Get Mystery Box with random crypto!

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የሰርጥ አድራሻ: @alainamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 69.32K
የሰርጥ መግለጫ

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-05-01 10:40:22 ከሃማስ ጋር ተኩስ ለማቋም ብንስማማም በራፋህ የምድር ውጊያ መጀመራችን አይቀሬ ነው - ኔታንያሁ

ሃማስ እስራኤል ላቀረበችው የ40 ቀናት ተኩስ አቁም ምክረሃሳብ አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ነው ኔታንያሁ ይህን ያሉት።

https://bit.ly/3UuDAbE
12.9K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 10:00:51 እንግሊዝ የመጀመሪያዎቹን ፈቃደኛ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ ላከች

የእንግሊዝ መንግስት በፍቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ ለሚመለሱ ስደተኞች ለእያንዳንዳቸው 3ሺ ዶላር እንደሚሰጥ ገልጿል።
https://bit.ly/4a58Cwe
12.6K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 09:05:45 ኢትዮጵያ በአውሮፓ ህብረት ውሳኔ ማዘኗን ገለጸች

የአውሮፓ ህብረት ከሰሞኑ በኢትዮጵያዊያን ላይ የቪዛ ገደብ መጣሉ ይታወሳል

ኢትዮጵያ ህብረቱ በኢትዮጵያዊያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ዳግም እንዲያጤነው ጠይቃለች

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3JDnszs
12.6K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 06:45:07
ቻይና የፍልስጤም ተቀናቃኝ ቡድኖች የሆኑትን ሃማስ እና ፋታህ ማደራደር ጀመረች

የሁለቱ ቡድኖች ተወካዮች በቤጂንግ ያደረጉት የመጀመሪያው ንግግር “ተስፋ ሰጪ” ውጤት የታየበት መሆኑንም የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊ ጂያን ተናግረዋል።

ቃልአቀባዩ በእለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ዝርዝር ጉዳዮችን ባይጠቅሱም የሃማስና ፋታህ ተወካዮች በቻይና ጋባዥነት ቤጂንግ በመገኘት ልዩነታቸውን ለማጥበብ ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

“ሁለቱም አካላት የፍልስጤማውያንን አንድነት ለማረጋገጥና ጥምረት ለመፍጠር ተከታታይ ውይይቶችን ለማድረግ ተስማምተዋል”ም ነው ያሉት።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/49Yi6JB
12.7K views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-30 23:34:58
የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምንድን ነው፤ የእስራኤል ባለስልጣናትንስ ለምን አስጨነቀ?

የእስራኤል ባለስልጣናት የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሀገሪቱ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ ሊሰጥ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።

እስራኤል በ126 ፈራሚ ሀገራት የተቋቋመው ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባል ባትሆንም በጠቅላይ ሚንስትሯ እና ጦር አመራሮቿ ላይ የእስር ማዘዣ ሊወጣባቸው እንደሚችል በማሰብ ይህ እንዳይሆን በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ተገልጿል።

አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ የጦር ወንጀሎችን፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን እና የጥቃት ወንጀሎችን ለፍርድ ለማቅረብ በፈረንጆች 2002 ተቋቁሟል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/what-is-the-international-criminal-court
13.1K views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 12:41:48 የዩክሬን ጦር በምስራቅ ግንባር ከ3 መንደሮች ለቆ ለመውጣት ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

የዩክሬን ጦር በምስራቅ ግንባር ያሉ ሶስት መንደሮችን ለቆ ለመውጣት መገደዱን የዩክሬን ጦር አዛዥ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
https://bit.ly/4baaVjf
12.9K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 11:46:42 ብሊንከን ከአረብ ሀገራት አቻዎቻቸው ጋር ለመምከር ሪያድ ገቡ

የሚኒስትሮቹ ምክክር ከጋዛው ጦርነት በኋላ በሰርጡ ሊኖር በሚችለው አስተዳደርና የመልሶ ግንባታ ስራዎች ላይ ያተኩራል ተብሏል።

https://bit.ly/3xXfpLg
12.9K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 11:05:51 እስራኤል በራፋህ በፈጸመችው የአየር ድብደባ 22 ፍሊስጤማውያን ሞቱ

በእስራኤል ጥቃት ከሞቱት መካከል 6 ሴቶችና 5 ህጻናት ይገኙበታል። በእስራኤል ሃማስ ጦርነት የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር ከ34 ሺህ አልፏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3UBAvHI
12.8K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 09:44:32
በጦር ግንባር ያለው ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ዩክሬን አስታወቀች

የሩሲያ ጦር ጥቃት መጨመሩን ተከትሎ በጦር ግንባሮች ያለው ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን የዩክሬን ጦር አዛዥ አስታወቁ።

የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ጄነራል ኦሌክሳንደር ሰርሰይኪ እንዳስታወቁት፤ የዩክሬን ጦር ከምስራቃዊ ዶኔስክ አከባቢ ለቀው እየወጡ በመውጣት ላይ ይገኛሉ።

ዩክሬን ቁልፍ ወታደራዊ ስፍራዎችን ማጣቷን ያመኑት ዋና አዛዡ፤ ሞስኮ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ ታክቲካዊ ስኬትን አስመዝግባለች ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3WedR9N

13.1K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 08:15:09
በትግራይ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በዋሉ የራያ እና አላማጣ አካባቢዎች ህይወት ምን ይመስላል?

ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል።

የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል።

የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል።

የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Qp1N1z

13.3K views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ