Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Media Corporation

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharamassmedia — Amhara Media Corporation A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharamassmedia — Amhara Media Corporation
የሰርጥ አድራሻ: @amharamassmedia
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 64.60K
የሰርጥ መግለጫ

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-17 12:30:48 የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማሪታይም አካዳሚ ለ21ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 119 መርከበኞች አስመረቀ፡፡

ባሕር ዳር ፡ ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማሪታይም አካዳሚ ለ21ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 119 መርከበኞች አስመርቋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተስፋየ ሽፈራው (ዶ.ር) አካዳሚው ከዚህ በፊት ሜካኒካል ኢንጅነሮችን ብቻ ያሰለጥን እንደነበር ጠቅሰዋል። በዚህ ዙር ስልጠና ግን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሰልጣኞችን አካቶ አስመርቋል ብለዋል።

በጣና ሐይቅ ላይ ልምምድ አድርገው ወደ ዓለም አቀፉ የመርከብ ቢዝነስ የሚቀላቀሉ ተመራቂዎች በሄዱበት ሁሉ በሥነ ምግባር እና በተግባቦት በመሥራት ሀገራቸውን እንዲያስመሰግኑ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ማሪታይም አካዳሚ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ፍራንስ ጆበርት በበኩላቸው የዛሬ ተመራቂዎች በየትኛውም ዓለም ተጉዘው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘው ስለመውጣታቸው ተናግረዋል።

ተመራቂዎች ወደ አዲስ ሀገር እና ሕዝብ ሲቀላቀሉ ቤተሰብ፣ ሀገር እና የኢትዮጵያ ጣፋጭ ምግቦች ሳይቀሩ እንደሚናፍቋቸው የገለጹት ፍራንስ ጆበርት ይህንን በትዕግስት በማለፍ ኢትዮጽያዊ ጀግንነት እንዲፈጽሙ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሀገራቸውን ሳይረሱ ጠንክረው በመሥራት የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ማሻሻል እንዳለባቸውም መክረዋል።

ተመራቂዎች ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት በሚኖራቸው የሥራ ስምሪት ሀገር እና ሰንደቅ ዓላማቸውን የሚያስከብር ተግባር የሚፈጽሙ እንደሚኾኑም አመላክተዋል።

ከተመራቂዎች መካከል መርከበኛ ሄኖክ ገበያ ለትምህርቱ ከፍተኛ ፍላጎት ይዞ በመግባቱ የላቀ ውጤት አስመዝግቦ ነው የተመረቀው። በኤሌክትሮ ቴክኒካል ኦፊሰርነት እንደተመረቀ ነግሮናል። ስልጠናው ከዕውቀት በተጨማሪ በሥነ ምግባር እና በሌሎች ክህሎቶችም ታንጾ ለመውጣት አስችሎኛል ብሏል። በተመደበበት ቦታ ሁሉ የሀገሩን ስም እና ክብር በጠበቀ መልኩ እንደሚሠራም ገልጿል።

ሌላው ተመራቂ መርከበኛ ይዲዲያ አዲስ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ መምህራን ጥራት ያለው ትምህርት ማግኘቱን ተናግሯል። ከዕውቀት በተጨማሪ የተሻለ አካላዊ ቁመና እና ስብዕና ይዞ ለመውጣት እንደቻለም ገልጿል። ያገኘውን ዕውቀት እና ክህሎት ወደ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይዞ በመግባት ራሱን፣ ቤተሰቦቹን እና ሀገሩን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥራ እንደሚያከናውን ተናግሯል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
6.3K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:29:01 የክልሉን ወቅታዊ ችግሮች እና የሕዝብን ጥያቄዎች መሠረት ያደረገ የአመራር ኮንፈረንስ ማዘጋጀቱን የአማራ ክልል ብልጽግና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር ፡ ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን” በሚል መሪ ሃሳብ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ከ1 ሺህ 400 በላይ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ኮንፈረንሱ ከግንቦት 10/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኅላፊ ዶክተር ጋሻው አወቀ ገልጸዋል፡፡

የኮንፈረንሱ ዓላማ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና ችግሮችን በመገምገም ጠንካራ ፓርቲ እና መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ጽናት እና የጋራ መግባባት መፍጠር ነው ያሉት ዶክተር ጋሻው የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ትግል እና መተማመን ከኮንፈረንሱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ብልጽግና እንደ ማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ በውስብስብ ችግሮች ውስጥ አልፎ የመጣ ነው፤ አሁናዊ ፈተናዎችን በሚገባ ገምግሞ እና አርሞ ለላቀ ተልዕኮ ራሱን ያዘጋጃል ብለዋል፡፡

ኮንፈረንሱ በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተደርገዋል ያሉት ዶክተር ጋሻው ከኮንፈረንሱ ኅይል የሚያሰባስብ ሠላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የሃሳብ ትግል ይካሄድበታል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ኮንፈረንሱ የክልሉን ወቅታዊ ችግሮች እና የሕዝብን ጥያቄ መሠረት ያደረገ በመሆኑ የሚጠበቁ ግቦች ይኖራሉም ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
6.3K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:28:59
6.2K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 10:25:45
የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ጁባ ገባ

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ልዑኩ ጁባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ አቀባበል አድርገውለታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ በደቡብ ሱዳን በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለመው ላፕሴት ፕሮጀክት አስመልክቶ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደሚሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

የላፕሴት ፕሮጀክት እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳን ሀገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ሥራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
7.8K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 09:46:09
7.7K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 11:38:56
1.7K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 09:48:58
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ)አንጋፋዋ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ባደረባት ህመም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በህክምና ስትረዳ ቆይታ ሕይወቷ ማለፉን ፋናቢሲ ቤተሰቦቿን ጠቅሶ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
3.3K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 19:11:13
ምሽት 1:00 ትዕይንተ ዜና ባሕር ዳር: ግንቦት 03 /2015 ዓ.ም (አሚኮ)
https://www.youtube.com/live/SdlPMXVmKls?feature=share
6.4K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 17:27:52 በአዲሱ አደረጃጀት የተካተቱ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት እና ሌሎች መረጃዎችን አካተናል



7.3K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:29:25
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ።

ባሕር ዳር: ግንቦት 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ተቀብለው አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛውን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታውቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
7.3K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ