2023-05-01 14:57:44
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር አካል የኾነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ::
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፍተዋል።
በምርቃቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርእሳነ-መሥተዳድሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ሪዞርቱ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።
የፕሮጀክቱ ግንባታም የአካባቢው ማኅበረሰብ ነባር የኪነ-ሕንጻ ጥበብን ከዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገልጿል።
በውስጡም ፕሬዝዳንታዊ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ዘመናዊ መኝታ ክፍሎች እና ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎችን የያዘ ነው።
ሪዞርቱ በተገነባበት ስፍራ የሚገኘው የጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ሰው ሠራሽ ሐይቅም በውሃ ላይ መዝናናት ለሚፈልጉ ጎብኝዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ መዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል።
በተጨማሪም ቀደምት የዳውሮ ንጉስ ሃላላ የተገነባው የሃላላ ድንጋይ ካብ (ሃላላ ኬላ) ታሪካዊነቱን እንደጠበቀ በስፍራው ተጨማሪ የመስህብ አካል በመሆን ያገለግላል።
የሪዞርቱ መገንባትም ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
6.6K views11:57