Get Mystery Box with random crypto!

'የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ዛሬ ከሰዓት በኃላ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡' የውጭ ጉዳይ ሚ | Amhara Media Corporation

"የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ዛሬ ከሰዓት በኃላ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መራሔ መንግሥቱ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ለ3 ቀናት እንደሚቆዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በሳምንታዊ መግለጫቸው እንዳሉት ኦላፍ ሾልስ አዲስ አበባ ሲመጡ በጀርመን እና በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መራሔ መንግሥቱ አዲስ አበባ የሚመጡት በርካታ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቡድን ይዘው በመኾኑ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚም ትልቅ ሚና ያለው ነው ተብሏል።

በሚቀጥለው ሳምንትም የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ እንደሚመጡም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck