2023-04-28 11:03:17
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሐዘን ገለጸ።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል፡፡
እኩልነትና ማኅበራዊ ፍትሕ የነገሰባት ጠንካራ ኅብረብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ አቶ ግርማ የተሰጣቸው ታላቅ ሕዝባዊ፣ ደርጅታዊና መንግስታዊ ኃላፊነት በልበሙሉነት፣ በትጋትና በኃላፊነት ስሜት የተወጡ ናቸው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
አቶ ግርማ የሺጥላ ሀገር ወዳድ፣ ብልህ ቁርጠኛ የፖለቲካ አመራር እንደነበሩ ገልጾ ለሀገርና ለወገን ሲሉ ሙሉ ጊዜያቸውን በመጨረሻም የማይተካውን ውድ ሕይወታቸውን ሰውተዋል ብሏል፡፡
የአቶ ግርማ ጉልህ ሀገራዊና መንግሥታዊ አበርክቶ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ማኅደር ፈፅሞ የሚዘነጋ አይሆንም ነው ያለው ምክር ቤቱ በሐዘን መግለጫው፡፡
ምክር ቤቱ በአቶ ግርማ የሺጥላና በግል ጠባቂዎቻቸው ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለወገኖቻችን ሞት ምክንያት የሆነውንም አሳፋሪ ፅንፈኛ ድርጊትና ጥቃት በፅኑ አውግዟል፡፡
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸውም መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
9.7K views08:03