Get Mystery Box with random crypto!

በሰው የመነገድ ወንጀልን በመከላከል ብሩህ ኢትዮጵያን እንፍጠር በሚል ርእሰ ጉዳይ የውይይት መድረክ | Amhara Media Corporation

በሰው የመነገድ ወንጀልን በመከላከል ብሩህ ኢትዮጵያን እንፍጠር በሚል ርእሰ ጉዳይ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የውይይት መድረኩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የብሔራዊ ትብብር ጥምረት እና በፍሪደም ፈንድ ትብብር የተዘጋጀ ነዉ ።

በመድረኩ ላይ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በቅድሚያ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ እየተሠራ እንደሆነ ተነግሯል። በተለይም መንግሥት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነት በመፈጸም ዜጎች በሕገ ወጥ መንገድ እንግልት እንዳይደርስባቸው እየተሠራ መሆኑ ተመላክቷል።

የውይይት መድረኩን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ገረመው ገብረፃዲቅ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ያስጀመሩት ሲሆን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች እያሳዩ ያሉትን ቅንጅታዊ አሠራር ዕውቅና ሰጥተዋል።

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት እያደገ ቢመጣም አሁንም ድረስ ወንጀሉ እየጨመረ መምጣቱን ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ጠቅሰው ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሀገር ውስጥ ወጣቶችንና ከስደት ተመላሾችን የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- ተስፋ ሞላ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!