ህብረቱ ሁለቱ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው ቦታዎች ያለው የንጹሃን መፈናቀል እንዲቆም ጠይቋል የአማራ እና የትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ እና አካባቢዋ ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በአወዛጋቢዎቹ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፎላ "በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ያሉ ውጥረቶችን" በትኩረት እየተከታተሉት መሆኑን ገልጿል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረሰው የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የዘላቂ ሰላም ስምምነት፣ ሁለቱ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው "አወዛጋቢ ቦታዎች" በህገመንግስቱ መሰረት እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይጠቅሳል። ሊቀመንበሩ ሁለቱም ወገኖች ግጭት ከማባባስ እንዲታቀቡ እና የአካባቢውን ንጹሃን መፈናቀል እንዲያስቆሙ ጥሪ አቅርዋል። https://bit.ly/3Wc5L1m 14.4K views20:21