2023-06-06 10:55:54
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዜጎች ምክክር ሊደረግባቸው ይገባል የሚሉትን ጉዳዮች እንዲጠቁሙ ጠየቀ።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዜጎች እንደ ሀገር ምክክር ሊደረግባቸው ይገባል ብለው የሚያምኑባቸውን ጉዳዮች እንዲጠቁሙና ለዚህ ሀገራዊ ጉዳይ በንቃት አንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።
ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 0111261196 ፤ 0975554500፣ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 32623፣ በኢ-ሜይል አድራሻ ethiopianndc@gmail.com ጉዳያቸውን እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል።
የኮሚሽኑ በስልክ፣ በፖስታ፣ በኢ-ሜይልና አዲስ አበባ ሽሮሜዳ አከባቢ በሚገኘው ቢሮው በአካል በመቅረብ አጀንዳቸውን እያቀረቡ ያሉ ዜጎች መኖራቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
6.9K views07:55