Get Mystery Box with random crypto!

ተርኪዬ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ማርች 24 /2022 በፌዴራል መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁ | ሰበር ዜና

ተርኪዬ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ማርች 24 /2022 በፌዴራል መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ከታወጀ በኃላ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶችን በሀዘን እና ስጋት ውስጥ ሆና እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልፃለች።

ሁሉም ወገኖች ግጭት በዘላቂነት እንዲቆም ለማድረግ እና በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ወደ ንግግር እንዲመለሱ ጋብዛለች።

ለዚህ አላማ ደግሞ ሁሉንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጣለች።

ተርኪዬ በኢትዮጵያ ሰላምን እና መረጋጋትን ለማስፈን ባሚደረገውን ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፃለች።

በሌላ በኩል ፤ ዩናይትድ ኪንግደም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶች እንደሚያሳስባት ገልፃለች።

ይህ ሁኔታ ቀድሞም አስከፊ የነበረውን የሰብዓዊ ሁኔታ ይበልጥ ያባብሰዋል ብላለች።

ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ግጭት እንዲያቆሙና የፖለቲካ መፍትሄ እንዲመጣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ አሳስባለች።

@BreakingNewsEthiopiaa