Get Mystery Box with random crypto!

Aki Man Z Menz

የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz A
የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz
የሰርጥ አድራሻ: @akiman12345
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 334

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-12 16:04:27
84 viewsAki_man , 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 16:04:07 #አባ_አርፈዋል

መላከ ምህረት ቀሲስ ሀብተወልድ ተምትሜ ከአባታቸው ከደብተራ ተምትሜ አስፈሪ ከእናታቸት ከወ/ሮ እህትማርያም በጋሻው ህዳር 29,1917 ዓ.ም በእመጓ ቆላ ልዩ ስሙ ሾላ ፊት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ተወለዱ ::

ከዚያም ከአባት እና እናታቸው ጋር ካደጉ በኋላ በአባታቸው አማካኝነት ውዳሴ ማርያምን ንባብ ተምረው ተጨማሪ እውቀትን ለማግኘት ወደ የህይጣ በመሄድ በአለቃ ደስታ መምህነት የውዳሴ ማርያም ዜማ መስተጋብዕ እና አቋቋም ተምረው ወደ ትውልድ ቦታቸው በመመለስ በአቡነ ቄርሎስ አማካኝነት በ1936 ዓ.ም ድቁናን ተቀብለው በማገልገል እንዳሉ ከወ/ሮ ጥሩወርቅ ተከተለው ጋር በህገ አብረሃም በ1941 ዓ.ም ተጋብተው እና ኑሮ መስረተው ልጆችም አፍርተዋል::

በመሆኑም የግብርና ሥራቸውን ከክህነት አገልግሎት ጋር በማጣጣም እየሠሩ ለ 5 ዓመታት ከቆዩ በኃላ 1947 ዓ.ም በአቡነ ባስሊዮስ አማካኝነት ቅስናቸውን ተቀበሉ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከ እመጓ ዑራኤል ፣ ቀጭን አንባ ማርያም ፣ አረጋይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጭምር ከድቁና እስከ ቅስና ባላቸው ሙያ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሠፊ አገልግሎት ሲያበረክቱ ቆይተው በ1988 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በአቡነ ኤፍሬም እዚሁ ቦታ በመምጣት ደብሩን ደብረ ምህረት ቅዱስ ዑራኤል እሳቸውን ደግሞ መላከ ምህረት ቀሲስ ሀብተወልድ በማለት ልቅናን ሠጥተው የደብሩ አስተዳደሪ እንዲሆኑ የሾሙአቸው ሲሆን የእመጓ ዑራኤል እና ቀጭን አንባ ማርያም ቤተክረስቲያን እንዲሠራ አድርገዋል::

ከዚህም በተጨማሪ ለረጅም አመታት የእግዚአብሔር አብ ገዳም በአዛዥ የገዳም አገልግሎት ሢሰጥ ቆይቶ 1972 ዓ.ም መሬት ሲደለደል የተወሰደበት በመሆኑ ወደ ቀጭን አንባ ማሪያም የተደረበውን የእግዚአብሔር አብ ፅላት በዚሁ ልዩ ስሙ ሳሎ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በ 2012 ዓ.ም በእሳቸው አማካኝነት የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን መስራች በመሆን አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገዋል ::

አባታችን ሀላፊነት የተቀበሉት በአመጓ ይሁን እንጂ የሚሠጡት አገልግሎት ወሰን ና ቦታ ገደብ ሳይኖራቸው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በጐ አድራጊዎችን በማሠባሰብ ለ 118 ቤተክርስቲያን የሚሆኑ ረድተዋል ፡፡

የአባታችን የመላከ ምህረት ተግባር በዚህ አጭር ጊዜ ፅፎ ማቅረብ አዳጋች ነው....... አባታችን በተጨማሪም ለሀገር አለኝታ ለእመጓ ተስፋ በመሆን መንፈሳዊ ስራዎችን በመስራት የቆዪ ሲሆን ህመማቸው
ሣይቆይባቸው ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም
በተወለዱ በ 98 አመታቸው ከዚህ አለም አርፈዋል::

የእርሳቸዉ የህይወት ታሪክ በርካታ እና ተፅፎ የማያልቅ ነዉ

አብዛኞቻችሁም ስለምታዉቋቸዉ ሙሉ ታሪካቸዉን በቀጣይ እንፅፍላቸዋለን!!

የአባታችን በረከትና ረድኤታቸው አይለየን።

Aki Man Z Menz
85 viewsAki_man , 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 15:22:47
118 viewsAki Man, 12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 15:21:55 በመዲናዋ ሲሚንቶ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ታሸጉ

የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ የማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር እንደሚሰራ ገልጾ፤ የተሰጡ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያዎችን በተላለፋ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

እርምጃው የተወሰደባቸው በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙና አለአግባብ ከተተመነው የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ፣ ምርት በመደበቅ መሸጫ ቦታቸውን ዘግተው በመጥፋት የተገኙ ሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል።
117 viewsAki_man , 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 09:21:00 እኔ የሁሉም ነኝ




አርሲ ተወልጄ ጐጃም ሄጄ ያደኩ
ጅጅጋ ተምሬ መቀሌ የተመረኩ
ሀመርዋን አግብቼ ሶዶ ላይ የወለድኩ
.
.
.
ባሕሌ ጉራማይሌ ስበትን ሚፈጥር
   ካገኘሁት ጋር የምኖር በፍቅር
ዑራኤል ቁጭ ብዬ አዛን  እየሰማው
      ቅዳሴ ምቀድስ
አንዋር ቁጭ ብዬ አሀዱን ሰምቼ
        ቁርአንን ምቀራ
               .
               .
     ......አዎ እኔ ልዩ ነኝ......
መልኬ ጠየም ያለኝ የደስደስ
በሄድኩበት ሁሉ ፍቅር ና ፈገግታን
      በአንድ ላይ ምለግስ
.
.
.
      በአንድ አንገቴ ላይ
ማተብ እና ኢማማን ሁለቱን ያረኩኝ
ሂጃቤን ጠምጥሜ ነጠላ የደረብኩኝ
.
.
.
እምነት ነው ፅናቴ, ሀይማኖቴም ፍቅር
   ተጠልዬ ምኖር ከቅድስቷ ምድር
106 viewsAki_man , 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 15:58:41 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

@Aki Man Z Menz
37 viewsAki_man , 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 09:55:54
ዐቢይ አሕመድ ያሠማራው ታጣቂ የኢንዱስትሪ መናኸሪያ በመሆኗ የምትታወቀውን የደብረ ብርሐን ከተማ በከባድ መሣሪያ እየደበደበ ነው።
95 viewsAki_man , 06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 09:51:10 መከላከያ ደብረብርሃን ህዝብ ላይ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው። መረበሽ አያስፈልግም ወንድም ወንድሙን ይጠብቅ
መዳኛዉ ከህዝብ ጎን መቆም ብቻ ነዉ
96 viewsAki_man , 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 09:50:46 በውጭ አገር ለምትኖሩ የአማራ ልጆች በሙሉ በኦነግ ሸኔ ታጣቂ የአማራን ሕዝብ ጨፍጭፎ መጨረስ እንደማይቻል የተረዳው አረመኔያዊ ሥርዓት ያለ የሌለ ወታደሩን አዝምቶ የአማራን ሕልውና ለማክሰም እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ የወገናችሁ ድምጽ እና ክንድ ሁኑ።
95 viewsAki_man , 06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:04:58
ምን ጎሎበት ሸዋ ~የአባ መስጠት ልጅ
ልክ እንዳመጣጡ ~ ይመልሳል እንጅ
(የሸዋ ጩህት አራት ኪሎ ድረስ ይሰማል )
107 viewsAki_man , 14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ