Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Media Corporation

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharamassmedia — Amhara Media Corporation A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharamassmedia — Amhara Media Corporation
የሰርጥ አድራሻ: @amharamassmedia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 64.60K
የሰርጥ መግለጫ

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-04 15:33:50 https://www.amharaweb.com/?p=36630
የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
6.2K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 12:30:31
"የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ዛሬ ከሰዓት በኃላ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መራሔ መንግሥቱ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ለ3 ቀናት እንደሚቆዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በሳምንታዊ መግለጫቸው እንዳሉት ኦላፍ ሾልስ አዲስ አበባ ሲመጡ በጀርመን እና በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መራሔ መንግሥቱ አዲስ አበባ የሚመጡት በርካታ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቡድን ይዘው በመኾኑ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚም ትልቅ ሚና ያለው ነው ተብሏል።

በሚቀጥለው ሳምንትም የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ እንደሚመጡም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
7.4K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:51:00
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አኹናዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ መገምገማቸውን ገለጹ።

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ዛሬ ጠዋት በማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው በኩል አኹናዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ ገምግመናል ፤የወደፊት ተግባራትንም ለይተናል“ ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
7.5K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 18:38:56 https://www.amharaweb.com/%e1%89%a0%e1%8a%a9%e1%88%ad-%e1%8c%8b%e1%8b%9c%e1%8c%a3-%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%8b%9d%e1%8b%ab-23-2015-%e1%8b%93-%e1%88%9d-%e1%8b%95%e1%89%b5%e1%88%9d/
9.3K viewsedited  15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 17:00:54 የታንዛኒያውን ድርድር እና ሌሎች ዜናዎችን አካተናል



9.5K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 13:36:20
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ ተጠናቋል።

ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም።

ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ ተግባብተዋል።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና እስካሁን ሲመራባቸው በነበሩ መሠረታዊ መርሖች መሠረት ግጭቱን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት መንግስት የጸና አቋም አለው።

ይህንን መልካም አጋጣሚና በውይይት ችግሮችን የመፍታት በጎ ጅምር በመጠቀም ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ፅኑ አቋም ዳግም ያረጋግጣል።

የሰላም ውይይቱን ላመቻቹና ላስተናገዱ አካላት የኢፌዴሪ መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
10.1K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 11:00:58
አቶ ደመቀ ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቡራክ አክሰፐር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል ባለው የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

በቀጣናዊና ሌሎች መድረኮች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ቡራክ ቱርክ በቅርቡ በገጠማት የርዕደ መሬት አደጋ ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ እና ላሳየችው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሱዳን የነበሩ ዜጎችንም እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያ ለተጫወተችው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

ሁለቱ አካላት በሱዳን ያለው ግጭት ረግቦ ሁለቱ ተፋላሚ አካላት ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያላቸውን መልካም ምኞትም ገልፀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
9.5K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 10:53:05
በሰው የመነገድ ወንጀልን በመከላከል ብሩህ ኢትዮጵያን እንፍጠር በሚል ርእሰ ጉዳይ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የውይይት መድረኩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የብሔራዊ ትብብር ጥምረት እና በፍሪደም ፈንድ ትብብር የተዘጋጀ ነዉ ።

በመድረኩ ላይ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በቅድሚያ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ እየተሠራ እንደሆነ ተነግሯል። በተለይም መንግሥት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነት በመፈጸም ዜጎች በሕገ ወጥ መንገድ እንግልት እንዳይደርስባቸው እየተሠራ መሆኑ ተመላክቷል።

የውይይት መድረኩን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ገረመው ገብረፃዲቅ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ያስጀመሩት ሲሆን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች እያሳዩ ያሉትን ቅንጅታዊ አሠራር ዕውቅና ሰጥተዋል።

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት እያደገ ቢመጣም አሁንም ድረስ ወንጀሉ እየጨመረ መምጣቱን ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ጠቅሰው ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሀገር ውስጥ ወጣቶችንና ከስደት ተመላሾችን የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- ተስፋ ሞላ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
9.3K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 21:23:00 https://youtube.com/live/ulxiTyWFoJI?feature=share
10.2K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 16:31:56 ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች ወደቤታቸው መመለስ እና ሌሎች ዜናዎችን አካተናል



11.7K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ