Get Mystery Box with random crypto!

#ትኩረት በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በታች ይገም ቀበሌ ትላንት አመሻሹ ላይ በመሄድ ትዉልድን የሚ | Aki Man Z Menz

#ትኩረት
በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በታች ይገም ቀበሌ ትላንት አመሻሹ ላይ በመሄድ ትዉልድን የሚያነሳሳ ለኛ ደጎሞ ትዉስታ መቼም የማይረሳ ገጠመኞችን ይዘን ተመልሰናል።
ይሄዉም በታች ይገም ቀበሌ ለመሃልሜዳ እና ለመንዝ ላሎ የቅርብ ረቀት የሆነዉ እና በአራት የመደበኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ማለትም በማዕከል፣ በጢጠር ፣ነቢድ አምባ ...ትምህርት ቤቶች ቁጥራቸዉ ከ2000 የማያንሱ ተማሪዎች ይማራሉ፣ ነገር ግን አብዛኞቹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ማለትም ደብተር ፣እስኪብርቶ ፣እርሳስ ፣ የተለያዩ አጋዥ መፅሐፎችን እንደሚፈልጉ እና እንደሚያስፈልጋቸዉ ተመልክች እና ተረድቼ ተመልሻለሁ።
ከእህታችን በፀሎት አደራ ባለፈዉ ሳምንት የመጣዉን ደብተር ከጎድጓዲት ከአቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል ትምህርት ቤት ላይ በመቀነስ ቁጥራቸው ወደ 576 የሚደርሱ ደብተሮችን ከቦታው ላይ በመገኘት ለዉስን (30) ተማሪዎች መስጠት የቻልን ሲሆን ለቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ በመምህሮቻቼዉ እና በርዕሰ መምህሩ በኩል እንዲደርሳቸዉ ፣በየስም ዝርዝራቸዉ አስረክበናል።
በዚህ ወቅት በርካታ ነገሮችን የታዘብኩ ሲሆን እንደሚከተለው ላጋራችሁ ወደድሁ
1) ይህ ቀበሌ በወረዳችን ከሚገኙ ቀበሌዎች በተሻለ መልኩ የወረዳው መንግስት ማገዝ እንዳለበት
2) የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት ከሌሎች ትምሙ ቤቶች በተሻለ መልኩ ትኩረት በመስጠት የአጋዥ መፅሃፍትን እና የእገዛ ክትትል ቢያደርግ (ከ1_8ኛ ክፍል የሚማሩበት ትምህርት ቤት የአጋዥ መፅሐፍት የሌለበት በመሆኑ)
3 ) ለሌሎች ትምህርት ቤቶች የመጣ/የሚመጣ የቁሳቁስም ሆነ የአጋዥ መፅሀፍት እርዳታ ካለ በቅድሚያ እንዲደርሳቸዉ (ከዞን ድረስ የመጡ እንግዶች እኝህን ተማሪዎች አይተዉ እንደተፀፀቱ እና እንዳለቀሱ ከዛም እገዛ እንደሚያደርጉላቸዉ ነግረዉኛል እና የቻሉትን ማድረግ ቢችሉ።)
4) በዚህ ቀበሌ ከፍተኛ የሆነ የብርድ ቦታ ስለሆነ የአልባሳት አጋዥ ባለሃብቶችን እና ተቋማቶችን በማፈላለግ ድጋፍ የሚያገኙበትን መድረክ ማመቻቼት ቢቻል......
5) እኝህ እንቁ ተማሪሩ ይህንን ሁሉ ችግር እና ብርድን ተቋቁመዉ በትምህርታቸዉ በጣም ጎበዝ መሆናቸዉን የነገሩን መምህራኖች በቀጣይ ህዳር 11የሚከበረውን የህፃናት ቀን በዚህ ትምህርት ቤት ለማክበር ወስነን ተመልሰናል።
6) በዚህ ትምህርት ቤት የተማራችሁ ተማሪዎች ፣ ከዚህ አካባቢ የወጣችሁ ባለሃብቶች ለእኝህ የነገ ተስፋዎች የማገዝ እና የማበረታታት ሀላፊነት አለብን የሚል መልዕክት አለኝ።
N.B ይህ እንዲሆን እና ይህንን ትዉልድ እንዳይ እና በቦታው ተገኝቼ ችግራቸዉን እንድጋራ ያደረከኝ እንቁ ወንድሜ ሽመልስ ፅጌ አመሠግናለሁ ወደፊትም ተጋግዘን እንደምናግዛቸዉ ሙሉ እምነት አለኝ።
ይህንን ከቦታዉ ድረስ እንዲደረስ ያገዘን ወንድማችንን ጳዉሎስ ገ/ፃዲቅም ምስጋና ይድረስህ!
የቀድሞዉ ርዕሰ መምህርም ቦታዉን በመምራት የተማሪዎቹን ሁኔታ ስላጋራሃን አመሠግናለሁ ወደፊትም የምናግዝበትን መንገድ እናመቻቻለን የሚል ፅኑ አቋም አለኝ።
የብርዱን ነገር ግን አታንሱብኝ