Get Mystery Box with random crypto!

Aki Man Z Menz

የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz A
የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz
የሰርጥ አድራሻ: @akiman12345
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 334

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-06 13:25:50 Alert

ዛሬ ከታህሳስ 28 ቀን 2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ ጠጥተው በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።

ይህ ቁጥጥር ለ2 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የቆየው  በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ነበር።
52 viewsAki_man , 10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 13:24:11 በዛሬው ከቀኑ ዕለት 6:00 አዳማ ከተማ ቦኩ ሸነን ቀበሌ በተለምዶ አደማ ቆርቆሮ እየተባለ በሚጠራው አከባቢ መከላከያን ጭኖ እየሄደ ያለ የጭነት አይሱዙ መኪና ተገልብጦ 7 ቱ ወዲያው ሙተው ሌሎች ቆስሎ በአዳማ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ።
Natnael mekonnen
53 viewsAki_man , 10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 20:31:44 https://www.facebook.com/100015895362276/posts/pfbid02Z9QNZkFfQx5rjnnERquE4T8syuM71sBn5LLx7xUw4V1niCejCua58KYzkofe3VVPl/?app=fbl
848 viewsAki_man , 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 15:41:06 አርቲ ቡርቲ ድሪቶ
ወርዶ ለብሶ ቦትቶ
መብላት ሳይችል ራት ምሳ
ለፀብ ተንኮል የሚነሳ
ማነው ስሙ ምንስ ይባል
አይነሳ ከአዘቅቱ አዛው ይጣል።
66 viewsAki_man , 12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 15:02:59 ከማዶ ሚመጣው፥ ዘመድ ነው እንግዳ
ከላይ የተለጋው፥ ኳስ ነው ወይስ ናዳ
ብየ መች ጠየቅሁኝ
መጭውን ጠበቅሁት
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብየ፤ ጸሀይ እየሞቅሁኝ፥

መከራም አላጣም፥ ተድላም አልጎደለኝ
ደንታ ነው የሌለኝ፥

ባካል በስሜትም፥ ታሞ ላገገመ
ወድቆ ለተነሳ፥ እየደጋገመ
ከገዛ ጉድጓዱ፥ አጽሙን ለሚለቅም
ሞትም ብርቅ አይደለም፥ ትንሳኤም አይደንቅም።
69 viewsAki_man , 12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 11:55:00 #ይጠንቁ
ሁሉም ማህበረሰብ ጥንቃቄ ያድርግ

###

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሐሰተኛ የብር ኖት ይዞ በሱቅ እየተንቀሳቀሰ ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥረ ስር ዋለ፡፡

ታህሳስ 27/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምንሊክ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽህፍት ቤት የኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንድር ደንሳ ጣሰው እንደገለፁት አድራሻው ሰሜን ወሎ ጋሸና የሆነው ተጠረጣሪ አብረሃም ተሰፋዬ ገበየሁ ታህሣስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብረሃን 3000 የሐሰተኛ ብር ይዞ በመምጣት በሚኒልክ ክፍለ ከተማ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ ልዩ ቦታው አጅብ አካባቢ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በተለያዩ ሱቆች በመንቀሳቀስ ባለ 200 የሐሰት የብር ኖትን በመጠቀም ከሱቅ ስኳር እና የተለያዩ ዕቃዎችን በመግዛት በማታለልና በማጭበረበረ ተግባር ተሰማርቶ የሐሰተኛ ብሩን ወደ መደበኛ ብር እየቀየረ እያለ ለፀጥታ ኃይል በደረሰው ጥቆማ መሰረት ግለሰቡ በእጁ ላይ ፎርጅድ 800 ብር እንደያዘ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡

በግለሰቡ ላይ ወዲያውኑ ምርመራ በመደረጉ ከአዲስ አበባ 3000 ፎርጅድ ብር ይዞ እንደመጣና ወደ ህጋዊ ብር ኖት 2200 ብር የሚሆነውን እንደቀየረው ማጣራት ተችሏል ብለዋል፡፡

በእጁ ላይ የተመነዘረ ብርም ባለ 200 ብር = 400፣ ባለ 100 ብር =200፣ ባለ 50 ብር = 500፣ባለ 10 ብር 240፣ባለ 5 ብር = 35፣ በድምሩ 1375 ብር ወደ ህጋዊ የብር ኖት የቀየረውን እና ፎርጅድ ብር 800 ብር እንደያዘ እጅ ከፈንጅ ተይዟል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ አንድ ሞባይል የሰረቀ ግለሰብም ከነ ሞባይሉ የተያዘ ሲሆን በክፍለ ከተማው በዓልን ምክንያት በማድረግ ለፀጥታው ግብረ ኃይል የተሰጠው አቅጣጫ ውጤታማ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ከማድረግ በዘለለ የፀጥታ ኃይሉን መገዙን እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
75 viewsAki_man , 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 11:54:56
63 viewsAki_man , 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 10:47:29
64 viewsAki_man , 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 10:47:27 @SHARE!!
የወላዲት አምላክ የእምየ ቤተልሄሟ ይህ ነው እዩት ፈርሷልshare በማድረግ በረከት እናግኞ!
።።።።።።።።።[አይኔ-ማርያም]!
ጥንታዊቷ ስለት ሰሚዋ በይፋት የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የኦሪት መሠዊያ ያለባት {የአይኔ -ማርያም}በዚህ ቦታ ገዳም ብዙ ነገስታት ነገስውባታል፤ብዙ ጳጳሳት ተቀምጠዋባታል።
የአይኔ-ማርያም ያላትም የንጉስ ስብስቲያኖስ(ሰብስቲ) አባት ንጉስ ነጋሴ ክርስቶስ ጊስ ማርያምን የተከለ ነው፤በርቀት ይችንም ጥንታዊ ገዳም አይቷት አይኔ -ማርያም አላት።
ንጉስ ነጋሴ ክርስቶስ 15 ዓመት በዚህ ቦታ መጦ ከተማ መስርቶ ከዚያም ወደ ጎንደር ሄዶ አረፈ በፊት አቦ በሚባል ቦታ ተቀበረ፤ ልጆቹም አክዋ ክርስቶስ እና ስብስቲያኖስ ይባሉ ነበር።እንዳረፈ ልጆቹ እኔ እንግሳለሁ እኔ እነግሳለሁ ተባበሉ ተጣሉ ታላቁን አክዋ ክርስቶስ አሸንፎ ሰበስቲያኖስ በዚህ ገዳም በአይኔ ማርያም ነገሰ።አክዋ ክርስቶስም ወጃ ቅዱስ ሚካኤልን ተከሎ አረፈ። እስካሁንም በይፋት ወጃ ቅዱስ ሚካኤል አካባቢ በቤተክርስቲያኑ አቅራቢያ አክዋ ባዶ የሚባል ቦታ አለ።
ንጉስ ስብስቲያኖስም 5አመት ገዝቶ ከማረፉ በፊት በይፋት ይች ብቻ አይኔ ማርያም ጥንታዊ ገዳም ነበረች፤ ቀጥሎም ይዛባ ማርያምን ገዳም ተተከለች።
ታቦት አልነበረም በየአድባራቱ ፤ከዚያም የንጉስ ስብስቲያኖስ ልጆቹ አብየ እና መርሐዊት የሚባሉ ነበሩት።
ነጋሴ ክርስቶስም የነበረውን መሬት እንደየ ደረጃቸው ለካህናቱ ለዲያቆናቱ ለአይኔ ማርያም ብዙ ጋሻ መሬትም ሰጥቷት ጎንደር አካባቢውን ይገዛ ስለነበረ ሄዶ በድንገት አረፈ።
ከአይኔ ማርያም የነበረውን የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የንጉስ ስብስቲያኖስ ልጅ አብየ እንደ ስርቆሽ አድርጎ ወስዶ ዶቋቂት በሚባል ቦታ የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ወስዶ ቤተክርስቲያን ስራ ።
ንጉስ ነጋሴ ክርስቶስ የስብስትያኖስ አባት ይዛባ ቅድስት ማርያምን ተከለ።
ንጉስ አብየ የሰብስቲያኖስ ልጁ ታቦታቱን እንደ ስርቆሽ አድርጎ ሲወስድ አባቱም ስብስቲያኖስ እና አይኔ ማርያም ካህናት አያውቁም ነበር። ያለፍቃዳችን እንዴት ይተክላል ገብተን ታቦታቱን እንይ ብለው ገብው ሲያዩት የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ጠፍቷል፤ የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ወስዶ ዶቋቂት ተክሎታል ቤተክርስቲያን ሰርቷል።
አባቱ ስብስቲያኖስ እንዴት ሳያስፈቅድ ታቦታቱን ይወስዳል ብሎ ከልጅ ከአብየ ተጣላ ጦርነት ገጠመ ሾላ ሚዳ በሚባል ቦታ፤የልጁ የአብየ አሽከሮችም ንጉስ ሰብስቲያኖስ ገደሉት።
ልጁ አብየ ማርኩት እንጅ እንዴት አባቴን ትገላላችሁ ብሎ አሽከሮቹን ተጣላቸው አብየ አሽከሮቹንም ገደላቸው ።ንጉስ ሰብስትያኖስም በአይኔ ማርያም ተቀበረ።ልጁም አቡየ ንጉስ ሆነ ስሙም አመሃእየሱስ ወይም አብየ ተብሎ ነገሰ።
የተተከለበት ተራራ ዶቋቂት የሚባለው ቦታው ቤተክርስትያን ከመሰራቱ በፊት አባቱ ስብስቲያኖስ በርቀት ሲያይ በተራራው መብራት አየ ፤በዚያም ግዜ በ16ክፍለ ዘመን በዚህ ቦታ መብራት ያየበት ቦታ ዶቋቂት ተራራ ሲሄድ ከሌላ ሀገር መጥተው የወረሩት እምነት የሌላቸውን ሰዎች አየ አስጠመቃቸው በዶቋቂት በሚባለው ቦታ ክርስትያን አደረጋቸው።
ልጁም ንጉስ አብየ በዶቋቂት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን የተከለበት ቦታ ማለት ነው።ንጉስ አብየ 30ዓመት ገዝቶ በዶቋቂት ቅዱስ ሚካኤል ተቀበረ።ቦታውም የአብየ(አመሀእየሱስ)ተባለ።
እህቱም መንበራዊት የምትባል ነበረች፤ ንብ አንባ በሚባል ቦታ ትኖር ነበር፤አሽከሮቿ ከንብ አንባ እያዘሉ እያመጡ ዶቋቂት ነበር የምታስቀድሰው፤አርግዛም አሽከሮቿ ወደ ዶቋቂት በተልባ ውስጥ ወሰዷት አርግዥ እንዴት በተልባ ምች መቶኞ እንዳሶርድ አሸከሮቼ እንዲህ አደረጉኝ ብላ ለወንድሟ ንጉስ አብየ(አመሀእየሱስ) አዝና ነገረችው።
ወንድሟ ንጉስ አብየ እንደስርቆሽ የወሰደውን ሁለት ታቦታት ማለትም ዶቋቂት በሚባል ቦታ የተከለውን የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ነበር። መንበራዊት የነበረችበት ንብ አንባ የሚባለው ቦታ ትንሽ ርቀትም ቆላም ስለነበረ ፤በንብ አንባ ወለደች ለወንድሟ ለንጉስም እባክህ በድንኳን ለአንድ ቀን የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ስጠኞና ክርስትና ላስነሳ ብላ ጠየቀችው ንጉሱም ወንድሟ ፈቅዶላት ክርስትና አስነስታ አንድ ቀን በድንኳን አድሮ ታቦቱን ሊወስዱ ሲል እንቢ አላቸው፤ በዚያሜ ታቦቱ በድንኳን በነበረብት ለአንድ ቀን መጥቶ በአረፈበት ንብ አንባ በሚባል ቦታ ቅዱስ ገብርኤል ተተከለ።
ልጅም ወልዳ በንብ አንባ ቅዱስ ገብርኤል ክርስትና አስነሳች።ቦታውም ንብ አባ የመንበራዊት ተባለ፤ዶቋቂትም የአቡየ(አመሀእየሱስ)ይባላል።
ንግስናውም ዘራቸው ከነጋሴ ክርስቶስ እስከ ሰሐለ ስላሴ ፣ሀይለ መለኮት፣ አፄ እምየ ምንሊክ እና አፄ ሐይለ ስላሴ ድረስ ደረሰ።
ከአይኔ ማርያም ብዙ ታቦታት ወስደው በተለያየ ቦታ ነገስታቶች ታቦታትን ተከሉ ወጃ ቅዱስ ሚካኤል ፣ደብረሲና መድሐኔዓለም ፣ይዛባ ማርያም፣ ዶቋቂት ቅዱስ ሚካኤል፣ ንብ አንባ ቅዱስ ገብርኤል ከአይኔ ማርያም እንደሄዱ ይነገራል።
አይኔ ማርያም እርዳታችሁን ትፈልጋለች
ሀ/ቤተልሄሟ ይህ ነው እዩት ፈርሷል
ሐ/አጥር የላትም
መ/መስቀል ቤትና ደጀ ሰላሙ ፈርሷል የአካባቢው ምዕመንም የመጀመሪያ ሆና ወደ ኋላ ቀረች አሮጊቷን ማርያም አስቧት ቤቷን እንስራ ብለዋል።
ለመርዳት እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነው፤ለእርሱ ብድር ነውና መስጠት መርዳት ለእግዚአብሔር ማበደር ነው።
ለመርዳት ለበረከቱ በያላችሁበት ታብቃችሁ፤ ሀገራችን ሰላሙን አንድነትን ፍቅርን እውነትን ትዕግስትን ትስጠን።አሜን!
የገዳሟ የባንክ ቁጥር
Acccount no-74327877
Account name-አይኔ ደብረ ንግስት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
አቢሲኒያ ባንክ
በሌላ በሁሉም ሐገር ድርቅ ሆኖ በዚህ በይዛባ እና በአይኔ ማርያም አካባቢ በልግ ሆኖ (እህል ሆኖ)____ይህ ተብሎ ነበር...........
<አይኔና ይዛባ አለች ወይ እናትህ፥
ከፈጠርከው ፍጡር ምነው መለየትህ፥
ከፈጠርኩት ፍጡር እኔ መለየቴ፥
አይኔና ይዛባ በትኖር ነው እናቴ።>
በዚያን ግዜ ተባለ ብለው የሐገሩ ሽማግሌዎች ነገሩኝ ተመስገን!
ቦታዋ፦በመንዝናይፋት በይፋት አውራጃ ከደብረሲና ከተማ በእግር የ1ሰዓት መንገድ በመኪና እስከ ቤተክርስቲያን ይገባል 15ደቂቃ መንገድ ነው።
64 viewsAki_man , 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 07:51:53 ጨዋታዉ ፈረሰ
.
.
ልጅነቴ ልጅነትህን፤
       ለጋነትህ ጮርቃነቴን፤
በትዝታ እየቃኘሁ፤
        ሳቃችንን እየሰማሁ፤
በትዉስታ ምልሰት፤
       በጥሞና ስመለከት።
በድንጋይ ከታትፈን፤
           ማባያ ጨምረን፤
መረቁን ከልሰን፤
          የሰራነዉ ጎመን።
ለሚመጣዉ ዘመን፤
          የእቃቃ ሰርጋችን፤
ሚዜ ስናዘጋጅ ፤
         መኖርን ስንዋጅ፤
ወረቀት ቀዳደን፤
            ቦጭቀን፤ 
ቦጫጭቀን፤
           እየጎዘጎዝን፤
ሰፈር ስናበላሽ፤
       መንደር ስናቆሽሽ፤
ቡና አፍልተን፤
        ቁርሱን በልተን፤
ደግሞ ስንጣላ፤
        ይጠፋናል መላ፤
ኩርኩም ስንቃመስ፤
          ጮኸን ስንዋቀስ፤
መተቃቀፍ በማግስቱ፤
         መንከባለል በክረምቱ፤
ስንቱ አለፈ በጊዜያቱ።
              የእቃቃ ቤታችን፤
ያለምነዉ ኑሯችን፤
          ጨዋታዉ ፈረሰ፤
ዳቦዉ ተቆረሰ።
70 viewsAki_man , 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ