Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ የሚደረጉ በረራዎችን አገደች የበረራ እገዳው ለአንድ ወር ገደማ ይቆያል | ሰበር ዜና

አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ የሚደረጉ በረራዎችን አገደች

የበረራ እገዳው ለአንድ ወር ገደማ ይቆያል ተብሏል
አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ የሚደረጉ በረራዎችን ላይ እገዳ መጣሏ ተሰምቷል።

ከዚህ በፊት በንግድ አሁን ደግሞ በታይዋን ጉዳይ መካረር ውስጥ የገቡት አሜሪካ እና ቻይና ሌላ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።
ቻይና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብሯን አቋረጠች

ቻይና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተወሰኑ የአሜሪካ አየር መንገዶች ላይ የጉዞ እገዳዎች አስተላልፋ ነበር። አሜሪካም ለዚህ እገዳ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች ሲሆን 26 በረራዎች ከቻይና ወደ አሜሪካ እንዳይደረጉ እገዳ ጥላለች።
እገዳ ከተጣለባቸው አየር መንገዶች መካከልም ሺያሜን፣ ኤየር ቻይና፣ ሳውዘርን ቻይና እና ቻይና ኢስተርን ዋነኞቹ ናቸው ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

እንደ አሜሪካ ትራንስፖርት ዲፓርትመንት መግለጫ ከሆነ በቻይን ላይ የተጣለው የበረራ እገዳ ከፈረንጆቹ መስከረም አምስት እስከ 28 ባሉት 23 ቀናት ነው።
ሰባቱ በረራዎች ከቻይና ወደ ኒዮርክ፣ 19ኙ በረራዎች ደግሞ ወደ ሎስ አንጀለስ ሊደረጉ ታስበው እንደነበርም ተጠቅሷል።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@BreakingNewsEthiopiaa