Get Mystery Box with random crypto!

Aki Man Z Menz

የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz A
የቴሌግራም ቻናል አርማ akiman12345 — Aki Man Z Menz
የሰርጥ አድራሻ: @akiman12345
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 334

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-05 07:50:55
ማስታወቂያ
66 viewsAki_man , 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 07:50:34 አላቹ
66 viewsAki_man , 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 08:58:32 ◉ በህይወቴ ከተማርኩት ነገር ውስጥ አንደኛው ለሰዎች መልካም  ነገር ብታደርግ ለመልካምነትህ ከሰዎች ዘንድ ምላሽ መጠበቅ ሊጎዳ እንደሚችል ነው።
                ••●◉••
● አንዳንዱ መልካም ስታደርግ ሞኝ እንደሆንክ ሊቆጥርህ ይችላል።
              ••●◉••
◉ አንዳንዱ ደግሞ ከእሱ የሆነ ነገር ፈልገህ የምታደርግለት ይመስለዋል።
              ••●◉••
● ሌላኛው ደግሞ ከምስጋና ይልቅ ጠላትህ ሊሆን ይችላል። 
             ••●◉••
◉ እናም እልሀለሁ ለመልካምነትህ ከሰዎች ምላሽን አትጠብቅ!
             ••●◉••
● ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምላሹ ምንም ይሁን ምን መልካምነት አብሮህ ይሁን!  ፈጣሪህ ይከፍልሀልና! ••
               
31 viewsAki_man , 05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 17:01:54
60 viewsAki_man , 14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 16:26:57 #ባህላዊ መድኃኒቶች በጥቂቶቹ እናስተዋውቃቹ።

ከእነዚህ ውስጥ

1.#ጤና_አዳም ( Ruta chalepensis)፦ ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ መታወክ ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ሕመሞች መድኃኒት ነው።

2.#ዳማከሴ (holy basil, tulsi, Ocimum tenuifolium) ለጉንፋን ፣ ለከባድ ራስ ምታት (ማይግሬን) በአፍንጫ ተስቦ የሚወሰድ ፣ ለመተንፈሻ ቧንቧ ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድኃኒት ነው።

3.#ሬት (Aloes)ቅርፊቱ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ የማር ወለላ የመሰለው ነገር ከሌላ ምግብ ጋር አዋህዶ በመምታት የከሱ ሕፃናት ቢመግቡት ወዲያውኑ ያፋፋቸዋል ፣ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው ፣ ለፎረፎር ቢቀቡት፣ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደ ሻይ አፍልተው ቢጠጡት የመፈወስ አቅም አለው።

4.#የጫት_ቅርፊት ((KhatCutin)፦ ስጋ በልቶ አልፈጭ ብሎት ሆዱ የታወከ ሰው ወቅጦ ቀቅሎ ቢጠጣው ይድናል።

5.#አርማ_ጉሳ (Cleome gallaensis)፦ አረንጓዴውን ቅጠል በማድረቅ ወቅጠው እንደ ሻይ ለረጅም ጊዜ በመጠጣት የስኳር ህመምተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ፈጥኖ የማውረድና የመቀነስ አቅም አለው። ቅጠሉን ደግሞ በአረንጓዴነቱ ወቅጠው ጨምቀው ቢጠጡት ከቁርጥማት የመፈወስ ኃይልና የምግብ አፒታይት የመክፈት ኃይል አለው።

6.#ነጭ_ሽንኩርት(Garlic)፦ ለደም ዝውውር ፣ ለጨጓራ ፣ ለውስጥ ካንሰር፣ ለመተንፈሻ አካል፣ ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ አዋቂዎች በአብነት በመጥቀስ ይናገራሉ።

7.#የኮክ_ዛፍ_ቅጠል(Prunus persica)፦ የጋማና የቀንድ ከብቶች በድንገት ሲታመሙም ሆነ ሰዎች በድንገተኛ በሽታ ሲያዙ ከጤና አዳም ጋር ተወቅጦና ተጨምቆ ሲጠጡት ከህመማቸው ይፈወሳሉ።

8.#ግራዋ (Vernonia amygdalina) ተመርጦ 7 ቅጠሉ ተቀንጥሶ በሰው እጅ መድኃኒት ለበላ ሰው ቢያጠጡት የመፈወስ ኃይል አለው ፣ እንዲሁም በግራዋ የታጠበ እቃ(እንስራ) ሽታን የሚያመጡ ባክቴሪያዎችን ያጠፋል። ከዚህ በተጨማሪም ግራዋ የተተከለበት ቦታ እባብ ፈፅሞ አይኖርም።

9.#የነጭ_ባህርዛፍ_ቅጠሉ (White Eucalyptus globulus) ቅጠሉን በውሃ ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነትን ያለ ኪኒን በሁለት ቀን ውስጥ ፈውስ ያገኛል።

10.#ቀይ_ሽንኩርት(Red onion)፦ ለአጠቃላይ ጤንነትና ለደም ዝውውር ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር የዘር ፈሳሽ እጥረት ላጋጠማቸው ሰዎች በብዛት ለማመንጨት እንደሚያገለግል አባቶች ይናገራሉ ፤ ኮረሪማና ቆንዶ በርበሬ እነዚህ በአንድ ላይ ተቀምመው ለራስ ምታትና ለሆድ ቁርጠት ፍቱን መድኃኒት ናቸው።

11.#ዞጓራጋጅ(አማርኛ ስሙን ለጊዜው አላቀውም) ቅጠሉ በእንጨት የሚጠመጠም ሆኖ እንደ አሚቾ ስር የሚያኮርት ሲሆን ይኸው ስሩ ትክትክ ለያዘቸው ሕፃናትና ወባ ለያዛቸው ሰዎች አገልግሎት እንደሚውል አባቶች ይናገራሉ።

12.#ኦሞሮ፦ ይህ አረንጓዴ ተክል የእግር ወለምታ ላለባቸውና ሰውነታቸው ተቀጥቅቶ ደም ለቋጠረባቸው ቅጠሎቹን በውሃ ቀቅሎ ቦታውን በቅጠሉና በተቀቀለው ውሃ ደጋግመው ሲያሹት እጅግ ፍቱን መድሐኒት ነው እንዲሁም ሴቶች በወሊድ ወቅት የፈሰሳቸውን ደም ለመተካትና በወር አበባ ጊዜ ተቀቅሎ እንዲጠጡት ይደረጋል። ይህ መድኃኒት የቅጠላቅጠል ዝርያ ሲሆን ለወለደች ሴትና የወር አበባ ያየች ሴት ከአንድ ሣምንት ላላነሰ ጊዜ እየተቀቀለ እንዲጠጡት ይደረጋል። ምክንያቱም ቁርጠትን ይከላከላል፣ሆድ ያጥባል ተብሎ ስለሚታመን ነው።

13.#እንስላል(Dill) በውሃ ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል።

14.#የምድር_እምቧይ_ስሩ /አሚቾው/፡- ተወቅጦ የታመሙ ከብቶች እንዲጠጡት ሲደረግ ከብቶቹ ይድናሉ።

15.#መቅመቆ (Rumex abyssinicus)፦ የተባለ ተክል ስሩ ተወቅጦ እንዲደርቅ በማድረግ ዱቄቱ 2 ወይም 3 በሻይ ማንኪያ በውሃ በማፍላት እንዳሻይ ቢጠጣ የደም ግፊት ይቀንሳል።

16.#የእንጆሪ_ቅጠል (Berry leaves)በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል።

17.#ፌጦ(garden cress)፦ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል።

18.#ቀበርቾ /ቾሳ/ (Echinops kebericho) ከስራስር ክፍል የሚመደብ ሲሆን አገልግሎቱም ለድንገተኛ ህመም ፣ ውጋት ወዘተ በማኘክ የሚወሰድ ፈዋሽ መድኃኒት ነው።

19.#ጣዝማ ማር፦ ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የማር ዓይነት ሲሆን ከነጭ አዝሙድና ኮረሪማ ጋር በመቀላቀል ጠዋት ጠዋት ሁለት ማንኪያ በመውሰድ ከሳል ፣ ከአስም ፣ ከቁርጥማት ወዘተ ህመም መገላገል ይቻላል።
ይህንን መድኃኒት የወሰደ አንድ ሰው መድኃኒቱ እንዲሠራ ቢያነስ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ጊዜ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይጠጣ ይመክራል።

20.#ሎሚ( Lemon )ለብዙ ዘመናት ከምግብ መመረዝና ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የሆድ በሽታ ለመፈወስ ሲጠቀሙት የቆየ ባህላዊ መድኃኒት ነው።

21.#ልምጭ (Clausena anisata) ከድንገተኛ ህመም ፈዋሽ ሲሆን የጥርስ መፋቂያ ዓይነትና ለብዙ በሽታዎች ፍቱን መድኃኒት ነው፤ከበሽታዎቹም መካከል የአፍንጫ ነስርና ላለበት ሰው ነስሩን ለማስቆም ቅጠሉን በመበጠስና በማሸት ቢያሸቱት ፍቱን መድኃኒት ነው።

22.#እንቆቆና_መስመስ(Embelia abyssinica)፦ ለሆድ ትላትልና መሰል በሽታዎች ተፈጭቶና ተበጥብጦ ከኮሶ ጋር በመደባለቅና በመጠጣት ለኮሶ ትልና መሰል የሆድ ህመም መድኃኒት ነው።

23.#ሰንሰል_እና_አግራ( (Adhatoda schimperiana) ሰንሰል ከሀገር በቀል መድኃኒት ውስጥ የሚካተት ሲሆን ቅጠሉን በመበጠስ ተወቅጦ በሻይ ብርጭቆ አንድ በባዶ ሆድ ሲጠጡበት በወፍ በሽታ ለተጠቃ ሰው ፍቱን መድኃኒት ነው።

24.#የእንሰት_ስር(አምቾ) ( zoom out root)፦ ከውስጥ አካሉ የሚገኘው ውሃ እና አሚቾው ተቀቅሎ ደጋግሞ መብላት ከወፍ በሽታ ይፈውሳል እንዲሁም እንዲመግል የተፈለገ የተጎዳ የሰውነት አካልም ሆነ በሰውነት የወጣ ማንኛውም እባጭ መግል ሆኖ እንዲፈነዳ/እንዲወጣ የእንሰት አምቾ ተደጋግሞ ይበላል ፣ የተሰበረ አጥንት በወጌሻ ማጀል ሲያስፈልግ የተሰበረው ቦታ ለማለዘብ (ለማለስለስ) አምቾውን በእርጎ እያማጉ ደጋግሞ መብላት ነው ፣ በጠቦት ሾርባ ደጋግሞ መብላት በመኪናም ሆነ በጦር ሜዳ ስጋው የተቦጨቀ ወይም አጥንቱ ላይ አደገኛ ስብራት ያጋጠመው ቁስሉ እንዲሽር(እንዲጠገን) ያደርጋል።

25.#ኮሶ((Hagenia abyssinica)፦የደረቀ የኮሶ ዛፍ አበባ ከእንቆቆና መስምስ ወቅጦ በብርጭቆ በመጠጣት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትልን ጠራርጎ ማስወጣት ይቻላል።

26.#ሽፈራው_ሞሪንጋ((Moringa stenopetala)፦ይህ የዛፍ ቅጠል የማያድነው በሽታ የለም ይባላል የስኳር መጠንን ይቀንሳል ፣ የደም ግፊትን ይቀንሳል ፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል ቅጠሉን.... እንደ ሻይ ተፈልቶ ፣ ዱቄቱ ተወቅቶ በውሃ መጠጣትም ይቻላል ፤ እንዲሁም እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላትም ይቻላል።

ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ የተወሰደ።
61 viewsAki_man , 13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 11:07:45
እንዳትታለሉ
“የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን” ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ።

ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረገፆች አራት የግዕዝ ፊደላት ያሉትን የአንድ ብር ሳንቲም በ2 ሺህ ብር እና ከዚያም በላይ እንገዛለን የሚሉ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በስፋት ተስተውለዋል። ማስታወቂያዎቹ ኅብረተሰቡን ለማጭበርበር እየተነገሩ ያሉ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ባንኩ አሳስቧል።
=======
62 viewsAki_man , 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 09:38:10
አይኑን ሰ'ቶ ሄደ
በልቡ ብርሃን፣ከሰማይ ሊገባ:
አይኑን ሰ'ቶ ሄደ፣ሆደ ቡቡው ባባ።
ከሞቱስ እንዲህ ነው፣በደንብ ተዘጋጅቶ፡
እስከ ሒወት ፍፃሜ፣በጎ ስራ ሰርቶ።

እርግጥ፦
የኪራይ ቤታችን፣ይህች ከንቱ አለም፡
በብልጭልጭ አስራ፣መኖር ብታጓጓም፡
የሰማዩን ሒወት፣ፈፅሞ አንዘንጋ፡
ለምድሩ ስንሮጥ፣ከላይ እንዳይዘጋ።

እናም፦

ነገ መኖራችን፣ከዛሬ ተሻግረን፡
ዋስትና የለንም፣ሸክላ ሒወት ይዘን፡
የበደልነው ካለ፣ዛሬውኑ ይቅርታ፡
ሸፍጥ ቂም አሻጥር፣በጊዜ ይገታ፡
ለወደድናቸውም፣ፍቅራችን እንግለጥ፡
ዛሬ ነገ ስንል፣ሒወት እንዳታመልጥ፡
በየ'ለት ኑሯችን፣ሞታችን እናስብ፡
ከክፉ ነገሮች እንድንሰበሰብ፡፡

ድንቅ የጥበብ ሰው አ'ተናል።ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እመኛለው።
33 viewsAki_man , 06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 09:35:32 የዘንድሮ ፈረስ አይቀድምም ጋሪውን
አታውቀውም እና ሒያጅና ቀሪውን
አልሰማሁም አትበል
እያነባህ ጠብቅ መርዶ ነጋሪውን
26 viewsAki_man , 06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 23:41:23 ተረግጦ ተገፍቶ
አልቅሶ ተጠቅቶ
ተርቦ ተጠምቶ
በድንቁራና በሕማም ፣በስቃይ በርሃብ በችግር
እየተንገላቱ ዘላለም ከመኖር
ከእኩልነትና ከነጻነት ጋር ይሻላል መቃብር፤
እንኳን ከውርደት ጋር እንኳን ከችግር ጋር ከደዌ ከጥቃት
ከክብር ጋር ቢሆን ከብዙ ጌትነት
ኑሮ ጣዕም የለውም ፣ከሌለው ነጻነት፤
ባይንህ አስመስክረህ ፣አላፊ መሆኑን ሁሉም በየተራ
ሞት አይቀርምና ብትደፍር ብትፈራም፣
ያገሬ ልጅ ቁረጥ፣ መቃብር ለመውረድ ከመብትህ ጋራ፣
ወንድም ሲሆንና መልካም ሲሰራ እንጂ ከባዕድ የሚለየው
ነጻነትህንና መብትህን ከነሳህ ወገንም ጠላት ነው፡፡
24 viewsAki_man , 20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 23:35:01 እድሜ እያላላኝ ፡
ግዜ እየቀጣኝ
ብሸራረፍ እንኳን ፡
አረሳውም መልኳን።
እጇን ...
ትናንት ይመስላል የዳበስኩት፣
መጠበቅ አርቆኝ ያስተዋልኩት።
ደሞ..
የናፈኳት ሰሞን
አመት ቅፅበት ሲሆን
ግዜ ሚዛኑ ሲላወስ
አብራው ምታዘግም የኔ ነብስ
ትታያለች........ደጇን እንዳጠረች...።

                           
25 viewsAki_man , 20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ