Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠራች ለቻይና በመሰለል ተጠርጥረው በርካቶች ጀርመን ውስጥ መታሰራቸው | Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

ቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠራች

ለቻይና በመሰለል ተጠርጥረው በርካቶች ጀርመን ውስጥ መታሰራቸውን ተከትሎ ቤጂንግ በቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠርታለች።

ሮይተርስ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው በበርሊን የሚገኙት የቻይና አምባሳደር ተጠርተው ቻይና እያደረገችው ነው በተባለው የስለላ ተግባር ዙሪያ እየተካሄደ ስላለው ምርመራ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ባለፈው ማክሰኞ በአውሮፓ ህብረት ጀርመንን በመወከል አባል የሆኑት ማክሲሚላን ራህ ረዳት ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለቻይና በመሰለል ተጠርጥሮ ጀርመን ውስጥ ታስሯል።

አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ የተያዘው ግለሰብ ጂያን ጉኦ እንደሚባል እና በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውስጥ ስለተደረጉ ውይይቶች ለቻይና ደህንነት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ እንደነበር ገሎጿል።

በሳምንቱ መጀመሪያ ደግሞ ሶስት ጀርመናውያን ለወታራዊ ስለላ ጥቅም ላይ ይውላል የተባለ መተግበሪያ አሳልፈው በመስጠት ተጥርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic