Get Mystery Box with random crypto!

Aki Man Z Menz

የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz A
የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz
የሰርጥ አድራሻ: @akiman12345
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 334

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-11-11 11:49:18
31 viewsAki_man , 08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 11:49:12 #ትኩረት
በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በታች ይገም ቀበሌ ትላንት አመሻሹ ላይ በመሄድ ትዉልድን የሚያነሳሳ ለኛ ደጎሞ ትዉስታ መቼም የማይረሳ ገጠመኞችን ይዘን ተመልሰናል።
ይሄዉም በታች ይገም ቀበሌ ለመሃልሜዳ እና ለመንዝ ላሎ የቅርብ ረቀት የሆነዉ እና በአራት የመደበኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ማለትም በማዕከል፣ በጢጠር ፣ነቢድ አምባ ...ትምህርት ቤቶች ቁጥራቸዉ ከ2000 የማያንሱ ተማሪዎች ይማራሉ፣ ነገር ግን አብዛኞቹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ማለትም ደብተር ፣እስኪብርቶ ፣እርሳስ ፣ የተለያዩ አጋዥ መፅሐፎችን እንደሚፈልጉ እና እንደሚያስፈልጋቸዉ ተመልክች እና ተረድቼ ተመልሻለሁ።
ከእህታችን በፀሎት አደራ ባለፈዉ ሳምንት የመጣዉን ደብተር ከጎድጓዲት ከአቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል ትምህርት ቤት ላይ በመቀነስ ቁጥራቸው ወደ 576 የሚደርሱ ደብተሮችን ከቦታው ላይ በመገኘት ለዉስን (30) ተማሪዎች መስጠት የቻልን ሲሆን ለቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ በመምህሮቻቼዉ እና በርዕሰ መምህሩ በኩል እንዲደርሳቸዉ ፣በየስም ዝርዝራቸዉ አስረክበናል።
በዚህ ወቅት በርካታ ነገሮችን የታዘብኩ ሲሆን እንደሚከተለው ላጋራችሁ ወደድሁ
1) ይህ ቀበሌ በወረዳችን ከሚገኙ ቀበሌዎች በተሻለ መልኩ የወረዳው መንግስት ማገዝ እንዳለበት
2) የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት ከሌሎች ትምሙ ቤቶች በተሻለ መልኩ ትኩረት በመስጠት የአጋዥ መፅሃፍትን እና የእገዛ ክትትል ቢያደርግ (ከ1_8ኛ ክፍል የሚማሩበት ትምህርት ቤት የአጋዥ መፅሐፍት የሌለበት በመሆኑ)
3 ) ለሌሎች ትምህርት ቤቶች የመጣ/የሚመጣ የቁሳቁስም ሆነ የአጋዥ መፅሀፍት እርዳታ ካለ በቅድሚያ እንዲደርሳቸዉ (ከዞን ድረስ የመጡ እንግዶች እኝህን ተማሪዎች አይተዉ እንደተፀፀቱ እና እንዳለቀሱ ከዛም እገዛ እንደሚያደርጉላቸዉ ነግረዉኛል እና የቻሉትን ማድረግ ቢችሉ።)
4) በዚህ ቀበሌ ከፍተኛ የሆነ የብርድ ቦታ ስለሆነ የአልባሳት አጋዥ ባለሃብቶችን እና ተቋማቶችን በማፈላለግ ድጋፍ የሚያገኙበትን መድረክ ማመቻቼት ቢቻል......
5) እኝህ እንቁ ተማሪሩ ይህንን ሁሉ ችግር እና ብርድን ተቋቁመዉ በትምህርታቸዉ በጣም ጎበዝ መሆናቸዉን የነገሩን መምህራኖች በቀጣይ ህዳር 11የሚከበረውን የህፃናት ቀን በዚህ ትምህርት ቤት ለማክበር ወስነን ተመልሰናል።
6) በዚህ ትምህርት ቤት የተማራችሁ ተማሪዎች ፣ ከዚህ አካባቢ የወጣችሁ ባለሃብቶች ለእኝህ የነገ ተስፋዎች የማገዝ እና የማበረታታት ሀላፊነት አለብን የሚል መልዕክት አለኝ።
N.B ይህ እንዲሆን እና ይህንን ትዉልድ እንዳይ እና በቦታው ተገኝቼ ችግራቸዉን እንድጋራ ያደረከኝ እንቁ ወንድሜ ሽመልስ ፅጌ አመሠግናለሁ ወደፊትም ተጋግዘን እንደምናግዛቸዉ ሙሉ እምነት አለኝ።
ይህንን ከቦታዉ ድረስ እንዲደረስ ያገዘን ወንድማችንን ጳዉሎስ ገ/ፃዲቅም ምስጋና ይድረስህ!
የቀድሞዉ ርዕሰ መምህርም ቦታዉን በመምራት የተማሪዎቹን ሁኔታ ስላጋራሃን አመሠግናለሁ ወደፊትም የምናግዝበትን መንገድ እናመቻቻለን የሚል ፅኑ አቋም አለኝ።
የብርዱን ነገር ግን አታንሱብኝ
30 viewsAki_man , 08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 15:31:36 ይህንን እፈልጋለሁ ። እንደዚያ ይሆናል ። ሄንሪ ፎርድ

ትልቅ ጥቅም የሚሰጠው ቀደም ብለው ስህተት ለሚሠሩ ሰዎች ለመማር ነው። ዊንስተን ቸርችል

አደጋዎች የሉም - በዚህ ዓለም ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ወይ ፈተና ፣ ወይም ቅጣት ፣ ወይም ሽልማት ፣ ወይም አስጸያፊ ነው። ቮልቴር

አንድ ሰው አመለካከቱን ብቻ በመቀየር ህይወቱን መለወጥ ይችላል። ዊልያም ጄምስ

ስኬትን ከፈለጋችሁ እና ለውድቀት ከተዘጋጁ, ያኔ እርስዎ እያዘጋጁት ያለውን በትክክል ያገኛሉ. ፍሎረንስ ሺን

ሕይወትን ለመምራት ሁለት መንገዶች ብቻ አሉ። የመጀመሪያው ተአምራት አለመኖሩ ነው። ሁለተኛው - በዙሪያው ተዓምራቶች ብቻ እንዳሉ. አልበርት አንስታይን

ዛሬ ጠዋት አንድ ጥሩ ነገር ይከሰታል ብለው በማሰብ በየቀኑ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከእንቅልፍዎ ከተነቁ. ዊል ስሚዝ

ሁሉም ሰው ዓለምን መለወጥ ይፈልጋል, ግን ማንም እራሱን መለወጥ አይፈልግም. ሌቭ ቶልስቶይ

የብልህ ሰዎች እና መሪዎች መለያ ምልክት፡-ከጥቂት ሰዎች ጋር ያለው ጥልቅ ግንኙነት እንጂ ከሰው ሁሉ ጋር ላዩን አይደለም። Henrik Fenheus

የማይቻል ነገር ከሞኞች መዝገበ ቃላት የወጣ ቃል ነው። ናፖሊዮን ቦናፓርት


በደስታ የመኖር ታላቁ ሳይንስ በአሁኑ ጊዜ ብቻ መኖር ነው። ፓይታጎረስ

ማድረግ የሚችሉት፣ የማይችሉት፣ ሌሎችን ያስተምሩ። ጆርጅ በርናርድ ሻው

እራስዎን መለወጥ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያስቡ, እና ሌሎችን የመለወጥ ችሎታዎ ምን ያህል ቀላል እንዳልሆነ ይገባዎታል. ቮልቴር

በሚወዱት ሰው ውስጥ ጉድለቶች እንኳን ይወዳሉ ፣ እና በማይወደው ሰው ውስጥ ፣ በጎነቶች እንኳን ያበሳጫሉ። ኦማር ካያም

የሚናገረው ነገር የሌለው ሰው ብዙ ይናገራል። ሊዮ ቶልስቶይ

ሥራ አንድን ሰው ከሦስት ዋና ዋና ክፋቶች ያድናል: መሰላቸት, ምክትል እና ፍላጎት. ቮልቴር

በወንድና በሴት መካከል ያለው ጓደኝነት የማይቻል ነገር ነው; በመካከላቸው ፍቅር ፣ ጠላትነት ፣ አምልኮ ፣ ፍቅር ፣ ግን ጓደኝነት አይደለም ። ኦስካር Wilde


ቆንጆ ሴት ዓይንን ደስ ያሰኛል, ለልብ ግን ደግ ናት; አንዱ የሚያምር ነገር ነው, ሁለተኛው ደግሞ ውድ ሀብት ነው. ናፖሊዮን ቦናፓርት

በነፍስ ደካማ የሆኑት ውሸት ያስፈልጋቸዋል. ማክሲም ጎርኪ

ሕይወት ሊተነበይ የሚችል ቢሆን ኖሮ ሕይወት መሆን ያቆማል እና ጣዕሟን ያጣ ነበር። ኤሌኖር ሩዝቬልት

ማለቂያ የሌላቸው ትናንሽ ሰዎች እጅግ በጣም ትልቅ ኩራት አላቸው. ቮልቴር

ደስ የሚል የፊት ገጽታ ቀስ በቀስ በውስጣዊው ዓለም ውስጥ ይንጸባረቃል። አማኑኤል ካንት

በሰው መሻሻል - የህይወት ትርጉም. ማክስምመራራ

አንድ አይነት አስተሳሰብ እና ወደ ችግሩ የመራዎትን ተመሳሳይ አካሄድ ከያዙ ችግርን በፍፁም መፍታት አይችሉም። አልበርት አንስታይን


የልማዳችን ባሮች ነን። ልምዶችዎን ይቀይሩ, ህይወትዎ ይለወጣል. ሮበርት ኪዮሳኪ

ደስተኛ የመሆን ጥበብ በቀላል ነገሮች ውስጥ ደስታን የማግኘት ችሎታ ላይ ነው። ሄንሪ ዋርድ ቢቸር

ችግሮች ሲያጋጥሙህ ተስፋ መቁረጥ አትችልም፣ ሩጡ። ሁኔታውን መገምገም, መፍትሄዎችን መፈለግ እና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሆነ ማመን አለብዎት. ትዕግስት የድል ቁልፍ ነው። ኒክ Vujicic

አንድ ነገር ባገኙ እና ምንም ነገር ባላገኙ መካከል ያለው ልዩነት የሚወሰነው ቀደም ሲል ማን እንደጀመረ ነው። ቻርለስ ሽዋብ

እራስህን መሆንህን እወቅ እና መቼም በእጣ እጅ ውስጥ መጫወቻ አትሆንም። ፓራሴልሰስ

እውቀት በቂ አይደለም, ተግባራዊ ማድረግ አለብዎት. ምኞት በቂ አይደለም, ማድረግ አለብዎት . ብሩስ ሊ

ያገኙትን ካልወደዱ የሚሰጡትን ይቀይሩ። ካርሎስ ካስታንዳ


ትርጉም የለሽ ሕይወት መኖር ዋጋ የለውም። ሶቅራጠስ

የባህር ዳርቻው እይታ እንዳይጠፋ ከፈራህ ውቅያኖሱን በፍፁም አትዋኝም። ክሪስቶፈር ኮሎምበስ

አንድ ሰው በሌሎች ላይ ስህተት ሲሠራ በሕይወቱ ውስጥ በአንዱ መስክ ትክክል ማድረግ አይችልም። ሕይወት የማይከፋፈል ሙሉ ነው። ማህተመ ጋንዲ

በሃያ አመት ውስጥ ከሰራህው ስራ ይልቅ ባልሰራህው ነገር ትፀፀታለህ። ስለዚህ, ጥርጣሬዎችን ያስወግዱ. ከአስተማማኝ ወደብ ይርቁ። በሸራዎችዎ የጅራት ንፋስ ይያዙ. ያስሱ። ህልም. መክፈት. ማርክ ትዌይን።

ከቀኑ 2/3 ለራሱ ሊኖረው የማይችል ባሪያ መባል አለበት። ፍሬድሪክ ኒቼ

ያለማቋረጥ የምናደርገው እኛ ነን። ስለዚህ, ፍጹምነት ተግባር አይደለም, ነገር ግን ልማድ ነው. አርስቶትል

ራስህን ፈጽሞ አቅልለህ አትመልከት። ሌሎች የሚያደርጉትን ሁሉ እርስዎ ማድረግ ይችላሉ። ብሪያን ትሬሲ


የሺህ ማይል ጉዞ የሚጀምረው በአንድ ትንሽ እርምጃ ነው። ላኦ ትዙ

እጣ ፈንታችን የሚቀረፀው በቀን 100 ጊዜ በምንወስናቸው ትንንሽ የማይታዩ ውሳኔዎች ነው። አንቶኒ ሮቢንስ
23 viewsAki_man , 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 15:24:46 ጥላቻ የተሸናፊዎች ዕድል ነው። - ኮንፊሽየስ.

እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ከጉድለታችን እንድንፈወስ በሚያስፈልጉን ሰዎች ይከብበናል። - የአቶስ ስምዖን.

ሰው የሚቃወምበት እስር ቤት አለ። - Epictetus.

ከእኛ የባሱ ሰዎች ብቻ ስለእኛ መጥፎ የሚያስቡ እና ከእኛ የሚበልጡ ብቻ ለእኛ ደንታ የላቸውም። - ኦማር ካያም.

ቴክኖሎጂ ከሰው ልጅ ግንኙነት የሚበልጥበት ቀን ይመጣል ብዬ እሰጋለሁ። አለም ደግሞ ሞኝ ትውልድ ታገኛለች። - አልበርት አንስታይን

ወደ ከዳተኞች መመለስ አይችሉም። የተከለከለ ነው። ክርናችሁን ነክሱ ፣ ምድርን አኝኩ ፣ ግን ወደ ተከዳችሁበት አትመለሱ ። - ዣን ሬኖ


በአንበሳ የሚመራ የበግ ሰራዊት ሁል ጊዜ በግ የሚመራውን የአንበሳ ሰራዊት ያሸንፋል። - ናፖሊዮን ቦናፓርት.

ነፍስ ከአእምሮ በተለየ መልኩ አታስብም ወይም አታስብም - ይሰማታል እና ያውቃል, ስለዚህ ስህተት አይሠራም. - ቪ ዜላንድ

አሁንም የዘላለምን ህይወት መግዛት ካልቻላችሁ ለአንድ መቶ አመት አንድ ሳንቲም መቆጠብ አስቂኝ አይደለምን? ይህ ሕይወት ለእርስዎ ተሰጥቷል ፣ ውዴ ፣ ለተወሰነ ጊዜ - ጊዜ እንዳያመልጥዎት ይሞክሩ! - ኦማር ካያም.

ጥርጣሬያችን ከሃዲዎቻችን ነው። ለመሞከር ካልፈራን ልናሸንፍ የምንችለውን እንድናጣ ያደርጉናል። - ደብሊው ሼክስፒር

ልምድ በዋጋ ሊተመን የማይችል ነው, ብቸኛው መጥፎ ነገር በራስዎ ወጣትነት መክፈል አለብዎት. - ስቲቭ ሃርቪ

ነፍስ ወደ አንድ ሰው ከደረሰች አትቃወሙ ... የሚያስፈልገንን በትክክል የምታውቅ እሷ ብቻ ነች። - Erich Maria Remarque.

ጥሩ ሀሳቦች በወጣትነት ጊዜ ብቻ ወደ አእምሮአቸው ይመጣሉ, ከዚያም አንድ ሰው የበለጠ ልምድ ያለው, የበለጠ ታዋቂ እና ደፋር ይሆናል. - አልበርት አንስታይን


ሊገለጽ የማይችል ነገር ነፍስ ነው. የት እንዳለ ማንም አያውቅም, ግን እንዴት እንደሚጎዳ ሁሉም ሰው ያውቃል. - ኤ.ፒ. ቼኮቭ.

ብዙ ማሰብ የለብዎትም። መጀመሪያ ላይ ያልነበሩ ችግሮችን የሚፈጥሩት በዚህ መንገድ ነው። - ፍሬድሪክ ኒቼ

መውደድ ማለት ሰውን እግዚአብሔር ባሰበው መንገድ ማየት ማለት ነው - ኤፍ.ኤም. Dostoevsky.

በእውነት የምትፈልገውን አንድ ነገር ለማድረግ በወሰንክበት ደቂቃ በህይወት ውስጥ ፍጹም የተለየ ጅረት ይጀምራል። - ሪቻርድ ባክሚንስተር ፉለር

ሰዎችን ነጻ ማድረግ ከፈለግክ መጀመሪያ እራስህን ነፃ አድርግ። መወደድ ከፈለግክ መጀመሪያ ራስህን ውደድ። የሆነ ነገር ከፈለግክ መጀመሪያ የራስህ ስጥ። - V. Likhachev.

በፈለከው መንገድ መኖር ራስ ወዳድነት አይደለም። ራስ ወዳድነት ሌሎች ማሰብ እና በፈለጋችሁት መንገድ መኖር ሲገባቸው ነው። - ኦስካር Wilde.

ከአሳማ ጋር በጭራሽ አይጣሉ። ብቻ ይቆሽሹ, እና አሳማው ይደሰታል. በሌላ አነጋገር፡ ለጭቅጭቅ ሲሉ መጨቃጨቅ ከሚወዱ ሰዎች ጋር በመጨቃጨቅ ጊዜህን አታጥፋ። - ኤሪክ ማኮርማክ.


ዓይኖቹ ወደ ሰማይ ሲቀመጡ, ሰማዩ በውስጣቸው ይንፀባርቃል. ረግረጋማውን ሲመለከቱ, ረግረጋማው ይንፀባርቃል. ፈቃዳችን እና ምርጫችን ዓይኖቻችንን የምናዞርበት ነው። - ዲ. Yemets.

እራስን መስጠት ማለት መሸጥ ማለት አይደለም, እና ከራስ አጠገብ መተኛት ማለት መተኛት ማለት አይደለም, አለመበቀል ማለት ሁሉንም ነገር ይቅር ማለት አይደለም. መለያየት ደግሞ አለመውደድ ማለት አይደለም... - ኦማር ካያም

በራስዎ ላይ ያለዎትን እምነት ለማዳከም የሚሞክሩትን ያስወግዱ። ይህ ባህሪ የአነስተኛ ሰዎች ባህሪ ነው. በሌላ በኩል ታላቅ ሰው አንተም ታላቅ መሆን እንደምትችል እንዲሰማህ ያደርጋል። - ማርክ ትዌይን.
24 viewsAki_man , 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 15:17:03 #ህሊናህን_አትሽጥ
#የፈለገው ነገር ቢቸግርክ ለሰዎች ጉልበትክን፣ እውቀትክን እንጂ ህሊናህን አትሽጥ አታስገዛ።
#ህሊና ያጣ ሰው ከሰውነት ተራ የወጣ ሰው ነው።
#ህሊና ማለት ከፈጣሪ በታች ስህተታችንን የሚያሳየን ከሳሻችን ነው።
#ከሳሽ ከሌለ ደግሞ ወንጀል ይበራከታል፣ ወንጀል ከተበራከተ ደግሞ ወንጀለኛ ይበዛል ፣ወንጀለኛ ከበዛ ደግሞ ሀገር ትጠፋለች።
26 viewsAki_man , 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 10:21:45
279 viewsAki_man , 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:36:17
74 viewsAki_man , 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:36:06 የአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ጸበል ከረጅም ገደል ላይ እየተወረወረ የሚወርድና በንጽህና ወደ ጸበሉ ለገባ ጸበልተኛ የቀስተ ደመና ግምጃ በሰውነቱ ላይ ተጠምጥሞ ያያል፡፡ "ወደ እግዚአብሄር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መስዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመስራት አዋቂዎች አይደሉምና፤" ተብሎ በመጽሀፈ መክብብ 51 እንደተጻፈው ስርዓተ እግዚአብሄርን ሳይጠብቅ ወደ ጸበሉ የገባ ሰው የምህረት ቀስተ ደመናው ሊታየው ቀርቶ በዘንዶና በእባብ ተከቦ ከጸበሉ ውስጥ ይባረራል፡፡ ጸበሉ ከላይ ሲወርድ የሚከፍለው ነገር ባይኖርም ከገደሉ ላይ ሲደርስ ከሁለት ተከፍሎ ይፈሳል፡፡ አንደኛው ለአጠቃላይ ደዌዎች ፈውስነት ሲያገለግል ሁለተኛው ደግሞ በቀጭኑ እየፈሰሰ የራስ ምታት ህመምን ይፈውሳል፡፡ብዙዎች ምእመናን ከደዌያቸው እየተፈወሱ የልባቸውን መሻት እያገኙ ወደየባእታቸው በመመለስ የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን ድንቅ ተአምር ይመሰክራሉ፡፡ በመዝ. 337 "የእግዚአብሄር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል"፡፡ ተብሎ እንደተጻፈው በአልጋ መጥተው በደስታ በእግራቸው እየዘመሩ ይመለሳሉ፡፡
በአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ሌላው ድንቅ ተዓምር ከሚፈጸምባቸው ውስጥ በፊት ከጸበሉ ስር እንደ ነበር የሚነገርለትና በአሁኑ ወቅት ተንሸራቶ በቤተ-ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አራት ዛፍ በመሆን የተቀመጠው የሾላ ዛፍ ፍሬ ይጠቀሳል፡፡ መውለድ ያልቻሉ እናቶች የሾላውን ፍሬ በልተው የተመኙትን ፀንሰው ይወልዳሉ፡፡ ካንሰርና መሰል ደዌ ያለባቸው ምእመናን ፍሬውን ተመግበው ከደዌያቸው ይፈወሳሉ፡፡
ስለቤተክርስቲያኑ ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ካነሳን አሁን ደግሞ በደብሩ ጸበልና የሾላ ፍሬ የተፈጸሙ ገቢረ ተአምራቶችን እንመልከት፡፡ ይህ ደብር ከተተከለ ጀምሮ የተለያዩ ገቢረ ተአምራቶች ሲፈጸሙ እንደቆዩ መላከ ምህረት አባ አምሳሉ ያዩትንና በታሪክ ያገኙትን ይናገራሉ፡፡
አንዲት ሴት ወደ ቤተ-ክርስቲያኑ ግቢ መጥታ ካስቀደሰች በኋላ የስለት እጣን ከመስኮት ላይ ተቀምጦ ስታገኝ ይዛ ወደ ቤቷ ለመሄድ ትነሳለች፡፡ ከቤተክርስቲያኑም ብዙም ርቃ ሳትሄድ ከመንገዱ ላይ እባብ አንገቱን ቀና አድረጎ ቆሞ አገኘችው፡፡ እሷም ስህተቷ ቶሎ ገብቷት አውቄዋለሁ ቅዱስ ሚካኤል ያውልህ ብላ ወደ ኋላ ስትወረውረው እባቡ መንገዱን ለቆ እንደሄደ ከአባቶች ያገኙትን ተአምር የደብሩ አስተዳደር መላከ ምህረት አባ አምሳሉ ገልጸዋል፡፡ አሁንም ቢሆን የቤተክርስቲያኑን ንብረት ለመዝረፍ የሚሞክር በእባብ፣ ዘንዶና ንብ ይከበባል፡፡
ሌላው በቅርብ ጊዜ እንደተፈጸመ የሚነገርለት ደቡብ ክልል አጋሮ ወረዳ በመንግስት ሰራተኛነት ተሰማርታ የምትኖር እንስት ለአቅመ ሂዋን ከደረሰች በኋላ ባል አግብታ ልጅ ለመውለድ ብታስብም ለአማታት ሊሳካላት አልቻለም፡፡ ዝናውን ሰምታ ወደ አጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል በመምጣት የሾላ ፍሬውን በጸበል አድርጋ ጠጥታ ወደ ቤቷ እንደተመለሰች ጸንሳ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፡፡
ስእለቷም በዚህ ደብር አምጥታ ክርስትና ማስናሳት ቢሆንም ወቅቱ ክረምት ስለነበር ሰው ሲያከላክላት ሳትመጣ ትቀራለች ከዚያም ክርስትና ካስነሳችበት ቤተ ክርስቲያን ሳትመለስ ገና ልጁ በህይወትና በሞት መካከል ሆነባት ደስታው በሀዘን ተለወጠ፡፡ መነኩሲት አክስቷ መጥተው በይ ተነሽ ወደ አጃና ሚካኤል እንሂድ ብለዋት እሬሳ የመሰለውን ህጻን ይዘው ጉዞ ጀመሩ፡፡ ከአጃና ሚካኤል ቤተክርስቲያን መድረሻ አካባቢ ስትደርስ የመውረጃ ደረጃውን እየወረደች የህጻኑን እግር ድንጋዩ ሲነካዉ ህጻኑ ድምፅ አሰማ፡፡ ትንሽ እንደተጓዘች ሽንቱን ሸና ቤተ- ክርስቲያኑን ሶስት ጊዜ ስትዞር ፍጹም ጤነኛ ህጻን ሆኖ ጡት ጠባ በማለት እራሷ በአውደ ምህረት ላይ ቀርባ የተናገረችውን ምስክርነት አባቶች ይናገራሉ፡፡


በተጨማሪ አንዲት ጸበልተኛ ውስጧን ንጹህ ሳታደርግ የሰራችውን ሀጥያት በንሰሃ ሳታወርድ በድፍረት ወደ ጸበሉ ስትገባ ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ ከስውነቷ ላይ ግዙፍ እባብ ተጠመጠመባት እባቡን ማንም ሊያስለቅቀው ስለማይችል የሰራችውን ሀጥያት እንድትናገር አባቶች ጠየቋት በእናቷ ልጅ በእህቷ ላይ ያልተገባ ተንኮል እንደፈጸመች ስትናገር እባቡ ምንም ጉዳት ሳያደርስባት ለቋት ተሰወረ፡፡
በዚሁ ወረዳ ሰላድንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት በጉልበቱ ሰርቶ ራሱንና ቤተሰቡን ለመርዳት ጥረት ሲያደርግ አንድ ቀን ከስራ ውሎ ሲመለስ በድንገት ያመዋል፡፡ ቶሎ ብሎ ወደ ሀኪም ቤት በመሄድ ይታከማል፡፡ አሁንም ሊድን አልቻለም እንዴውም በሽታው እየጨመረ መጣ፡፡ ድጋሚ ወደ ግል ሀኪም ቤት በመሄድ 10 መርፌና ኪኒን ታዘዘለት፡፡ በእግሩ ይሔደ የነበረውን አልጋ ላይ ዋለ፡፡ ግራ ሲገባው በባጃጅ ወደ አጃና ሚካኤል ጸበል ሄደና መጠመቅ ጀመረ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በሰው እርዳታ የሚንቀሳቀሰውን ወጣት በአንድ ወር ውስጥ ተሸክሞት የመጣውን አልጋ ራሱ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲመለስ የምህረት በትሩን ላከለት፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጤነኛ ሆኖ የጉልበት ስራውን እየሰራ ምድራዊ ኑሮውን እየመራ ይገኛል፡፡ የሚሉት ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ቀጥለን ደግሞ በአሁኑ ሰአት በደብሩ ምን እየተሰራ ነው የሚለውን እንመልከት፡፡ የአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ከተመሰረተ ጀምሮ ረጅም እድሜ ቢያስቆጥርም በርካታ ተአምራቶችን ቢፈጸምበትም የእምነቱ ተከታዮች ወደ ቦታው በመሄድ ፈውስን ለማግኘት ቢመኙም ጉልበት ያለው ካልሆነ በስተቀር የመኪና መንገድ ባለመሰራቱ ለአዛውንቶች እና ህሙማን የማይታሰብ ነበር፡፡ይህንን በመረዳት ደብሩ ከህዝቡና ከበጎ አድራጊዎቹ ገንዘብ በማሰባሰብ በዶዘር የቆረጣ እና ጠረጋ ስራ ማሰራት ተችሏል፡፡ አሁን ላይ አቅም በማጣት ስራው ቢቆምም ኮሚቴ በማቋቋም ስራውን ለማስጨረስ በእንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡ ጸበልተኞች ወደ ቦታው ሲመጡ መጠለያ እንዳይቸገሩ የተለያየ መጠን ያላቸውን የሴትና የወንድ መጠለያ አዳራሾች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ሰፊ የሆነ የቦታ ችግር እንደለባት በመረዳት ከቀበሌ እስከ ወረዳ ካሉ የአስተዳደር አካላት ጋር በመነጋገር ይዞታ ለማስከለል በሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዋሻዎቹ ጉዳት ሳይደርስባቸው የተለያየ አገልግሎት እየሰጡ እንደተጠበቁ ይገኛሉ፡፡
ለዚህ ሁሉ ሀይማኖታዊ እና ልማታዊ እንቅስቃሴ ዉጤታማነት ህዝበ ክርስቲያኑ ያደረገው እና እያደረገ ያለው መልካም ተግባር በመሆኑ ለዚህም ደብሩ በእግዚአያብሄር ስም ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይም ከቤተክርስቲያኒቱ ጎን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ከቅዱስ ሚካኤል ምህረትንና ፈውስን እንዲሁም ሀይማኖታዊ አገልግሎት መስጠትም ሆነ ታአምራቶቹን ማየት የምትሹ ምእመናን በሙሉ ወደዚህ ወደ ተቀደሰ ቦታ መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ስም እንጋብዛለን፡፡
70 viewsAki_man , 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:36:06 የአጃና ደብር ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ታሪክ
የአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል በሃገረ እግዚአብሄር ኢትዮጲያ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጃና ወደራ ወረዳ አይሶፌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሚገኝ ሲሆን ከወረዳው ዋና ከተማ ደቡብ ምእራብ አቅጣጫ 12ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤልን ለማግኘት ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በስተሰሜን አቅጣጫ 130 ኪ/ሜ ከተጓዙ በኋላ ጥንታዊቷን የደብረ ብርሃን ከተማ ያገኛሉ፡፡ ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ 50ኪ/ሜ የአስፋልት ጉዞ እንደጨረሱ ቀዝቃዛዋንና የመንዝ ደሴና ሰላድንጋይ መገንጠያ የሆነችውን አነስተኛዋን ከተማ ጣርማበርን ያገኛሉ፡፡ ከጣርማበር በስተምዕራብ አቅጣጫ 22ኪ/ሜ በጠጠር መንገድ እንደተጓዙ በ1875 ዓ.ም አፄምኒልክ የቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያንን ሲያሰሩ ለ6ወር መዲና አድርገዋት የነበረችውንና ንጉስ ሳህለስላሴ ተወልደው ክርስትና የተነሱባት ሰላድንጋይ ከተማን ያገኛሉ፡፡ ከሰላድንጋይ በስተምዕራብ ሳሲት በር እየተባለ በሚጠራው መንገድ 12 ኪ.ሜ የመኪና እና 10 ደቂቃ የእግር ጉዞ በኋላ በትላልቅ ሀገር በቀል ዛፎች ታጥሮ ከረጅም ገደል ላይ የሚወረወር ተዓምረኛ ጸበል ወደሚገኝበት አጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ደብር ይደርሳሉ፡፡አጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤልን በደገኛው ንጉስ አፄ ዘርያዕቆብ የተተከለችው ደብረ ምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም፣ አፄ ሚኒሊክ ከግብፅ አገር አስመጥተው ያስተከሉት ቅዱስ ማርቆስ፣ምስካበ ቅዱሳን መድኃኒያለም አንድነት ገዳም፣የነጭ ገደል በዓታ እና እምብስ ዋሻ ቅዱስ ጊወርጊስ ያዋስኑታል፡፡
ይህ ቤተክርስቲያን በማን እና እንዴት እንደተመሰረተ ከማንሳታችን በፊት "አበው ውኃን ከጥሩ ነገርን ከስሩ" እንዲሉ ይህ ቦታ ምን ነበር የሚለውን እንይ፡፡ የአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከመቆርቆሩ በፊት አካባቢው በደንና በሳር የተሸፈነ ባዶ ቦታ እንደነበረና ሳሩም ሆነ ደኑ ባለቤት የሌለው መሆኑና የቦታውን ምቹነት በማየት ደብሩን የቆረቆሩ አባት ወደዚህ ቦታ እንደመጡና እንዳቀኑት ቀደምት አባቶች ይናገራሉ፡፡
የክርስትና እምነትን ኢትዮጲያ ከተቀበለችበት ከ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ አባቶች በዱር በገደል ጽላቶችን በመሸሸግና ለአማንያኑ በማስተማር ወደ ማህል አገር እና ሰፊ የእምነቱ ተከታይ ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ በአዲስ ያቋቁሙ ነበር፡፡ በመዝሙረ ደዊት 3319 "የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው እግዚያብሄርም ከሁሉ ያድናቸዋል" እንዳለው በእግዚያብሄር ፍቃድ በብዙ መከራ እና ስቃይ በክርስትና እምነት ላይ ከተሰነዘሩ ጥቃቶች ካተረፏአቸው ጽላቶች መካከል የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል አንዱ በመሆኑ በንጉስ ስብስቲያኖስ ዘመነ መንግስት ሁለተኛው የኢትዮጵያ ጳጳስ አባ ሰላማ መልካም ፍቃድ መምህር አግናጢዮስ ከአህያ ፈጅ ቁስቋም ፅላቱን በማምጣት በአንካሴያቸው በፈለፈሉት ዋሻ ውስጥ እንዳኖሩትና ከዚያን ጀምሮ ደብሩ እንደተመሰረተ ይነገራል፡፡ መ/ር አግናጢዮስ ከአህያ ፈጅ ቁስቋም ተነስተው ገራዶ ዋሻ የሚባል ቦታ ጽላቱን አሳርፈው ቦታ መፈለግ ጀመሩ፡፡ እግዚአብሄር የፈቀደውን ቦታ ማግኘት ባለመቻላቸው እንደገና ጽላቱን ይዘው ጎድጓዲት የሚባል ቦታ ላይ ድንኳን በመትከል ለ21ቀን ሱባኤ ገብተው በ21ኛው ቀን ተነስተው አሁን ወዳለበት ቦታ ይዘው እንዲሄዱና በአንካሴያቸው ዋሻ ፈልፍለው እንዲያኖሩ ታዘዙ፡፡ እርሳቸውም ያንኑ ፈጸሙ፡፡ ምንም እንኳን ደብሩ ከተመሰረተ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ በገዳምነት ቢታወቅም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከገዳምነት ወደ ደብርነት በመቀየር ለህዝበ ክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ መምህር አግናጢዮስ ከላይ መቋሚያ ከታች አንካሴ በሆነ መሳሪያ መጀመሪያ የራሳቸውን በዓት ከፈለፈሉ በኋላ ቀጥለው የፅላቱን መኖሪያ ፈልፍለው ጽላቱን በዋሻ አኖሩ፡፡ በአካባቢው ሰው ባለመኖሩ አገልጋዮች ከሩቅ ቦታ እያመጡ በወር አንድ ጊዜ ያስቀድሱ ነበር ፡፡ አልፎ አልፎም አገልጋይ ከጠፋ አባ ኃብተማርያም ኬሻ ዝተት በመልበስ ያጥኑ እንደነበር ቀደምት አባቶች ይናገራሉ፡፡
ደብሩ መተዳደሪያ የሚሆን ኃብት ስላልነበረው እና አካባቢው የሳር ምድር ስለነበር 30 ላሞች ማርባት ጀመሩ ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከላሞቹ መካከል ገና ጊደር የነበረችው አንዷ ነጭ ላም ጠፋች፡፡ እረኞችም ፈልገው ሊያገኟት አልተቻለም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ "እግዚዓብሔር ላመኑት እንደሃሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን" እንዳለው የላሟን መጥፋት ለበጎ ነው ብለው እንደተቀመጡ ከቀናት በኋላ ላሟ ከጸበሉ መነሻ አካባቢ እረኛው የማያውቀው ነገር ስትልስ ያገኛትና የምትልሰውን ለቃ ወደ ጓደኞቿ እንድትቀየጥ ቢደበድባትም ልትሄድ ባለመቻሏ ለመምህር አግናጢዮስ ይነግራቸዋል፡፡ እርሳቸውም ቀረብ ባለው መንገድ እረኛው እንዲወጣ አዘው ርቀት ባለው መንገድ ጉዞ ጀመሩ፡፡ በምን እንደወጡ ሳይታወቅ እረኛውን ቀድመውት ቦታው ላይ ደረሱ፡፡ ወደዚያው ላሟ የምትልሰውን ነገር ለቃ ገለል አለች፡፡ ተጠግተው ሲየዩትና ሲያነሱት ከሰማይ የወረደ መስቀል ሆኖ አግኝተው በደስታ ለፈጣሪያቸው ምስጋና ሲያቀርቡ የፀበሉ መነሻ ትንሽ ትንሽ ይመነጭ የነበረው ሽቅብ እንደዘለለ ያገኘነው ታሪክ ያስረዳል፡፡ " እግዚአብሄርም ለህዝቡ መድሃኒት ላከ ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ" ተብሎ በመዝ.1109 ላይ እንደተፃፈው በጸበሉ ላመኑት የበዛና የበለጠ ሁሉ መዳኛ ተገኘ፡፡ ከዚያን ጀምሮ ጸበሉ በነብርና ዘንዶ ይጠበቃል፡፡ መስቀሉም አሁንም በቤተ-ክርስቲያኑ በክብር ተቀምጦ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዙ ምእመናንን በመፈወስ ላይ ይገኛል፡፡
መ/ር አግናጢዮስ የፈለፈሏቸው ዋሻዎች ብዛት 5 ሲሆኑ እያንዳንዳቸው የብርሃን ማስገቢያ የጭስ መውጫና ውስጥ ለውስጥ መዘዋወሪያ ያላቸው ናቸው፡፡ ሁሉም ዋሻዎች የየራሳቸው አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ መጀመሪያ የተፈለፈለው ዋሻ ሴቶች እንዲገቡ የማይፈቀድላቸው የመ/ር አግናጢዮስ መኖሪያ፣ሁለተኛው ደግሞ የታቦቱ መኖሪያ ሲሆን የተቀሩት ዋሻዎች የእቃ ቤት፣ የአገልጋዮች መኖሪያና የግብር ቤት በመሆን ያገለግሉ ነበር፡፡ መ/ር አግናጢዎስ የራሳቸውን መኖሪያ ዋሻ በ2፡30 ሰዓት፣ የጽላቱን መኖሪያ ደግሞ በ3፡30 ሰዓት ፈልፍለው እንዳጠናቀቁት እድሜ ጠገብ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ታሪክ ይናገራሉ፡፡ ዋሻዎቹ ሲታዩ ፍጹም በእግዚአብሄር ኃይል እንጂ በሰው ጉልበት ለዚያውም በአንካሴ ተፈለፈሉ ብሎ ማመን ይከብዳል፡፡
ከቀልቦ ደን ቆመብሴ በማምጣት ቤተ-ክርስቲያን ከተሰራ በኋላ ታቦቱ ከዋሻ ወጥቶ ወደ ተሰራው ቤተ-ክርስቲያን ሲገባ የታቦቱ መኖሪያ የነበረው ዋሻ አሁን ድረስ በንብ መንጋ እየተጠበቀ እቃ ቤት በመሆን ያገለግላል፡፡ ከንቡ የሚገኘውን ማርም የበቁ አባቶች ጸሎት እያደረጉ ማሩን ይቆርጡ ነበር፡፡ ከመ/ር አግናጢዮስ ህልፈተ ሞት በኋላ ማሩ ተቆርጦ እንደ ማያውቅ ይነገራል፡፡የአጃና ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ከተተከለ በኋላ
64 viewsAki_man , 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 11:53:04
በስማ በለው ~ በሬ ወለደ
የሀሰት ሞቱን ~ ቆሞ የለመደ

ካስመሳይ ሊኖር ስላልወደደ
ዛሬስ የእውነቱን ታዝቦን ሄደ። RIP
37 viewsAki_man , edited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ