2023-01-12 11:01:29
#አቤቶ_ነጋሲ...!!
አቤቶ ነጋሢ ክርስቶስ!!
ይህንን አንጋፋ ትምህርት ቤት የ75ኛ ዓመት በዓሉን ስናከብር የበረካታ ታሪክ መነሻና መዳረሻ መሆኑን ለማስተዋወቅ እናም በትምህርት ቤቱ ዉስጥ የምናሳካቸዉ ዘርፈ ጉዳዮች አሉን።
ሆኖም አብዛኞቻችን ስለ አቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል/ ስለዚህ አንጋፋ ትምህርት ስያሜ ጥያቄ ዉስጥ አሳድሮብናል እናም አጠር ባለ ቋንቋ ታሪካዊ ዳራዉን ለማስቀመጥ እወዳለሁ።
አቤቶ ነጋሲ ክርስቶ የአቤቶ ሁን ያዕቆብ የልጅ ልጅ ልጅ ሲሆኑ በ1633 ዓ.ም መንዝ እመዝዋ ተራራ ላይ ነጋሪት ጎስመዉ የሸዋ ንጉስ መሆናቸዉን ያወጁ የሸዋ ስርዎ መንግስት መስራች ናቸዉ፡፡
በ1688 ዓ.ም የጎንደሩ ንጉስ አጼ ኢያሱ ከጎንደር ደብረሊባኖስ ድረስ መጥተዉ የነጋሲ ክርስቶስን የሸዋ የበላይ መስፍንነታቸዉን እንዳጸኑላቸዉ በታሪክ ተመዝገቦ ይገኛል፡፡
ነጋሲ ክርስቶስም ግዛታቸዉን እያስፋፉ፤ከተሞችን እየከተሙ፤ አብያተክርስቲያናትን እያሰሩ፤ መሬት ሳይቀር ለህዝቡ እያከፋፈሉ ሸዋን ለ27 ዓመት ገዝተዉ በመጨረሻም በጎንደር የነበሩ ወንድሞቻቸዉን ሊተዋወቁ እንዲሁም ማህተም ሊያስቀርጹ እና ግብር ሊያስገቡ ጎንደር ሄደዉ በፈንጣ በሽታ ታመዉ በ1690 ዓ.ም ስለሞቱ እዚያዉ ጎንደር ፊት አቦ እንደተቀበሩ ታሪካቸዉ ያስረዳል፡፡
ነጋሲ ክርስቶስ ያስጀመሩትን የሸዋ ስርወመንግስት የሳቸዉ ልጆች አስቀጥለዉት እስከ ታላቁ ንጉስ እምየ ምኒልክ እና የት/ቤቱ መስራች እስከሆኑት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቀጥለዉ የእሳቸዉ እና የአባቶቻቸዉ ህልም የነበረችዉን ኢትዮጵያን እዉን አድርገዋታል፡፡
በ1954 ዓ.ም ት/ቤቱን አቤቶ ነጋሢ ክርስቶስ ወረደ ቃል ብለዉ የሰየሙት መምህር ወልደሐዋርያት ወ/ሚካኤል የሚባሉ ለንጉሰ ነገስቱ ቅርበት የነበራቸዉ መንዜ የቤተክርስቲያን ሊቅ እንደነበሩ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይሄዉም ነጋሲ ክርስቶስ ይጠሩ የነበረዉ በአባታቸዉ ሳይሆን በአያታቸዉ ቀረደ ቃል እንደነበረ ያነሰጥራል፡፡
ለዚያ ነዉ ት/ቤቱ አቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል ት/ቤት ተብሎ የተሰየመዉ፡፡ ተቋሙ እስከ 1954 ዓ.ም ድረስ አዳሪ ትምህርት ቤት እንደነበርም ታሪክ ያወሳል፡፡
አሁን ላይ ግን
የአስተዳደር ህንጻ/ አሁን ያለዉ ህንጻ እየፈረሰ ያለ እና በሰራተኞች ህይወት ላይም አደጋ የደቀነ መሆኑ /ሙሉ ለሙሉ መቀየር ያለበት
የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ መስጫ ክፍል አለመኖር
የመምህራን ማረፊያ አለመኖር
የጽዳት ክፍል አለመኖር
ደረጃዉን የጠበቀ የፊዚክስ ቤተ ሙከራ አለመኖር
ደረጃዉን የጠበቀ የባዮሎጅ ቤተሙከራ አለመኖር
የሂሳብ ክፍል አለመኖር
የቴክኒካል ድራዊንግ ክፍል አለመኖር
የአይሲቲ ማዕከል አመኖር
የአይሲቲ ቤተ ሙከራዎች በመማሪያ ክፍል ዉስጥ መሆን
የመሰብሰቢያ አዳራሽ አለመኖር
የትምህርት ማበልጸጊያ /ወርክ ሾፕ አለመኖር
የሰዉነት ማጎልመሻ/ስ/ሳ ክፍል አለመኖር
የትምህርት ክፍል ቢሮዎች አለመኖር
የመምህራን መዝናኛ አለመኖር
በቤተመጽሃፍ የመቀመጫ ወንበር እጥረት
የማንበቢያ ጠረንጴዛ እጥረት
የመጽሃፍት መደርደሪያ እጥረት
የላቦራቶሪ መስሪያ ጠረንጴዛዎች እጥረት
የኩርሲ እጥረት /ላቦራቶሪ
የቁም ሳጥን እጥረት/ላቦራቶሪ
ለየትምህርት ክፍሉ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች እጥረት
ለትምህርት ማበልጸጊያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች አለመኖር
በአይሲቲ ቤተሙከታዎች የኮምፒዉተር እጥረት
የኮምፒዉተር ማስቀመጫ ዴስኮች ችግር
ለአስተዳደር ስራ እና ለተለያዩ የስራ ጅፍሎች የሚያገለግሉ የኮምፒዉተር እጥረት
የፕሪንተር እጥረት
የፎቶ ኮፒ ማሽኖች፤የፋክስ፤እስካነር እንዲሁም ፕሮጀክተር አለመኖር
ለተማሪዎች እና መምህራን መዝናኛ ክፍል የሚሆኑ እቃዎች/ማቴሪያልስ / አለመኖር
የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች አለመኖር ...
ወ.ዘ.ተ ችግሮችን የምንሞላበት ጊዜዉ አሁን ነዉ!
ሁላችንም ታሪኩን በማስረዳት የበኩላችንን ማድረግ ይጠበቅብናል !!
Aki Man Z Menz
106 viewsAki_man , 08:01