Get Mystery Box with random crypto!

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የሰርጥ አድራሻ: @alainamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 69.32K
የሰርጥ መግለጫ

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-29 06:45:08
በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ ለአእምሯችን የሚሰጣቸው ጥቅሞች…

ተመራማሪዎች በቀን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችንን አቅም ለማሳገድ እንደሚረዳ አስታወቁ።

አዲስ የተሰራ የኒውሮሳይንስ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችን አዲስ መረጃ ለመውሰድና ለመያዝ እንዲዘጋጅ ያደርገዋል።

በተለይም ውሳኔ ለመስጠት፣ ጭንቀትን ለመቆጣጠርና፣ በባህሪያችን ዙሪያ የሚያቅደው የአእምሯችን ክፍል ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ነው ተመራማሪዎች ያስታወቁት።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Wiai28
13.1K views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 04:30:22
በቱርክ የ1 ሺህ 800 ዓመት እስር የተፈረደባት አህላም አልባሽር

የቱርክ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የፍርድ ትዕዛዝ የሽብር ወንጀል ፈጽማለች ያላትን አንድ ተከሳሽ በ1 ሺህ 800 ዓመት እስር እንድትቀጣ ወስኗል።

እንደ ቱርክ ብዙሃን መገናኛዎች ዘገባ ከሆነ ተከሳሿ ከሁለት ዓመት በፊት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ኢስታምቡል ልዩ ቦታው ኢስቲክላል በተሰኘ ስፍራ የተፈጸመውን የሽብር ትቃት አቀነባብራለች ተብሏል።

በዚህ የሽብር ጥቃት ምክንያት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ማጉደል አደጋ እንዳጋጠማቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4aTusEm
13.3K views01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 02:32:01
ጋናዊው ግለሰብ ከ1 ሺህ 100 በላይ ዛፎችን በማቀፍ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ

የተፈጥሮ ጉዳዮች ማህበራዊ አንቂ እና የስነ ደን ተማሪ የሆነው ጋናዊው አቡበከር ታሂሩ በአንድ ሰዓት ውስጥ በርካታ ዛፎችን በማቀፍ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

አቡበከር ታሂሩ የተባለው የ29 ዓመቱ ጋናዊ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአጠቃላይ 1 ሺህ 123 ዛፎችን ያቀፈ ሲሆን፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥም በአማካይ 19 ዛፎችን ማቀፍ ማቸሉ ነው የተነገረው።

አቡበከር ስለ ዛፍ ማቀፍ ክብረ ወሰኑ ሲናገር፤ “በጣም ከባዱ ነገር በዛፎቹ መካከል የሚደረገው ምልልስ እንዲሁም እያንዳንዱ ዛፍ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት መታቀፉን ማረጋገጥ ነበር” ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3JImO3q
12.8K views23:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 23:21:59 ህብረቱ ሁለቱ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው ቦታዎች ያለው የንጹሃን መፈናቀል እንዲቆም ጠይቋል

የአማራ እና የትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ እና አካባቢዋ ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት መግለጫ አውጥቷል።

መግለጫው የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በአወዛጋቢዎቹ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፎላ "በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ያሉ ውጥረቶችን" በትኩረት እየተከታተሉት መሆኑን ገልጿል።

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረሰው የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የዘላቂ ሰላም ስምምነት፣ ሁለቱ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው "አወዛጋቢ ቦታዎች" በህገመንግስቱ መሰረት እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይጠቅሳል።

ሊቀመንበሩ ሁለቱም ወገኖች ግጭት ከማባባስ እንዲታቀቡ እና የአካባቢውን ንጹሃን መፈናቀል እንዲያስቆሙ ጥሪ አቅርዋል።
https://bit.ly/3Wc5L1m
14.4K views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 20:38:50
ቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠራች

ለቻይና በመሰለል ተጠርጥረው በርካቶች ጀርመን ውስጥ መታሰራቸውን ተከትሎ ቤጂንግ በቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠርታለች።

ሮይተርስ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው በበርሊን የሚገኙት የቻይና አምባሳደር ተጠርተው ቻይና እያደረገችው ነው በተባለው የስለላ ተግባር ዙሪያ እየተካሄደ ስላለው ምርመራ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ባለፈው ማክሰኞ በአውሮፓ ህብረት ጀርመንን በመወከል አባል የሆኑት ማክሲሚላን ራህ ረዳት ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለቻይና በመሰለል ተጠርጥሮ ጀርመን ውስጥ ታስሯል።

አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ የተያዘው ግለሰብ ጂያን ጉኦ እንደሚባል እና በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውስጥ ስለተደረጉ ውይይቶች ለቻይና ደህንነት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ እንደነበር ገሎጿል።

በሳምንቱ መጀመሪያ ደግሞ ሶስት ጀርመናውያን ለወታራዊ ስለላ ጥቅም ላይ ይውላል የተባለ መተግበሪያ አሳልፈው በመስጠት ተጥርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
15.0K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 19:23:30 ከተገደለችው እናቷ ማህጸን በህይወት የወጣችው ህጻን ህይወቷ አለፈ

በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደለችው እናቷ ማህፈን በህይወት የወጣችው የጋዛዋ ህጻን የተወሰነ ቀናት ከቆነች በኋላ ህይወቷ ማለፉን ዶክተሩ ተናግረዋል።
https://bit.ly/44fVx22
15.0K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 17:23:53 የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ


የዩንቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በስራ ላይ ከታዩ አንድ ወር እንዳለፋቸው ተቋሙ ገልጿል


ትምህርት ሚንስቴር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ተቋማት ስለ ጉዳዩ ከመናገር ተቆጥበዋል


ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3QjgLWS
16.1K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 16:47:19 በአወዛጋቢዎቹ የራያ አካባቢዎች ግጭት መከሰቱን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት መግለጫ አወጣ

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረሰው የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የዘላቂ ሰላም ስምምነት፣ ሁለቱ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው "አወዛጋቢ ቦታዎች" በህገመንግስቱ መሰረት እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይጠቅሳል።
https://bit.ly/3Wc5L1m
15.3K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 16:47:03 በ58 ዓመቱ ወደ ኳስ የተመለሰው ሮማሪዮ

ብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሮማሪዮ በ58 ዓመቱ ወደ እግር ኳስ ጨዋታ አስታውቋል።
ከ15 ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ እግር ኳስ የተመለሰው ሮማሪዮ፤ ከአዲሱ ክለቡ የብራዚሉ አሜሪካ የእግር ኳስ ክለብ ጋርም ልምምድ አድርጓል።
ቪዲዮውን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤

14.8K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 14:08:52 በጋዛ ሆስፒታሎች የተገኙት ጅምላ መቃብሮች ምርመራ እንዲደረግባቸው የፍልስጤም ባለስልጣናት ጠየቁ

ቡድኑ እንደገለጸው የእስራኤል ወታደሮች ቦታውን ለቀው ከወጡ በኋላ በሆስፒታሎቹ አጥር ግቢ ውስጥ 400 ሰዎች የተቀበሩባቸው ጅምላ መቃብሮች ተገኝተዋል።
https://bit.ly/44e4Bo5
15.5K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ