Get Mystery Box with random crypto!

ተረግጦ ተገፍቶ አልቅሶ ተጠቅቶ ተርቦ ተጠምቶ በድንቁራና በሕማም ፣በስቃይ በርሃብ በችግር እ | Aki Man Z Menz

ተረግጦ ተገፍቶ
አልቅሶ ተጠቅቶ
ተርቦ ተጠምቶ
በድንቁራና በሕማም ፣በስቃይ በርሃብ በችግር
እየተንገላቱ ዘላለም ከመኖር
ከእኩልነትና ከነጻነት ጋር ይሻላል መቃብር፤
እንኳን ከውርደት ጋር እንኳን ከችግር ጋር ከደዌ ከጥቃት
ከክብር ጋር ቢሆን ከብዙ ጌትነት
ኑሮ ጣዕም የለውም ፣ከሌለው ነጻነት፤
ባይንህ አስመስክረህ ፣አላፊ መሆኑን ሁሉም በየተራ
ሞት አይቀርምና ብትደፍር ብትፈራም፣
ያገሬ ልጅ ቁረጥ፣ መቃብር ለመውረድ ከመብትህ ጋራ፣
ወንድም ሲሆንና መልካም ሲሰራ እንጂ ከባዕድ የሚለየው
ነጻነትህንና መብትህን ከነሳህ ወገንም ጠላት ነው፡፡