Get Mystery Box with random crypto!

Aki Man Z Menz

የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz A
የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz
የሰርጥ አድራሻ: @akiman12345
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 334

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-07-07 14:53:15 አሉታዊ ነህ ወይስ አዎንታዊ ?

አሉታዊ ስህተትን ይፈላልጋል ፤ አዎንታዊ መፍትሄን ያገኛል ፡፡ አሉታዊ ከንፈር የሚመጥለት ሰው ይፈልጋል ፤ አዎንታዊ መፍትሄን ይፈልጋል ፡፡ አሉታዊ በሰዎችና በሁኔታዎች ሲፈርድ ይታያል ፤ አዎንታዊ ሁኔታዎችንና ሰዎችን ለመቀየር ራሱን ያቀርባል ፡፡ አሉታዊ በእጁ ላይ ስላለው ጥቂት ፍሬ ሲነጫነጭ ይታያል ፤ አዎንታዊ ተነስቶ ይዘራዋል ፡፡

አሉታዊ በፊቱ መከራና ውድቀት እንዳለ ያስባል ፤ አዎንታዊ የስኬት ዘመንን ወደ መኖር ለማምጣት ይሰራል ፡፡ አንድ ሰው አሉታዊውን አመለካከት በመጣል ወደ አዎንታዊው ለመዝለቅ ራሱ ማስለመድና አመለካከቱን ንድፍ መቀየር የግድ ነው ፡፡ አዎንታዊን ዝንባሌ ያዳበሩ ሰዎች እይታዎቻቸው አስገራሚና ለስኬት አመቺ ናቸው ፡፡ የሚከተሉትን የአዎንታዊ ሰዎች አመለካከት እንመልከት ፡፡

የዛሬ አለመሳካት ዘላቂ እንዳልሆነ ማወቅ “ጸሃይ የጠለቀችው በአዲስ ሁኔታ ልትወጣልኝ ነው” - Robert Browning ፡፡ በአዎንታዊ አመለካከት የተሞላ ሰው እይታው ይህ ነው ፡- የጠለቀ እንደገና ይወጣል ፤ የወደቀ እንደገና ይነሳል ፤ የጠፋ እንደገና ይገኛል ፤ የተበላሸ እንደገና ይታደሳል ፡፡

ነገሮች ከዚህ የከፉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ “ሁል ጊዜ የተበላሸውንና የጠፋውን ሳይሆን የተረፈውን አስብ” - Robert H. Schuller ፡፡ አዎንታዊ ሰው ነገሮች ተበላሽተው እያሉ እንዳልተበላሹ ለማስመሰል አይኑን አይጨፍንም ፡፡ በምትኩ እውነታውን ለመጋፈጥ አይኑን ይከፍታል ፣ የሚያተኩረው ግን የተበላሸው ላይ ሳይሆን የተረፈው ላይ ነው ፡፡

በስሜትና በጊዜአዊ ግምት አለመመራት “ነገ ዓለም ያከትምላታል ብባልም እንኳ ዘርን ከመዝራት አልመለስም” - Martin Luther ፡፡ ለአዎንታዊ ሰው ነገር የሚያከትምለት በርግጥም ሲያከትምለት ብቻ ነው ፡፡ እስከዚያው ድረስ እንደሚሳካ ፣ ሁኔታዎች እንደሚለወጡና ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ከማሰብ አያቆምም ፡፡ በአሉባልታና ለጊዜው በተናፈሰ መረጃ-ቢስ ወሬ አደራረጉን አይለውጥም ፣ ወደ ፊትም ከመገስገስ አይገታም ፡፡

የስህተትን አይቀሬነት መቀበል “አብዛኛዎቹ እርሳሶች ለመጻፊያ ሰባት ኢንች ርዝመት ሲኖራቸው ለማጥፊያ ደግሞ ግማሽ ኢንች ላጲስ አላቸው - አዎንታዊ አመለካከት” - Robert Brault ፡፡ ከአንድ እርሳስ ጋር አብሮ ማጥፊያ ላጲስን መስራት የአዎንታዊ ሰው እይታ እንጂ የአሉታዊ አይደለም ፡፡ አዎንታዊ ሰው ነገሮች እንደተጀመሩ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ያውቃል ፡፡ ከዚህ እውቀቱ ጋር ግን የተበላሹ ነገሮች ሊሰረዙና ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ጽኑ እምነት አለው ፡፡
48 viewsAki_man , 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:50:41 የ2015 በጀት አመት 6 የትኩረት አቅጣጫዎች ዛሬ ለፓርላማው ተገልፀዋል።
1. ብድር መቀነስ
2. የበጀት ጉድለት መቀነስ
3. ያለንን ሀብት በቁጠባ መጠቀም
4. የዋጋ ንረትን ማረጋጋት ነው
5.መልሶ ማቋቋም እና ሰብአዊ እርዳታ ነው
6. የሀገር ደህንነት እና ሰላምን ማስጠበቅ ነው
49 viewsAki_man , 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 18:12:20
ነገ 2:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ

ብዛታቸው 24 ሺህ 491 የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ይወጣል።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአቱ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች ውድድሩ ውስጥ ይካተታሉ ።

ከ1997 ዓ.ም የ20/80 ተመዝጋቢዎች መካከልም 60 ወራት ሳያቋርጡ የቆጠቡ ቅድሚያ ይሰጣል።
88 viewsAki_man , 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 18:11:32
የወያኔ ዉሻ እኔ አልታረቀዉ እሱ አይታረቀኝ
ለእናት ሀገሬ ነዉ ብሞትም አይቆጨኝ

ድምፃዊ አበበ ካሴ
83 viewsAki_man , 15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:12:23 አንጽሮተ እንስት
==============
ሴት ማለት፣
አረፍተ ነገር ሳይኖር፣ ሥርዓተ ነጥብ፣
በባዶ ወረቀት ሥር፣ እምትነበብ፣
የሁኔታ ልብወለድ፣ የጊዜ አንቀጽ፣
ትርጉም የሌላት ስህተት፣ እንዴት ብዬ ልግለጽ?!

እናትነት ግን፣
ከአንድ ትልቅ ቡልኮ ሥር፣
የተመዘዘች አንዲት ክር፣ ...
በዛች ቀዳዳ፣ በዛች ሽንቁር፣
የበረሃ ንፋስ፣ የደጋ ቁር፣
ጆሮ እንዲያደነቁር፣
ልብ እንዲያወልቅ፣
አንድ ክር ናት፣ ተቆጥራ እማታልቅ።
እናትነት።

እናትነት ማለት፣
ብዕር ወረቀት ሳይኖር፣ የተጣፈች ጥበብ፣
ሥርዓተ ነጥብ ሳይኖር፣ የምትተረክ ነቢብ፣
የልብወለድ አላባዊ፣ የመልዕክቱ ክበብ፣
እናትነት ባይኖር፣ ሕይወትን ማ'ሊያነብ?!!

እናት ሳይሆኑ ሴት፣
ኤፉድ ያለ መቀነት።
እናትነት።

ጥምጣም የሌለው ካህን፣
ምግብ የሌለው ሳህን፣
ትርጉም አለው በምስጢር፣
እናት ሳይኮን፣
የሴትነት ዓለም፣ የሴትነት ምድር።

ጽላት ሳይኖር፣ የተጣፈ ትዕዛዝ፣
ግብጽ ሳይኖር፣ የፈርዖን አገዛዝ፣
ትርጉም አለው በስውር፣
ገረድ ሳይኮን፣
መመኘት የልዕልትነትን ክብር።

ከእናትነት ጎጆ፣ ብትነቀል አንዲት ሴት፣
የጥላቻ ዝናብ፣ አይዘንብም እኛ ቤት።
የተገላቢጦሽ ሆኖ፣ ቢዘንብ እንደ ድንገት፣
እዛም እዚህም ይዘረራል፣ የፍቅር ቅል አንገት።
================
84 viewsAki_man , 12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:41:45
ብሞት ፀፀት እንዳይሆንብኝ ነው
.
« የፓርላማ አባሉ ሀንጋሳ ኢብራሂም »

ወለጋ ያለውን ጭፍጨፋ የሚፈፅሙት የኦሮሚያ ክልል መንግስት እና አመራሩ ናቸው። ሸኔዎች አይደሉም። ሁለት አይነት ሸኔ ነው ያለው። አንዱ ሸኔ የሚመራው በኦሮሚያ ክልል መንግስት ነው። ሌላኛው ሸኔ ንፁህ ታጋይ ነው።

ሰዎች በብሔር ማንነታቸው ተለይተው እንዳይገደሉ ከተፈለገ የክልሉ መንግስትና መዋቅሩ መፍረስ አለበት። ዶክተር አብይ አትታለል። በውሸት አይሸውዱህ። የውሸት ሪፖርት ነው የሚሰጡህ። እሱን እየሰጡህ በህዝብ ፊት እያሷሽህ ነው። ገዳይ ያለው እዚህ እመንግሥት ቢሮ ውስጥ ነው።
የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀላፊና የክልሉ መንግስት ናቸው እያስገደሉ ያሉት።

ይችን ሀቅ ተናግሬ ብሞትም አይቆጨኝም።
ሳልሞት በፊት ያስቀየምኳችሁ ሰዎች ካላችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ። ከሦስት ቀን በፊት ነበር የሀንጋሳ ኢብራሂም የግል ጠባቂ አዲስ አበባ ላይ የተገደለበት። ሀሰንጋሳም ሂዎቱን ያቀዋል። መንግስት ልክ እንደሰለጠኑት አገራት ለልጅ ጠባቂ ያድርግለት።

ልጁ ግን ጎበዝ ነው። በቃ ሀቅን ተናግሮ ሞቱን መርጧል። እኛ የቆምነውም ሆነ ነፍሳቸው በፈጣሪ እጅ ያሉ የግፍ ተጨፍጫፊዎች « ፍትህን የምንጠይቀው አገሪቱን ከሚመራት መንግሥት ነው »። ከዚህ በኋላ የሚታለል ሰው የለም። የፓርላማ አባሉ የተናገሩት'' ትናንት የሰላም ሚኒስቴሩ "አቶ ታየ ዳንዳ በወፍ በረር የፃፉትን ሀሳብ ነው። የንፁሀን ደም እንዲህ ይፈርዳል። አሁን ሁሉም ነገር ገልፅ ሆኗል።

እናመሰግናለን ሀንጋሳ ኢብራሂም (ዶክተር )
76 viewsAki_man , 11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:30:36 ስጋችን ተበላ ደማችን ተጠጣ
የለዉጡ መሪያ አብይ ሲመጣ::
82 viewsAki_man , 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:28:44 "ተጠያቂነት ይስፈን!" አቶ ታዬ

<< ንፁኃን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ የሁሉም ጤነኛ ሰዉ ልብ ያዝናል:: ያዘነ ሀዘኑን መግለፁም አግባብ ይሆናል:: እኛ ደግሞ እንደመንግስት የዜጎችን ደህንነት ማስከበር ትንሹ ኃላፊነታችን ይመስለኛል:: ሰላምና ፀጥታ ከሰፈነ ሌላዉን ህዝቡ ራሱ ይሰረዋል:: ነገር ግን የዜጎች ሞት በየቀኑ ይሰማል:: ግምቢ ላይ የተፈፀመዉን አስነዋሪ ጭፍጨፋ ሳንረሳ ሌላ ጭፍጨፋ በቄለም ዛሬ ተደግሟል:: በነገራችን ላይ ጥፋቱ የማነዉ? ጠያቂና ተጠያቂ ሊኖር ግድ ይላል! ተጠያቂነት ባለመኖሩ አንድ ችግር መቶ ጊዜ ራሱን ይደጋግማል!

በርግጥ ላለፉት ሦስት ዓመታት ኦሮሚያ ላይ የፀጥታ ችግር ገንግኗል:: ከመቼዉም ጊዜ በላይ ህዝባችን እጅግ የከፋ መከራ አይቷል:: እዉነታዉን መናገር " ስልጣን ፈላጊ" ያስብላል:: እዉነትን ለመደፍጠጥ የስልጣን ልበወለድ ተፅፎ ወደ ላይ ይተረካል:: ለመሆኑ ህዝብ በሌለበት ምድር ስልጣን ለምን ይጠቅማል? አሁን ተጠያቂነትን በማስፈን እንቆቅልሹን መፍታት የህልውና ጉዳይ ሆኗል! ከዚህ ካለፈ አደጋዉ ከቁጥጥር ይወጣል! >>

አቶ ታዬ ደንደኣ
የሠላም ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ
92 viewsAki_man , 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 13:09:00 ስጠጣ ውዬ አየጨለጥኩ ይንጋ
ጅብ አይበላም አሉ #የሰካራም ስጋ
109 viewsAki_man , 10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 13:08:10
105 viewsAki_man , 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ