Get Mystery Box with random crypto!

Aki Man Z Menz

የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz A
የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz
የሰርጥ አድራሻ: @akiman12345
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 334

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-12-05 23:32:43 ሕዝቡ ይሄን ሥርዓት ማሽቀንጠር አለበት" የሚል ትዕዛዝ ከማስተላለፍህ በፊት የብልጽግና አባል ተብለው ወርሐዊ ክፍያ ከሚከፍሉትና ፓርቲውን ከተሸከሙት 4 ሚሊዮን አማራዎች መሀከል አንዱ አለመሆንህን አረጋግጥ!
አሳዬ ደርቤ
26 viewsAki_man , 20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 16:14:46 ልምጭ
""""""""""
ከተማሪው አይደል፣
ከትምህርቱም አይደል፣
አልያም ከጠመኔው ከጥቁሩ ሰለዳ፥
ዕውቀት የሚያጣመም
የሚሆን ወልጋዳ።

ይልቅስ...
የየኔታ ልምጭ ያልሞካከረችው
በጀርባው ላይ አርፋ፣
የጊዜው ምሁር ነው
በሸውራራ ዕውቀት ተማሪ ሚያጠፋ!
45 viewsAki_man , 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 10:50:23
70 viewsAki_man , 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 10:50:09 ☞ከእግዚአብሔር ቤት መራቅ ስትጀምር ፍቅር ከአንተ ትርቃለች፡፡
:
►ከምታየው ነገር ጋር ሁሉ ትጣላለህ፡፡
:
►የምትጣላው ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ከምታገኘው ሁሉ ነገር ጋር እና ከራስህ ጋር ጭምር ነው፡፡
:
►ከራስህ ጋር ተከራክረህ ራስህን መርታት ከማትችልበት ጭንቀት ውስጥ ትወድቅና የሞትህን ጊዜ ታመቻቻለህ፡፡
:
►እንደ ይሁዳ ታንቆ ለመሞት አልያም አንደሌሎች በሌላ ምክንያት ራስህን እስከማጥፋት ድረስ ማንነትህን ትጠላለህ፡፡
:
►ራስህን እንደ ሰው መቁጠር ከማትችልበት ከባድ ሙግት ውስጥ ትወድቃለህ፡፡
:
►በዚህም ከአምላክ ጋር እና ከሰዎች ጋር በፍቅርና በሰላም መኖር አልችል ትላለህ፡፡
:
►ሁልጊዜ ከሰዎች ጋር ክርክር እና ጥላቻ ይሆንብሃል፡፡
:
►ጠላትን የምታጠፋበት ትልቁ መሣሪያ ፍቅር ብቻ መሆኑን ትዘነጋለህ፡፡
:
☞ይህን የከበረ ዕንቁ የማይስተካከሉትን ልዩ ጸጋ ማጣት ማለት ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሰው ሆኖ አለመገኘት ማለት ነው፡፡
:
︵‿♡︵✿︵♡︵ ︵‿♡︵✿︵♡︵
:
#አዎን ወዳጆቼ፥

☞የሰውነት መመዘኛው ትልቁ ሚዛን ፍቅር ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ያለው....
:
“በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ሆኛለሁ፡፡
:
ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትንም ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ፡፡
:
ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም፡፡
:
ፍቅር ይታገሣል ቸርነትንም ያደርጋል ፍቅር አይቀናም ፍቅር አይመካም ፍቅር አይታበይም የማይገባውን አያደርግም የራሱንም አይፈልግም
አይበሳጭም በደልንም አይቆጥርም ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጅ ስለ አመፃ ደስ አይለውም ሁሉን ይታገሣል ሁሉን ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይጸናል፡፡
:
ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም… እንዲሁም ከሆነ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው፡፡” /1ኛ
ቆሮ13 ÷ 1-13/
:
☞ፍቅር በሰዎችና በመላእክት ልሳን ከመናገር በላይ ነው፡፡ ድሆችንም ከመመገብና ሥጋችንን ለእሳት አሳልፈን ከመስጠት የላቀ ነው፡፡
:
☞እውነተኛ ፍቅር የሚታገስ፣ ሁሉን የሚያምን፣ ከእውነት ጋር ደስ የሚለው፣ የማይቀና፣ ቸርነት የሚያደርግ፣ የማይመካ፣ በደልን የማይቆጥር፣ ሁሉን ተስፋ የሚያደርግ ነው፡፡
:
☞ይህን ፍቅር የምናገኘው ደግሞ ከእግዚአብሔ ጋር በመሆን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር ነውና፡፡

☞ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ እንዲህ ይላል “… ወዳጆቼ ሆይ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለሆነ
የሚወደው ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ እርስ በርሳችን እንዋደድ” /1ኛ ዮሐ4÷7/
:
☞ለዚህም ነው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሔር ስትርቅ ፍቅር ደግሞ ከአንተ የምትርቀው፡፡ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ በመሆኗ ትልቅ ገንዘብ ናት፡፡ ፍቅርን የምንገልጸው ሰውን፣ እግዚአብሔርን
እንዲሁም አገርን በመውደድ ነው፡፡
:
#የፍቅር አምላክ ንጹሕ ፍቅርን ያብዛልን!"(አሜን)
:
"በቸር ያቆየን!"
:
(ሙሌ ቤስት 11/7/9 ዓ/ም አርባምንጭ~ኢትዮጵያ)
68 viewsAki_man , 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 10:36:38 #አልልሽም
:
:
ከፍጥረት ለይቶ እንደሰራሽ በማር
የውበትሽና የፀባይሽ ማማር
ባንድ ተሰባጥሮ አቅሌን አስቶኛል
አንደኛዬ ነሽ ግን ማለት ይከብደኛል።
:
:
ጡት እንዳጣ ዕፃን ልጅ ስነፋረቅ ውዬ
ልክ ዐይንሽን ሳየው በደስታ ዘልዬ
ማልቀሴን ረስቼ ሰላም አድሬያለው
አንደኛዬ እኮ ነሽ ማለት ግን ፈራለው።
:
:
የህይወቴ ግማድ የመኖሬ ጉዳይ
የደስታዬ ወሰን የአንድ ልቤ ሙዳይ
አንቺ እንደሆንሽ ባውቅም
የኔ አንደኛ ብዬሽ አልመፃደቅም።
:
:
ተንጠራርተሽ ደርሰሽ አቅፈሽ በሹክሹክታ
ዐይን ዐይኔን እያየሽ ስትዪኝ የኔ ጌታ
ሀሴት ይወረኛል ከእግር እስከ ፀጉሬ
አንደኛዬ ነሽ ግን አልልም ደፍሬ።
:
:
እውነት ነው የኔ ውድ እንዴትስ ደፍራለው
አንቺን እንዲ ማለት በጣሙን አፍራለው።
:
:
አንቺን አቅፎ ኖሮ አንቺን አቅፎ መሞት ምን ልቤ ቢመኝም
ተቀየሚኝ እንጂ አፈር እስክገባ አንደኛዬ አትሆኚም።
እንደው ቢሆን እንኳን አንደኛዬ እንድልሽ እውን ፈልገሽም
ሲያምርሽ ይቅር እንጂ መቼም አልልሽም።
:
:
ምክንያቱም ውዴ ...
አንደኛ ነው ሲባል አንድ ነገር ደርሶ
ሁለተኛ ሆኖ ከእርሱ ትንሽ አንሶ
የሚፎካከረው ሌላ አካል እንዳለ
መረዳት ቀላል ነው በደንብ ላስተዋለ።
:
:
ስለዚም እንቁዬ ...
በውበት በፀባይ ሁለተኛ ሆኖ ካንቺ ሚወዳደር
ቢፈለግ አንዳች ሰው በሌለበት ሀገር
አንደኛዬ እኮ ነሽ እንዴትስ እላለው
ብቸኛዬ ሆነሽ ብቻሽ ሆኜ ሳለው።
61 viewsAki_man , 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 15:45:05
የጌታቸው ረዳ እና ጄኔራል ፃድቃን መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች
በድርድሩ መቀሌን አትርፈንበታል፣ተገደን ቢሆንም ድርድር አድርገን የተኩስ አቁሙን ስምምነት ፈርመን መጥተናል። ይሄን ያደረግነው ግን የትግራይ ህዘብ አሁናዊ ሁኔታ እና መጠነ ሰፊ ችግሮች ነው ብለዋል።
ሌላው በመግለጫቸው ያነሱት ይሄ ስምምነት ከወታደራዊ አኳያ የሀይል መዛባት አምጥቶልናል።ድርድሩን ያካሄድነው የውጪ ሀይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስለተስማማን የኤርትራ እና የአማራ ልዩ ሀይል ከትግራይ እንዲወጣ ስለሆነ ይህ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ሌላው ስምምነቱ የራስን እድል በራስ ለመወሰን ከፍተኛ ዕድል ፈጥሮልናል፣ጥቅምት 18 መከላከያ መቀሌ ገብቶ ቢሆን ይሄን እድል አናገኝም ነበር ብለዋል።
ሌላው የትግራይ መንግሥት እና ህወሃትን እመኑ፣እኛ የትግራይ ህዝብን የሚጎዳ ነገር ላይ አልፈረምንም። እኛን እመኑ ሲሉ በተማፅኖ ደረጃ ተናግረዋል።
የኤርትራ ሰራዊት አሁንም ውድመት እያስከተለ ነው፣ከትግራይ በሰላም ለቃ  እንድትወጣ እንጠይቃለን። ይሄ ካልሆነ ግን የኤርትራ ህዘብ ዋጋ ይከፍላል ሲሉ በመግለጫቸው አንስተዋል።
ለድርድሩ ጉዞ የአሜሪካ ወታደራዊ መስሪያ ቤት የበራራ አውሮፕላን እንደላከላቸው እና በዚህ አውሮፕላን እንደወጡ አንስተዋል። ጅቡቲ ላይም ሁለት ጊዜ ከመንግሥት አመራሮች ጋር እንደተገናኙ ተናግረዋል።
አዩ ዘ ሀበሻ
55 viewsAki_man , 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 15:34:19 እንኳን ለገናናው መልዐክ ለሊቀ መላዕክት ለቅዱስ ሚካኤል በዓል አደረሰን::

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡
+ ጻዲቁ ንጉሥ በእደ ማርያም ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣ በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡

ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀንበእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡  

ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡›› የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የተበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን እንቸላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡     

እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናለቸዋል፡፡ እነሆ ይህ ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ነገር ግን ወደቤቱ ሳይርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንድሰነጥቅ አዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300 የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡

እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››      
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
ምንጭ:—ከገድላት አንደበት
53 viewsAki_man , 12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 20:02:40 በወለጋ ኪረሙ በርካታ አስኬሬን መሰብሰባቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። እጅግ አሳዛኝ ነው። ኦነግ ሸኔ መጠነ ሰፊ ጥቃት እያደረሰ ነው
39 viewsAki_man , 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 18:40:18 #ተጀመረ

በእንቁ መምህር እና ታዋቂ የባህል ህክምና በሆኑት መምህር ወልደሃና ወልደዮሐንስ የአቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል ትምህርት ቤት ገቢ ማሰባሰቢያ መረሃ ግብር ተጀምሯል።

እኝህ እንቁ መምህር እና ፍቱን የባህል ሀኪም ሲሆኑ ከ200 በላይ ለሚሆኑ በሽታዎች ፍቱን መሆናቸዉ የተመሰረተላቸዉ የመንዝ ፈርጥ አባታችን በዘንድሮዉ የበጎ ሰዉ ተሸላሚ መሆናቸዉን ዓለም ያዉቃል።

ይሁን እንጂ በዚህ ተቋም ከ7_12ኛ ክፍል የተማሩበት ሲሆን በርካታ ትዝታዎችን ያሳለፉበት ተምረዉም ከምሁር እስከ ሀኪም ፣ ከዶክተር እስከ ዶክትሬት ድግሪ የደረሱ ተማሪዎችን አስተምረዉ አብቅተዋል።

እናም በዛሬዉ ስብሰባችን በርካታ ሀሳቦችን ያነሱ ሲሆን ለመጀመሪያ የሚሆን 10,000 ( አስር ሺህ ብር) ቃል የገቡ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በሁለት ሺህ ብር ጀምረዋል።

ከመገረም እና እድሜ ይስጠዎት ከማለት ዉጭ በኔ አንደበት የነሱ ታሪክ እና ቀናነት የሚፃፍ ስላልሆነ በዚሁ ልቋጨዉ እና የሚከተሉትን አጭር መልዕክቶች ላስተላልፍ።

1) ሁሉም የመንዝ እና የይፋት አዉራጃ የቀድሞዉ ተማሪዎች

2) ከቀበሌ እስከ ፌደራል ያላችሁ የመንግስት ሰራተኞች

3) ሀገር ዉስጥም ይሁን ከሀገር ዉጭ ያላችሁ ባለሃብቶች እና ሀገር ወዳድ እህት ወንድሞቻችን ሁሉ...

4) ሁላችሁም ሀገር ወዳድ እና ይህንን ትልቅ እንዲሁም ታሪካዊ ትምህርት ቤት ለመደገፍ የሁላችንንም ጥረት እና ቅንነት ይጠይቃል።

ስለሆነም ከዚህ በታች ባሉት የትምህርት ቤቱ አካዉንቶች ማገዝ ይኖርብናል

የአቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሚቀጥለዉ ሚያዚያ ወር 2015 ዓ.ም 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን ለማክበር በሚያደርገዉ ዝግጅት የት/ቤቱን ችግሮች በመቅረፍ ተቋሙ ለተማሪዎች ምቹ የት/ቤት አካባቢ እንዲሆን ለማድረግ እና ጥራት ያለዉ ትምህርት ለትዉልዱ ለማድረስ የሚደረገዉን ጥረት እንድትደግፉ ትዉልድ አድን ጥሪያችንን እያስተላለፍን ቀጥሎ ባሰፈርናቸዉ አካዉንት ቁጥሮች እና ስልክ ቁጥሮች የገንዘብ እና የሃሳብ ድጋፍ እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

3301119111862015 አባይባንክ

1000508370998 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

4789501000416 ቡና ባንክ

5653362311011 ዳሸን ባንክ

115782808 አቢሲኒያ ባንክ

013250413486000 አዋሽ ባንክ

መረጃ ለምትፈልጉ ስልክ ቁጥሮች

0920481112 ኩራ ድፋባቸዉ - ር/መ/ር

0911719403 መ/ር ወልደሃና ወልደዮሐንስ -የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ

0910768690 አቶ ጥበቡ ታደሰ የአብይኮሚቴ ሰብሳቢ

Aki Man Z Menz
34 viewsAki_man , 15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 18:40:17
31 viewsAki_man , 15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ