Get Mystery Box with random crypto!

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የሰርጥ አድራሻ: @alainamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 69.32K
የሰርጥ መግለጫ

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-05-09 19:00:15 1 ሺህ የማራቶን ውድድሮችን ያጠናቀቁት እንግሊዛዊ ክብረወሰን ሰበሩ

ለ43 አመታት ማራቶን የሮጡት የ61 አመቱ አዛውንት ውድድሩን ያጠናቀቁበት አማካይ ጊዜ በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ እንዲሰፍሩ አድርጓቸዋል።

https://bit.ly/4bNQMiT
14.8K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 16:56:32 የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በቱርክ እና ሴኔጋል አደጋ አጋጠማቸው

በሴኔጋል መዲና ዳካር በማረፍ ላይ እያለ ባጋጠመው የቴክኒክ አደጋ 11 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል

በቱርክ ደግሞ በማረፍ ላይ እያለ ጎማው እንደወለቀ ሲገለጽ በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት አላደረሰም

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/44zf916
15.6K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 15:28:37 “ማንም እንዲያስፈራራን አንፈቅድም” - ፑቲን

የምዕራባውያን “እብሪተኝነት” ቢቀጥልም ሩሲያ አለማቀፍ ግጭትን ለማስቀረት የትኛውንም እርምጃ ትወስዳለች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።

https://bit.ly/4bxYcXl
15.4K views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 10:59:08 አስትራዘኔካ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመላው አለም ሊሰበስብ መሆኑን አስታወቀ

ኩባንያው ክትባቱን ለመሰብሰብ ያመለከተው ከሁለት ወራት በፊት ቢሆንም ተቀባይነት ያገኘው ግን በትናንትናው እለት ነው
https://bit.ly/3UQggGB
12.8K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 10:03:37 አሜሪካ ወደ እስራኤል ቦምብ መላክ አቆመች

የእስራኤል የራፋህ የምድር ውጊያ እቅድ ንጹሃንን በመጠበቅ ረገድ የአሜሪካን ስጋት የሚመልስ ሆኖ አልተገኘም ተብሏል።

https://bit.ly/4btqeTD
12.8K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 08:14:58
ለፈተና አይበገሬዋ ሚስት ለ10 አመት ኮማ ውስጥ የቆየ ባሏ ሲነቃ ተመልክታለች

በምስራቃዊ ቻይና አንሁይ በተባለችው ግዛት ነዋሪ የሆነችው ሰን ሆንግሻይ ባሏ በ2014 በገጠመው ድንገተኛ የልብ ድካም ኮማ ውስጥ ይገባል።

በአጭር ጊዜ ከኮማ ይወጣል፤ የቤተሰቡም ስጋት ይወገዳል ተብሎ ቢጠበቅም ምን እየተካሄደ እንደሆነ በውል መረዳትና መግለጽ የማይችለው ባል 10 አመታት ኮማ ውስጥ ይቆያል።

ከሰሞኑ ግን ሰን ለድፍን አስር አመታት በተስፋ የጠበቀችው፤ በብዙ የደከመችለት ጉዳይ ፍሬ አፍርቶ የምትወደውና የሁለት ልጆቿ አባት ነቅቷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3wfeJk1
13.4K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 06:44:58
አውስትራሊያን ያበሳጨው የቻይና ተግባር ምንድን ነው?

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ፤ የቻይና የጦር ጄቶች የሀገሪቱን ሄሊኮፕተር ማዋከባቸውን ተከትሎ ተግባሩን “ተቀባይነት የሌለው” ሲሊ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃውማቸውን ያሰሙት የቻይና ጦር ጄቶች በዓለም አቀፉ የውሃ ክልል ላይ በማለፍ ላይ የነበሩ የአውስትራሊያ ሄሊኮፕተሮች ላይ ሆን ብለው እሳት ለቀዋል የሚል ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ ነው።

የቻይና ጦር ጄቶች የአውስትራሊያ ባህር ኃይል ሄሊኮፕተርን አዋክበዋል ነው የተባለው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/australian-pm-criticises-china
13.2K views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 04:29:58
“ሩሲያውያን በአንድነት በመሆን ማንኛውንም መሰናክል እናልፋልን” - ፕሬዝዳንት ፑቲን

ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ፕሬዝዳንት በመሆን በዛሬው እለት ለአምስተኛ የስልጣን ዘመን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግርም፤ “እኛ ሩሲያውያን ህብረት ያለን እና ታላቅ ህዝብ ነን” ያሉት የፕሬዝዳንት ፑቲን፤ “በአንድነት በመሆን ማንኛውንም መሰናክል እናልፋልን” ሲሉም ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን አከለውም መላው ሩሲያውያንን እንዲሁም ለዓባት ሀገራቸው በጦር ግንባር እየተዋደቁ ያሉ ሩሲያውያን ወታደሮችንም አመስግነዋ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3UMwUa3
12.7K views01:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 02:32:58
ባየርሙኒክ የማንቸስተር ዩናትድ አሰልጣን ቴን ሃግን ለመቅጠር ማሰቡ ተነገረ

የጀርመኑ ባየርሙኒክ የማንቸስተር ዩናይትዱን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የቶማስ ቱኸል ተተኪ ለማድረግ ማቀዱ ተነገረ።
የቡንደስሊጋው ክለብ ከሆላንዳዊው አሰልጣኝ ወኪል ኪስ ቮስ ጋር መነጋገሩ ተዘግቧል።

ባየርሙኒክ ከቴን ሀግ ጋር እስካሁን በቀጥታ ይፋዊ ንግግር አልጀመረም ቢባልም የባቫሪያኑ ክለብ አይኑን እንደጣለባቸው አውቀዋል ይላል ዘገባው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/44DCK0Q
12.7K views23:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 23:34:58
አሜሪካዊው ወታደር ሩሲያ ውስጥ በስርቆት ወንጀል ተጠርጥሮ መታሰሩ ተገለጸ

የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተከሰሰው የአሜሪካ ወታደር ሩሲያ ውስጥ በታሰሩን የአሜሪካ ጦር በትናንትናው እለት አስታውቋል።

የሩሲያውን ጋዜጣ ኢዝቨስቲያን እንደዘገበው በደቡብ ኮሪያ መቀመጫውን አድርጎ የነበረው ይህ ወታደር በሩሲያ የሩቅ ምስራቅ ወደብ ቭላድቮስቶክ ከምትኖር ሩሲያዊት ሴት ጋር በኢንተርኔት አማካኝነት ተዋውቋል።

ጥንዶቹ አበረው መኖር ከጀመሩ በኋላ ወታደሩ በጥፊ መትቶ 2200 ዶላር እንደቀማት ተገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4a4F1Dn
13.3K views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ