Get Mystery Box with random crypto!

በቅርቡ ስልጣን የያዙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ሽምቅ ተዋጊውን ቡድን አሸባብን ለ | ሰበር ዜና

በቅርቡ ስልጣን የያዙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ሽምቅ ተዋጊውን ቡድን አሸባብን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ ጦርነት ለመክፈት ቃል ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጡት መግለጫ የሶማሊያ ህዝብ የሰላም ጠላት በሆኑት ጨካኞች ላይ ለሚካሄድ አጠቃላይ ጦርነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።የሶማሌ ህዝብ ማብቂያ በሌለው የሀዘን መግለጫና ሀዘን መሰላቸቱን አውቃለሁ ያሉት ፕሬዝዳንቱ አሸባሪው ቡድን በሚፈጽመው በእያንዳንዱ ግድያ እጅግ የተከበሩ ሰዎች እንደሚሞቱም አስታውሰዋል። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያው የተባለው የአሸባብ ከባድ ጥቃት ባለፈው አርብ በዋና ከተማይቱ መቅዲሾ በሚገኘው በሃያት ሆቴል ውስጥ ደርሷል።

በዚሁ የጠመንጃና የቦምብ ጥቃትም 21 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 117 ደግሞ ቆስለዋል። ከሟቾቹ መካከል የኖርዌይ ዜጎች እንደሚገኙበት የኖርዌይ መንግሥት አስታውቋል።የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙበትን የብሔራዊ የፀጥታ ኮሚቴ ስብሰባ ትናንት ያካሄዱት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ በመግለጫቸው «ህዝባችንን የሚያጠፉት አሸባሪዎች የሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ነጻ እስኪወጡ ድረስ ቡድኑን ለማዳከም ቆርጠን ተነስተናል»ብለዋል።ይህም መንግሥታቸው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ የእቅዱ ዝግጅትና አተገባበሩ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

[DW]
@BreakingNewsEthiopiaa