም 21 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 117 ደግሞ ቆስለዋል። ከሟቾቹ መካከል የኖርዌይ ዜጎች እንደሚገኙበት የኖርዌይ መንግሥት አስታውቋል።የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙበትን የብሔራዊ የፀጥታ ኮሚቴ ስብሰባ ትናንት ያካሄዱት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ በመግለጫቸው «ህዝባችንን የሚያጠፉት አሸባሪዎች የሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ነጻ እስኪወጡ ድረስ ቡድኑን ለማዳከም ቆርጠን ተነስተናል»ብለዋል።ይህም መንግሥታቸው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ የእቅዱ ዝግጅትና አተገባበሩ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

[DW]
@BreakingNewsEthiopiaa
3.2K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 16:33:44 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ተነገረ

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናውን እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱንም ገልፀዋል። ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

[Addis Zeybe]
@BreakingNewsEthiopiaa
3.5K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 13:31:58 አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ 800 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጸደቀች

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሩሲያ ጋር ቀጥታ ጦርነት ውስጥ ላለችው ዩክሬን ተጨማሪ 800 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ፈርመዋል።

አሜሪካ የጦር መሳሪያውን ድጋፍ ያደረገችው ዩክሬን የኑክሌር ጥቃት ከሩሲያ ሊያጋጥማት ይችላል በሚል እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 176ኛ ቀኑ ላይ ሲገኝ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።

@BreakingNewsEthiopiaa
5.2K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ