Get Mystery Box with random crypto!

8:30 እንገናኝ #ተጠርታችኋል #ሁሉም_ኮሚቴ በዓሉን ለማክበር በሞላሌ ከተማ የከተማችሁ | Aki Man Z Menz

8:30 እንገናኝ


#ተጠርታችኋል
#ሁሉም_ኮሚቴ

በዓሉን ለማክበር በሞላሌ ከተማ የከተማችሁ እንግዶች እንዲሁም ይህ ትምህርት  ቤት ይመለከተኛል የምትሉ ሁሉ
ትምህርት ቤታችን በታላላቆቻችን በኩል ጠርቶናል።

የተወደዳችሁ የአቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል ትምህርት ቤት ፍሬዎችና የልማት ሀሳቡ ደጋፊዎች ሁሉ በተለይም በአካል መንዝ ምድር በነዋሪነትም ይሁን ለበዓል የተሰባሰባችሁ የማትቀሩበት ክቡር ጥሪ ተጠርታችኋል።

በትልቁ እቅዳችን ጉዞ ላይ እየተማከርን በዓሉን እንጨዋወትበት ሲሉ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ኩራ ድፋባቸውና ታላቁ አባታችን መምህር ወልደሃና ወልደዮሃንስ ተጣርተዋል።
ፕሮግራሙ ነገ ከሰዓት 8:30  በትምህርት  ቤቱ አዳራሽ  ይጀምራል።
ይህ ጥሪ የማይታለፍ የማይዘገይበት ነውና የቻላችሁ ሁሉ ታደሙ።

ይህ በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ
በሞላሌ ከተማ አስተዳደር ሞላሌ ከተማ የሚገኝ የ75 ዓመት አንጋፋ ትምህርት ብት ጥሪ ነዉ

ሼር በማድረግ መረጃውን ያድርሱልን።