Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ጁባ | Amhara Media Corporation

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ጁባ ገባ

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ልዑኩ ጁባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ አቀባበል አድርገውለታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ በደቡብ ሱዳን በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለመው ላፕሴት ፕሮጀክት አስመልክቶ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደሚሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

የላፕሴት ፕሮጀክት እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳን ሀገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ሥራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck