2024-04-22 16:39:17
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ፓኪስታን ገቡ።
ፕሬዝዳንት ራይሲ ከፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ ጋር ባደረጉት ምክክር የቴህራን እና ኢስላማባድን አመታው የንግድ ልውውጥ 10 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ተስማምተዋል።
ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል የተስማሙት መሪዎቹ በጋዛ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም መጠየቃቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።
900 ኪሎሜትር ድንበር የሚጋሩት ፓኪስታን እና ኢራን በጥር ወር 2024 አንዱ የሌላኛውን የአየር ክልል በመጣስ የፈጸሟቸው ጥቃቶች ግንኙነታቸውን ማሻከሩ የሚታወስ ነው።
ግንኙነቱን ለማደስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር ኢስላማባድ የገቡት ፕሬዝዳንት ራይሲ በላሆር እና ካራቺ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተዘግቧል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
13.9K views13:39