Get Mystery Box with random crypto!

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የሰርጥ አድራሻ: @alainamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 69.08K
የሰርጥ መግለጫ

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-04-18 11:52:03 የአውስትራሊያ የኦርቶዶክስ ጳጳስ በስለት ጥቃት ለፈጸመባቸው ግለሰብ “ይቅርታ አድርጊያለሁ” አሉ

አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በቀጥታ በሚተላለፍ መርሃ ግብር ላይ እያስተማሩ ነበር ጥቃት የተፈጸመባቸው። ጳጳሱ “ይህንን ጥቃት እንዲፈጽም ለላኩትም ይሁን ጥቃቱን ለፈጸመው ግለሰብ ሁሌም እጸልያለሁ” ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/3w7qJ6N
13.9K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 11:03:16 የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ባለው ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ

ተቋሙ የባህር ሀይል አባላቱ በ"ጽንፈኞች" ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4aElkmU
13.9K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 10:00:40 የአምናው ሻምፒዮን ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል ከሻምፒዮንስ ሊግ ተሰናበቱ

የእንግሊዝ ክለቦች በተመሳሳይ ቀን በሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሲሰናበቱም የመጀመሪያው ሆኗል።

https://bit.ly/3Jmu7Og
14.3K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 20:40:21
የዓለም ቁንጅና ውድድሮችን ደጋግመው ያሸነፉ ሀገራት እነማን ናቸው?


ሚስ ወርልድ በመባል የሚታወቀው የቁንጅና ውድድር ከ1952 ጀምሮ እእየተካሄደ ይገኛል


ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ላይ በዲና ፈቃዱ አማካኝነት አንድ ጊዜ ብቻ ተወዳድራ በምርጥ 20 ቆነጃጅት ዝርዝር ውስጥ ተካታ ነበር

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/4cZXl36
16.5K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 20:40:12
በ6 የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች 29 ጎሎች የተቆጠሩበት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት ምን ያስመለክተናል?

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ምሽት 4 ስአት ላይ ሲደረጉ አርሰናል ወደ አሊያንዝ አሬና በማቅናት ባየር ሙኒክን ይገጥማል።

የአምናው ሻምፒዮን ማንቸስተር ሲቲ በበኩሉ ሪያል ማድሪድን በኢትሃድ ያስተናግዳል።

የሁለቱ የምሽቱ ፍልሚያዎች አሸናፊዎች በግማሽ ፍጻሜው ይገናኛሉ።

ፒኤስጂ እና ዶርትሙንድ ትናንት ምሽት የባለፈው ሳምንት ሽንፈታቸውን ቀልብሰው የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆናቸውን ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

ዛሬ ምሽት የሚደረጉት ጨዋታዎችስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገብባቸዋል? ግምትና አስተያየትዎን ያጋሩን!

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
15.5K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 19:36:20 በኤምሬትስ በ75 አመታት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዘገበ

የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም በዝናብና ጎርፍ ምክንያት በረራ ለማስተናገድ መቸገሩ ተገልጿል።

https://bit.ly/49FmoFB
15.0K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 19:05:50 አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ለምን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላሉት ጦርነቶች ትኩረት ነፈጉ?

እነዚህ ተቋማት እና ሀገራት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት እንዲቆም ሲያደርጉት የነበረውን ጫና ለምን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ መድገም አልቻሉም የሚል ጥያቄ ይነሳባቸዋል።
አል ዐይን አማርኛ በዚህ ጉዳይ የፖለቲከኞችን፣ የአውሮፓ ህብረትን እና የአሜሪካ መንግስትን አስተያየት አካቷል።
ዝርዝሩን ያንብቡ፦
https://bit.ly/4cZKBJO
15.2K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 18:10:03 ለጋሾች ለሱዳን ሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ 2 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገቡ

ጦርነቱ የእርዳታ ማዕከል በሆነችው እና እስካሁን በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ባልተያዘችው የመጨረሻዋ የምዕራብ ዳርፉሯ ከተማ አል ፋሽር ዙሪያ እየተስፋፋ ነው።
https://am.al-ain.com/article/donors-raise-2-bln-euro-sudan
15.1K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 16:25:30 የኢራን ጦር እስራኤል የምትስነዝረውን ማንኛውንም ጥቃት እንደአመጣጡ ለመመከት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

የሀገሪቱን የ'ጦር ቀን' ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ወታደራዊ ትርኢት ላይ የተገኙት የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲ "በጽዮናዊው መንግስት በመሬታችን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት ከባድ ምላሽ ይሰጠዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
https://am.al-ain.com/article/iran-says-ready-deal-threat-israel
16.0K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 15:26:28 ዩክሬን የሩሲያን ጥቃት መከላከያ "ሚሳይል አልቆብኛል" አለች

ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ቀደም ሲል የሩሲያ ሚሳይል ጥቃት የማይቀንስ ከሆነ ዩክሬን የመከለከያ ሚሳይሎች ሊያልቅባት እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር።
https://am.al-ain.com/article/urakine-says-ran-out-missile-defend-russian-attack
16.1K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ